የቅስና ትርጉምና ሚና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፤ በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ወያኔ ጫካ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ለአገዛዙ የማትመች መሆኗን በመገንዘብ ጦርነት ከፍቶባት እየገዘገዛትና እያደማት መሆኑ ይታወቃል። ወያኔ ቤተክርስቲያኒቷ ለዘመናት የገነባችውን በህዝብ ዘንድ ያላትን ከበሬታና አለኝታነት ለመናድ ከሚጠቀምባቸው ሥልቶች ውስጥ አንደኛው፣ ቤተክርስቲያኒቷን በካድሬዎችና በሰላዮች መሙላት ነው። ወያኔ ታጋዮቹን ልብሰ ተክህኖ እያለበሰና በካህናት ትምህርት ቤት ውስጥ እያሰለጠነ “መምህር” የሚል ማዕረግ እየሰጠ በየቤተክርስቲያኑ ውስጥ አፈ ጮሌ ካድሬዎቹን አሰማርቷል። እነዚህ አፈ ጮሌ፣ ልበ ጩቤ “መምህር” ነን ባዮች የምዕመናን ቀልብ በመስለብ በየቤተክርስቲያኑ አወደ ምሕረት ላይ ቆመው እውነተኛ መስለው በመቅረብ ቤተክርስቲያኒቷን ወደማትወጣው አዘቅት ውስጥ ይዘዋት እየነጎዱ በመሄድ ላይ ናቸው።

በአሁኑ ጊዜ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የወረሯት ጊዜ ያመጣቸው “መምህራን” ተብየዎች ብቃቱ፣ ንጽህናው፣ግብረ-ገብነቱ፣ትምህርቱና ችሎታው ሳይኖራቸው የግል ጥቅማቸውን ለማጋበስ የክህነት አገልግሎትን እንደ አንድ ተራ የሙያ መስክ በመቁጠር በየቤተክርስቲያኑ ላይ  እንደ አልቅት ተለጥፈዋል። አብዛኛው ምዕመንም የክህነት አገልግሎት ለመስጠት ብቃት የሌላቸውን ‘ካህናት’ተብየዎችንና እንደ አሸን የፈሉትን ‘መምህራን’ ነይ ባዮች” የሚሰሩትን ጸረ-ክርስትና ደርጊት ቸል እያለ እንዲሁም እያየና አየሰማ “እግዚያብሔር ይጠይቃቸው” እያለ የራሱን ስራ በፈጣሪ ላይ እየጫነ እጁን አጣጥፎ ለነሱው እያጨበጨበ ተቀምጧል። ይህ ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰበት በመሄድ ላይ እንጅ ምንም ዓይነት መሻሻል እያሳየ አይደለም። አብዛኛዎቹ የዘመኑ መምህራን ነን ባዮች ሥራቸው ምዕመናንን ማደንዘዝና ማላሸቅ ነው። የስነሱ ተግባር ከተቻለ ለወያኔ ይደልዎ የሚል ካልሆነም ለወያኔ ባርነት የተመቻቸ የማይጠይቅና የማይመረምር በድን የሆነ ምዕመን ማደራጀት ነው። በዚህም ምክንያት ምዕመናን ሐይማኖታቸውን የሚያጸና ሥራ እንዳይሰሩ ተሸብበውና ተለጉመው ተይዘዋዋል።

እዚህ ላይ አንድ አስረጅ ለማቅረብ ያህል ክርስትና ሐይማኖትን ጠንቅቀው ባልተረዱና ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ወኔያቸው በከዳቸው ምዕመናን ቸልተኝነትና ተባባሪነት ምክንያት የአሌክሳንደሪያ ቨርጅኒያው ታደሰ ሲሳይ የተባለው ግለሰብ ስልጣነ ክህነቱ ቢገፈፍና ቢወገዝም እንኳን እስከ አሁን ድረስ ከቤተ መቅደስ ውስጥ አልወጣም ብሎ እንደ መዥገር ተጣብቆ የምዕመናንን ገንዘብ እየመጠጠና የለመደውን ድርጊት እየፈጸመ ይገኛል። እውነተኛ ክርስቲያኖች ለእምነታቸው ጽናት ከፍተኛ መስዋዕትነትን እንደሚከፍሉ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ቢያሳዩም፣ የሐመረ ኖህ ምዕመናን ግን በዝሙት የተጨማለቀውን ግለሰብ ሥልጣነ ክህነቱ መገፈፉ ከታወጀበትም በኋላ እንኳን እንደ ትክክለኛ ክህን እየቆጠሩ እየተጎናበሱለት ይገኛል። እንደዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ለቤተክርስቲያኒቷና ለምዕመናን ታላቅ ውድቀት ነው። በአካባቢው ያሉ ሌሎች ካህናትም ይህንን አፍጥና አግጦ የመጣ ጉዳይ አንዳንዶቹ “እኛ ምን አገባን” ብለው እንደ ተራ ነገር ሲያልፉት አብዛኛዎቹ ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ለታደሰ ሲሳይ ድጋፍ ሲሰጡና ሲከራከሩለት ይደመጣሉ።እርግጥ “ግም ለግም አብረህ አዝግም” እንደሚባለው እራሱ በዝሙት የወደቀ ካህን ነኝ ባይ ታደሰ ሲሳይን ያወግዛል ተብሎ አይጠበቅም። ለዚህም መሆን አለበት እነ መምህር ተስፋዬ መቆያ፣ መምህር ዘበነ ለማ፣ አባ ገብረወልድ፣ አባ ፊሊጶስ፣ ወይም ሌሎቹ ታደሰ ሲሳይን ሊያወግዙ ያልቻሉት።

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ “የቅስና ትርጉምና ሚና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን” በሚል ርዕስ የሰጡት ትምህርተ ወንጌል እጅግ ብስለት ያለውና የፓስተሮችንና የቄሶችን ልዩነት ፍንትው አድርገው አሳይተዋል። ቀሲስ አስተርአየ ለወደፊቱ ምዕመናን ምግባረ ብልሹ ካህናትን በተመለከተ በተለይም ሴት ምዕመናን ከጋጠ ወጥ ካህናትና መምህራኖች እራሳቸውን እንዴት መጠበቅ እንደሚገባቸውና በሴትነታቸው ምክንያት ለሚደርስባቸው ጫናዎች (unwanted sexual advances) መውሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች ከቤተክርስቲያንኒቷ ቀኖና አኳያ በዚህ አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ትምህርት ወንጌል ቢሰጡ በአሁን ሰዓት እየደረሰ ላለው ችግር መፍትሄ ሊሰጥና የሰፈነውን ብዥታ ሊያጠራ ይችላል የሚል አመለካከት አለ።

 

የአንባቢያን አስተያየቶች

 1. Tito says:

  I fonot understand some people said that they stand for the church’s dignity and unity and their country but they donot know how Woyane playa at church and other religión .Should deferentiate Good From bad .They put Woyane’s coat .

 2. Tamene says:

  I have an answer for women who face unwanted and unsolicited sexual advance by wayward, criminal or mean-spirited priests they have to immediately contact appropriate law enforcement. These women should realize that they live in a country founded on rule of law. It’s not like Ethiopia where corrupt officials can do whatever they like,

 3. ከአ says:

  በመጀመርያ ቄስ አስተስርያ ፅጌ ማናቸው እራሳቸው ተወግዘው የተቀመጡ ቄስ ናቸው ሀሉንም እግዚአብሔር። ይጠይቀው እንጂ የራስን ደብቆ የስውን ሀጥያት አናውራ

 4. Workitu says:

  Thank you so much Kesis Asreaye! Please tell us what to do when women face sexual harassment by “kahenat”. This problem is a time bomb for the church. Both Synodoses are not paying attention to this extremely important issue. The church must do a preemptive actions to prevent sexual aggression by bad persists or Zemaris.

 5. yirgu says:

  Reta is correct 100%, business and Christianity are opposite.

 6. kt says:

  Reta is correct 100%, business and Christianity are opposite.

 7. Retta says:

  I have credible information that Zenebe is engaged in real estate and rental properties business in Ethiopia. I believe there’s nothing wrong in investing in Ethiopia. But doing business in earthly areas is off-limit for priests accord to EOTC. How can Zebene serve as priest and also engage in business endeavors? This will put him in a complete collision course with the teaching of the Bible.
  According to Matthew 6:24 it says,
  “No one can serve two masters. Either you will hate the one and love the other, or you will be devoted to the one and despise the other. You cannot serve both God and money”.
  In addition to this Zenebe and others who’re running businesses and at the same serve as preachers are corrupted by TPLF not to speak about the suffering of Ethiopians. This is a fact that can not be refuted!

 8. አሰለፈች says:

  እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ይህ የኢትዮጵያን ረቪው የሃሳብ መስጫ መድረክ የተዘጋጀው ኢትዮጵያውያን ሃሳባቸውን በነጻነት እንዲያንሸራሽሩ ነው። አቶ ጳውሎስ አዳነ እርስዎ ቀሲስ አስተርአየ ላይ የሚያቀርቡት ትችትና ነቀፌታ ካለዎት ማቅረብ ይገባዎታል። እኔ እስከማውቃቸው ድረስ ቀሲስ አስተርአየ የግምባር ሥጋ በመሆን በየቤተክርስቲያኑ የተሸጎጡትን አወናባጅና ቀጣፊ ካህናትን በማጋለጥና ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ በመታገል ላይ ይገኛሉ። ስለሆነም እርስዎ ለቤተክርስቲያኒቷ የሰሩትን ትውግባሮች ቢነግሩን የሚሻል ይመስለኛል

 9. Paulos says:

  Kesis Asteraye,

  What you have written is absolutely correct, but you are no better than the people whom you are accusing of this or that act. If you have done an honest self-assessment, you would know the answer. It is easy to point your index finger at others, but don’t forget that your three fingers are pointing towards you. Their crime may be different from yours, but you both share the same key word. Therefore, while I support the criticism against the people mentioned in your article, I encourage you to look into your self and make a genuine self-assessment of who you are and what your history is so that you can cleanse yourself as well, besides to helping others to look into themselves and correct their lives.

  Again, I don’t disagree with you on your criticism of the priests, so-called memheres or deacons that have inundated the church with various anti-Christ motives, including weyane politics, easy money, corruptions etc. What i am all saying is that you are no better than them as you have other big weaknesses or falling. You may not be seeking undue monetary benefit; you may not be promoting weyane politics and attempt to undermine the church in that way; and you may not be corrupt in the way the people you accuse are; however, you have many other major issues of your own. There is no need to delve into those details now, but it is suffice to say that your criticism of the wrong-doers at the EOT Church would be more powerful if you were a better person. Please see the log in your own eyes before positioning yourself as critic of others. There is a good old saying that goes “first attend to your own garden before trying to extend your hands to others.”

  Kind regards,
  Paulos Adane

 10. ታሪኩ says:

  ዘበነ ከመስፍን በዙ/ ወያኔ ጋር መስራቱ ከተረጋገጠ የደብሩ አባላት ምንድን ነው የሚጠብቁት? የስደተኞችን ቤተክርስቲያ ለአራጆችና አገር አጥፊዎች ተላልፎ መሰጠቱ እጅግ ያናድዳል።

 11. Fikerte says:

  What about your brother Amare?
  He is the same shrewd person. But now he is fired. Ye Shabiya barriyawoch temenxrew mebarer
  Alebachew. Haymanotachinen
  iyeberezubn neaw.

 12. Guttu says:

  Asteraye ibakh tew ante bequmh
  yetemetah neh.
  Isqi kura teshekmh be adebabay Alahhu AKBER yemtil neh
  .
  Tegbarh inde meqh
  yexefa neaw. kkkkk

 13. መስፍን በዙና ዶ/ር ዘበነ ለማ አንድነታቸውን አሳዩ says:

  ትናንት ለሊት አንድ ጉድ አየሁ፣ አይኔንም ማመን ተጠራጥሬ ነበር። የወያኔው ወሬ ለቃቃሚና ልክስክሱ መስፍን በዙ በደብረ ገነት ቤ/ክ ውስጥ ተገኝቶ ቪዲዮ ካሜራውን ይዞ ለገና በአል የተገኘውውን አስቀዳሽ ሲቀርጽ ነበር። መስፍን በዙ ሳይፈቀድለት ይህንን ለማድረግ ስለማይችል ዶ/ር መምህር ዘበነ ለማ ከወያኔ ጋር ያለውን የስውር ቁርኝትና የሚያካሂዳቸውን የግል ቢዝነሶች ምክንያት በወያኔ እጁ በመጠምዘዙ ምክንያይ አሁን በይፋ እያደረገው በመሄድ ላይ መሆኑ ማረጋገጫና ለሚቃወሙም አንዳንድ ምእመናን “ምን ታመጣላችሁ” አይነት ምላሽ ይመስለኛል። ለመስፍን በዙ ፍቅድ መስጠት ማለት ለደብሩ ምእመናንን በተለይም ለተቃዋሚዎቹ ለነዶክተር ገብርዬ አይነቶቹ ትልቅ ውርደት ነው።

 14. Anonymous says:

  Look at his face . Is he not look
  like LEPROSY . KKKKKK
  Not only his face his deeds too.
  He is member of the ISIS.
  Sat Allah Akber ! with your
  brother Amare Aradaw .

 15. Anonymous says:

  ለክርስትና እምነት ተከታዮች … እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!!
  http://niletube.net/?a=vVid&vidId=1056&vidCId=8

Leave a Reply

Please answer this math question before submitting your comment: