እስኪ ሰከን እንበል – #የመደማመጥ_ቀናነት ቡድን።

እስኪ ሰከን እንበል ———–#የመደማመጥ_ቀናነት ቡድን። ————- ግን እንደኛ አገርና ህዝብ አስፈሪ የህልውና አደጋ ላይ ያለ ይኖራል? እንደኛስ መላቅጡ የጠፋበት ህዝብ ይኖራል። 100 ሚሊዮን ህዝብ፣ 100 ቁዋንቁዋ፣100 የፖለቲካ ድርጅት ፣ 100 ብሄረሰብ ፤ በኢትዮጵያ የአየር ፀባይ፣ በኢትዮጵያ መልክአ ምድር፣ በኛ ጎረቤቶች፣ በኛ መንግስት፣ በኛ ድርቅና እና ራስ ወዳድነት! እስኪ አስቡት ጎበዝ ሳት ብሎን ጦርነት ውስጥ ብንገባ ምን ሊፈጠር እንደሚችል።

ተመድ፣ አአድ ገሌ መሌ ጭው ባለ ሜዳ አንድ ቁዋንዋ አንድ ሀይማኖት ላለው አገር እንኳ ምንም እንዳልፈየደ እያየን! አንድስ የሚያክል ጠላት አስቀምጠን የጠላት ያለህ፣ ጠላት አውርድ የምንል ምን ክነቶን ይሆን። ባለፉት አስርታት የወረደብን መአት እንኳን ለኛ ለአለም ትምህርት አይሆንምን? የ25 እና 40 አመት ሰቆቃና ስቃይ ያላስተማረን ምን ሊያስተምረን ነው? ምን ስንሆን ይሆን ባንክሮ ናማሰብ ማስተዋል የምንጀምረው? ወያኔን እንላለን እንጂ እኛው እራሳችን ነን ሀገራችንን በልተን እየጨረስናት ያለው። ወያኔስ ኢትዮጲያን ማጥፋት ስራው ነው። የኛስ ምን ይሉታል።

ወያኔን በርግጥ እንጠላለን። ግን ወያኔን የምንጠላበትን ድርጊት ላለማድረጋችን ምን ማረጋገጫ አለን? በየርከኑ ስንነሰነስና ስንበጣጠስ ስንት ትንንሽ ልንሆን እንደሆነ አስተውለነዋል? ተበጣጥሰን ተሰነጣጥቀንስ አማን ውለን አማን እንደማናድርስ ነጋሪ ያስፈልገናል? እኛ እኮ እስከየሩሳሌም ግዛታችን ነው ብለው የሚያልሙ አባቶች ልጆች ነን። እኛ እኮ ለአለም ጥቁሮች ሁሉ የነፃነትን ቀንዲል የለኮሱ አርበኞች ልጆች ነን። ሌሎች ከኛ ሊማሩ እንጂ ይሳለቁ ዘንድ እንዴት እንፍቀድ! አረ ተዉ ጎበዝ! አረ በባንዲራው! እኛ ስንጎማመድ እኮ የምትጎመደው ይች ምስኪን አገር ነች። ይረከቡት የሚያጡት እኮ ልጆቻችን ናቸው።

አረ በልጆቻችን! የኛ መጠላለፍ የጠላታችንን ክንድ እያፈረጠመው ነውና ወደ ልቦናችን እንመለስ። ሰከን፣ በሰል እንበል። ቅንነት ካለ ሁሉም ይቻላል። ወደ ጎን የሰበቅነውን ሰይፍ ወደ ጠላት እንቀስረው። ለህዝባችን ስንል ትንሽ ዝቅ እንበል። ዝቅ ያለን ሁሉ አንድየ ከፍ ያደርገዋል። ይሄንን የማህበራዊ መገናኛ አሳፋሪ ጦርነት ዛሬውኑ አቁመን ትግላችን ላይ እናተኩር። አገራችን አታልቅስብን። ወገናችን አይዘንብን፣ ልጆቻችን አይፈሩብን። ጠላታችንም አይሳለቅብን። የኢትዮጵያ መፃኢ እጣ ፈንታ በእጃችን ነው። ቅን ከሆንን እግዚአብሄርም ያግዘናል።

#የመደማመጥ_ቀናነት ቡድን።

#የመደማመጥ_ቀናነት ቡድን።

የአንባቢያን አስተያየቶች

 1. Esubalew says:

  I Love ETHIOPA !
  Long live EPRDF !

 2. Mola says:

  Long live president Essayias Afewerk ! You do good job for
  Your beloved country Ethiopia! Ezaw yazilign yihin
  Kehadina hager shiach ye Arab
  telalaki hodam hula !Sebsibeh
  dingay aslekimilign !

 3. Anonymous says:

  Yehunie Belay SEKEN BEL ሰከን በል! NEW Music 2016

 4. ቅዱስ ኢትዮጵያ says:

  To all Agames / Woyanes /TPLF thugs and those masquerading with crocodile tears trolling the web: ውጥረትን ለማርገብ ለቀረበው ምክር፤ ሊቀመንበር አቶ ኤሊያስ ክፍሌ ሆነው ተሹመዋል።

  1/የአርበኞች ከግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመሻር እቶ ሄኖክ የሺጥላን ሊቀመንበር ሆኖ ተሾሞአል።

  2/አቶ ደምስ በለጠ የሥራ መደራረብ ያለባቸው መሆኑን ብንረዳም ከስድስት አመት በላይ በእሳትና በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ በጽሁፍ ያቀረቡት ተቃ ውሞ ውጤት ባለማምጣቱ ባላቸው ሥ ራ ላይ የኢሳት ሥራአስኪያጅ ሆነው እንዲሰሩ ተሹመዋል።

  3/ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሱት ድርጅቶች በአንድ ቦርድ እንዲጠቃለሉ ተወስኖአል፣የቦርዱም ሊቀመንበር አቶ ኤሊያስ ክፍሌ ሆነው ተሹመዋል። ለምርጫው የተውሰደ መስፈርት፣

  1- አቶ ኤሊያስ ክፍሌና አቶ ደምስ በለጠ ቀደም ሲል ሰሜን ዘምተው የተመለሱ በመሆናቸው፣
  2- አቶ ሄኖክ የሺጥላ የአርበኞች ግንቦት 7 አባል በመሆን የአንድ አመት ከ6 ወር ለምድ ያካበቱ በመሆኑና ሊሄዱም እንደነበረ የተናገሩትን መሰረት በማድረግ ነው።

  ተመራጮች አሁን እንቅልፍ እንደሚወስዳቸው የምርጫ ቦርዱ እምነት ነው። የጥልቅ ተሀድሶ ምርጫ ቦርድ።

  Ato Elias Kifle
  የER ሥራአስኪያጅ

 5. Isubalw says:

  To be honest
  Ginbot 7 is not an Ethiopian Movement. What people should know is Berhanu has no right to say anything about Ethiopia without the consent of Colonel Fitsum.
  That is why we said do not expect anything from the Shabia puppets Gim 7 leadership.ye Lencho condomch.

 6. Awen says:

  Bezariew qen Agerie adis be ecadf, srgut g.slasie besatenaw grum genbi litegeber michil hasab aqrbewalna tegabzachuhal.

 7. ካራማራ ሶማሌ says:

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ??????????????????????????????????????

 8. Alemash says:

  Ginbot 7 Dollar amlakiw ahun yachi
  ye genzb minch medrkwa atqerm .
  beyesbsebaw inema indmisebsebu
  inayalen bexam asafari . Woyane
  inlalen inji ke megarejaw bestejerba
  yalutn inawqachewaln . Berhanue le
  Amaraw yalew nqet yetayw ye Amarsn zern ke chefchafu
  nefse gedayoch ke ine Lencho Leta gar ijna guant
  mehonu ande masaya neaw.

 9. Jil neh says:

  Tagel tru bilhal
  mogna woreqet yasyazutn ayleq
  new negeru
  ya jil qidu etiopia mil bequm neger lay mejajal yaqum.
  Mirx jeginochn aynekaka.

 10. tagel says:

  ምናለ አንተ ሰው አይበቃም እንዴ ፡ መተው አታውቅም ።

  • No semi says:

   Yebelachiw yastefatal esum belay belay yagorsatal alu.
   Eskahun yetefelefelew beza eyaln beyeqenu adadis drjit yifelefelal.
   Demo yemedemamex qenanet budn mibal mexa.
   Leziawm sebeka aylut limena ma mann lisema

 11. ተሾመ says:

  መጠራረብና በቁም ንገር ወቅት እንደ ሕጻን እቃ አቃ መጫውት በሀገርና በውገን ላይ ማፌዝ ስለ እሚሆን እውንትም ስከን እንበል ።

 12. tagel says:

  ቅዱስ ኢትዮጵያ ማለቴ ነው ፡

 13. tagel says:

  አፍና ደጃፍ እኩል ይከፈታል አሉ ፡ አንድነትና ጎጠኝነትን ምን ያገናኛቸዋል ፡ ይኸውና ከላይ የዘባረከ ጎሰኝነት ነው ።

 14. ቅዱስ ኢትዮጵያ says:

  ውጥረትን ለማርገብ ለቀረበው ምክር፤ ሊቀመንበር አቶ ኤሊያስ ክፍሌ ሆነው ተሹመዋል።

  1/የአርበኞች ከግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመሻር እቶ ሄኖክ የሺጥላን ሊቀመንበር ሆኖ ተሾሞአል።

  2/አቶ ደምስ በለጠ የሥራ መደራረብ ያለባቸው መሆኑን ብንረዳም ከስድስት አመት በላይ በእሳትና በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ በጽሁፍ ያቀረቡት ተቃ ውሞ ውጤት ባለማምጣቱ ባላቸው ሥ ራ ላይ የኢሳት ሥራአስኪያጅ ሆነው እንዲሰሩ ተሹመዋል።

  3/ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሱት ድርጅቶች በአንድ ቦርድ እንዲጠቃለሉ ተወስኖአል፣የቦርዱም ሊቀመንበር አቶ ኤሊያስ ክፍሌ ሆነው ተሹመዋል። ለምርጫው የተውሰደ መስፈርት፣

  1- አቶ ኤሊያስ ክፍሌና አቶ ደምስ በለጠ ቀደም ሲል ሰሜን ዘምተው የተመለሱ በመሆናቸው፣
  2- አቶ ሄኖክ የሺጥላ የአርበኞች ግንቦት 7 አባል በመሆን የአንድ አመት ከ6 ወር ለምድ ያካበቱ በመሆኑና ሊሄዱም እንደነበረ የተናገሩትን መሰረት በማድረግ ነው።

  ተመራጮች አሁን እንቅልፍ እንደሚወስዳቸው የምርጫ ቦርዱ እምነት ነው። የጥልቅ ተሀድሶ ምርጫ ቦርድ።

  Ato Elias Kiflr
  የER ሥራአስኪያጅ

Leave a Reply

Please answer this math question before submitting your comment: