አርሰን ዌንገር በቁጭት ውስጥ

አርሰን ዌንገር በቁጭት ውስጥ

የመሀመድ  ኤልነኒ ወደ አፍሪካ ዋንጫ መጓዝ ፣ የ ፍራንሲስ ኮክለን እና የሳንቲ ካርዞላ ጉዳት እንዲሁም የ አሮን ራምሴ አቋም መዋዠቅ አሰልጣኝ አርሰን ዌንገር በወሰኑት ውሳኔ ላይ ቁጭት እንዲያድርባቸው እንዳደረገ ገልፀዋል፡፡ 

የመሀል ሜዳው መሳሳቱን ተከትሎ ጃክ ዊልሻየርን በውሰት ለመስጠት መወሰናቸው እንደሚቆጫቸው ሳይሸሽጉ ገልፀዋል፡፡ ስለዊል ሻየር ሲጠየቁ በቁጭት ” አሁን ልጠቀምበት እችል ነበር ”  አርሰን ዌንገር ቀጥለውም ” አሁንም  ተጫዋቹን በዉሰት ለመስጠት መወሰኔ ልክ እንደሆነ አምናለሁ  ግን አንድ ቀን ልፈልገው እንደምችል አውቅ ነበር ”

የ 25 ዓመቱ ጃክ ዊልሻየር በቦርንማውዝ የተሳካ የሚባል ግዜን እያሳለፈ ይገኛል ፡፡ ባልተለመደ በሚባል መልኩ ተከታታይ ጨዋታዎችን መጫወት መቻሉ ለአርሰናል ጥሩ የተስፍ ጭላንጭልን እያሳየ ይገኛል በተለይም የ 32 ዓመቱ ሳንቲ ካርዞላ ጉዳት እዲሁም የ እድሜ መግፍት አርሰናል ተጫዋቹን ለመተካት ብዙም እርቆ እንዳይሄድ የዊልሻየር አቋም ጠቋሚ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ሆኖም ሰሞኑን እየወጡ ያሉ ዘገባዎች እንደገለፁት አርሰናሎች ውላቸው በዚህ ዓመት ለሚጠናቀቀው ለሁለቱ የ 32 ዓመት ተጫዋቾች  ለሳንቲ ካርዞላ እና ፔር ሜርቲሳከር የተጨማሪ የአንድ ዓመት ኮንትራት ለማቅረብ መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል ፡፡

የአንባቢያን አስተያየቶች

  1. Anonymous says:

    2016 በስፖርቱ ዓለም – አበይት ክስተቶች – 2016 in Sports – Main Events – DW (Dec 26, 2016)

  2. Desalegn Assfa says:

    Good by Wenger

  3. mberequ says:

    are u serious man? what has to do British football history to Ethiopian readers? I have a strong feeling u could be one of woyaneas stooge who is aiming to divert the discussion to the wrong end.

Leave a Reply

Please answer this math question before submitting your comment: