አጫጭር ወሬዎች: የአውሮፓ ጋዜጦች የዝውውርና ሌሎች አዝናኝና አጓጊ ወሬዎች

አጫጭር ወሬዎች: የአውሮፓ ጋዜጦች የዝውውርና ሌሎች አዝናኝና አጓጊ ወሬዎች

በሚኪያስ በ. ወርዶፋ

በቅርቡ በጠብታ ዶክተሮች (Drip Doctors) የህክምና ክትትል የተደረገለትና በስፔኑ ሲቪላ በውሰት የሚገኘው የሲቲው አማካኝ ሳሚር ናስሪ አበረታች መድሀኒት ከመጠቀም ጋር በተያያዘ የአለም ፀረ አደንዛዥ ኤጀንሲ (World Anti-Doping Agency) ህግን ተላልፎ ከተገኘ የአራት አመታት እገዳ እንደሚጠብቀው ታወቀ። (ዴይሊ ሜይል)

ሮቤርቶ ፈርሚንሆ በሊቨርፑል ቤት ያለውን ህይወቱን እንደሚወደውና ብዙ አመታትን በሊቨርፑል ቤት መቆየት እንደሚፈልግ አስታወቀ። (ሊቨርፑል ኤኮ)

የአትሌቲኮ ማድሪዱ አጥቂ አንቶን ግሪዝማን እንደ ብሄራዊ ቡድን አጋሩ ፓል ፓግባ የ 220,000 ፓውንድ ሳምንታዊ ደሞዝ ከዩናይትድ ቀርቦለታል። (ዘ ሰን)

ዌስትሀሞች በሰንደርላንዱን አጥቂ ጄርሜን ዴፎ ዙሪያ ክለቡን ለማማለልና ተጫዋቹን በእጃቸው ለማስገባት በማሰብ ከዚህ ቀደም ያቀረቡትን የዝውውር ሂሳብ እጥፋ በማድረግ 13 ሚሊዮን ፓውንድ ለተጫዋቹ አቅርበዋል። (ዴይሊ ኤክስፕረስ)

የጁቬንቱሱ የ 35 አመት ግራ ተከላካይ ፓትሪስ ኤቭራ ወደ እንግሊዝ ለመመለስ ከዌስትሀምና ከቀድሞ ክለቡ ዩናይትድ ጋር በመነጋገር ላይ ይገኛል። (ካልቺዮ መርካቶ)
ዩናይትድ ቪክቶር ሊንድሎፍን ከቤኔፊካ የማስፈረም እቅዱ ከከሸፈ በኃላ ለሮማው የ 25 አመት ተከላካይ ኮስታስ ማኖላስ የ 32.5 ሚሊዮን ፓውንድ ጥያቄ አቅርቧል። (ዘ ሰን)

ሜምፈስ ዲፔይን እየፈለጉ ያሉት ሮማና ኒስ የተጫዋቹን 20 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብና 90,000 ሺህ ፓውንድ ሳምንታዊ ደሞዝ መክፈል ስለተቸገሩ ተጫዋቹ እስከ አመቱ መጨረሻ በዩናይትድ ሊቆይ ይችላል። (ዴይሊ ቴሌግራፍ)

ሜሶት ኦዚል በያዘው ጉንፋን ምክንያት በአርሰናል የህክምና አባላት ምርመራ ሊደረግለት ማክሰኞ ወደ ለንደን ኮለኒ እንደሚያመራ አርሰን ቬንገር ተናገሩ። (ለንደን ኢቭኒንግ ኒውስ)

ዌስትሀሞች የሴልቲኩን አጥቂ ሙሳ ዴምቤሌን በዝውውር እቅዳቸው ውስጥ ያስገቡ ሲሆን ለ 20 አመቱ ተጫዋችም 20 ሚሊዮን ፓውንድ ለማቅረብ ፍቃደኛ ሆነዋል። (ጎል)
ነገር ግን መዶሻዎቹ ተጫዋቹን ለማስፈረም እስከ 30 ሚሊዮን ፓውንድ ማቅረብ አለባቸው። (ዴይሊ ሜይል)

ቼልሲ የ 20 አመቱን የአትላንታ አጥቂ ፍራንክ ኬሲን ለማስፈረም በንግግር ላይ ቢሆንም ዝውውሩን ለማጠናቀቅ እስከ ክረምት መቆየት ሊጠበቅበት ይችላል። (ጋርዲያን)

የቻይና መንግስት ምክንያታዊ ያልሆኑ የክለቦች ወጪ እንዲቆም፣ በትልልቅ ብር የሚደረጉ ዝውውሮች መላ እንዲበጅላቸው እንዲሁም ለተጫዋቾች የሚደረጉ ከፍተኛ ክፍያዎች ጣሪያ እንዲኖራቸው የሚያስገድድ ትዕዛዝ አወጣ። (ዴይሊ ቴሌግራፍ)

አርሰን ቬንገር የቶሪኖውን አጥቂ አንድሬ ቤሎቲን ለማስፈረም ፈልገዋል። ነገር ግን የተለጠፈበት የ 50 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ አስፈርቷቸዋል። (ዘ ሰን)
የዩናይትዱ ሶስተኛ ተመራጭ በረኛ ሳም ጆንስቶን በስቶንቪላን እስከ አመቱ መጨረሻ ለመቆየት በውሰት ውል ወደ ቪላ ፓርክ አመራ። (ማንችስተር ኢቭኒንግ ኒውስ)

የስዋንሲ አሰልጣኝ ቡድን አባል የነበሩት አለን ኩርቲስ ከዚህ በኃላ የቡድኑ አካል እንዳልሆኑ የሚገልፅ መሰናበቻ በስልክ የፅሁፍ መልዕክት እንደደረሳቸው ይፋ ሆነ። (ዴይሊ ሜይል)

የማድሪዱ ጀምስ ሮድሪጌዝ የክለቡ ቆይታ ገና ውሳኔ ባላገኘበት በዚህ ወቅት ጣሊያናዊው ጋዜጠኛ ሚና ሩዝኪ ተጫዋቹ ወደ ዩናይትድ ሊያመራ እንደሚችል ተናገረ። (ቢቢሲ ራዲዮ 5 ላይቭ)

የቼልሲው የ 28 አመት አጥቂ ዲያጎ ኮስታ ስለ እንግሊዝ ዳኞች ያለውን እውነተኛ አስተያየት ቢሰጥ አራት ወይም አምስት ጨዋታዎች ሊቀጣ እንደሚችል ተናገረ። (ኦንዳ ሴሮ)

ቼልሲ በስታምፎርድ ብሪጅ አካባቢ አዲስ 60,000 ተመልካች መያዝ የሚችል ስታዲየም መስራት የሚያስችላቸው ፈቃድ ለማግኘት በሂደት ላይ ናቸው። (ዴይሊ ቴሌግራፍ)

የጀርመኑ ባየር ሊቨርኩሰን የስፓርት ዳይሬክተር በአጥቂያቸው ጃቪየር ኸርናንዴዝ ዙሪያ ክለባቸው ከቼልሲ ምንም አይነት የዝውውር ጥያቄ እንዳልቀረበለት ተናገሩ። (ቶክ ስፓርት)
ሊቨርፑል የ 23 አመቱን ተከላካይ ቲያጎ ኢሎሪ ለሬዲንግ በ 3.75 ሚሊዮን ፓውንድ ሊሸጠው ነው። (ሊቨርፑል ኤኮ)

የስላቪያን ቢሊች የዌስትሀም ስራ ሰዎች እንደሚያስቡት ዋስትና ያለው እንዳልሆነ ቶኒ ኢቫንስ የተሰኘው የስፓርት ጋዜጠኛ ተናገረ። (ቢቢሲ ራዲዮ 5 ላይቭ)

በመጨረሻም …

በክለቡ መልቀቅ እንደሚችል የተነገረው ሞርጋን ሽንደርሊን በካንትሪ ፓርክ አካባቢ ብቻውን ልምምድ ሲሰራ የሚያሳይ የቪዲዮ ምስል ለቀቀ። (ዴይሊ ስታር)

ትውልደ ለንደናዊ የሆነው የኤልኤ ሌከር ክለብ ትንሹ አጥቂ ሉል ዴንግ ቢሊየነር ከሆነ የመጀመሪያ ስራው የእንግሊዙን ክሪስታል ፓላስ ክለብ መግዛትእንደሆነ ተናገረ። (ዴይሊ ኤክስፕረስ)

አጫጭር ወሬዎች: የአርብ አመሻሽ የአውሮፓ ጋዜጦች የዝውውርና ሌሎች አዝናኝና አጓጊ ወሬዎች■ Subscribe to mereja.com's email newsletter. ⇒ CLICK HERE እዚህ ላይ ይጫኑ ⇐

► Post your comment below
የአንባቢያን አስተያየቶች

Leave a Reply

Please answer this math question before submitting your comment: