በአዲስ አበባ 5 ሰዎች በጎርፍ ተወስደዋል – የሦስቱ አስክሬን አልተገኘም

ሰሞኑን በአዲስ አበባ 5 ሰዎች በጎርፍ ተወስደዋል
– የ ሦስቱ አስክሬን አልተገኘም ተብሏል
• ‹‹ከ18 አካባቢዎች ነዋሪዎችን ከጎርፍ አደጋ ማሸሽ ያስፈልጋል››

በአዲስ አበባ ሰሞኑን የጣለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ 5 ሰዎች ተወስደው ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በክረምቱ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ናቸው የተባሉ አካባቢዎች በጥናት መለየታቸው ታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ እሣትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ሰሞኑን በአዲስ አበባ የጣለው ዝናብ ያስከተላቸውን አደጋዎች በተመለከተ ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ በሠጡት ማብራሪያ፤ ሰኔ 25 እና 26 ቀን 2009 ዓ.ም በመዲናዋ የጣለው ሃይለኛ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ፤ የ5 ሰዎች ህይወት መቅጠፉንና የ3ቱ አስክሬን አለመገኘቱን አስታውቀዋል፡፡

አንደኛው የጎርፍ አደጋ የደረሰው ንፋስ ስልክ ክ/ከተማ፣ ሃና ማሪያም አካባቢ ሲሆን 4 ሰዎች በጎርፍ ተወስደው ሲሞቱ፣ የሁለቱ አስክሬን ብቻ ሊገኝ ችሏል፡፡ የሁለቱን አስክሬን የማፈላለግ ስራ መቀጠሉንም አቶ ንጋቱ አስረድተዋል፡፡ ሌላኛው የጎርፍ አደጋ ቦሌ፣ ወረዳ 7 ጃክሮስ አካባቢ የተከሰተ ሲሆን አንዲት ሴት በጎርፉ መወሰዷንና አስክሬኑም አለመገኘቱ ተገልጿል፡፡
ከጎርፍ ጋር ተያይዞ በንብረት ላይ የደረሰው አደጋ እጅግ በርካታ መሆኑን የገለፁት አቶ ንጋቱ፤ በተደጋጋሚም በንብረት ላይ አደጋው እየደረሰ ነው ብለዋል፡፡
በክረምት ለጎርፍ ተጋላጭ ይሆናሉ ተብለው የታሠቡ አካባቢዎች ላይ ኮሚሽኑ ጥናት ማካሄዱን የጠቆሙት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው፤ አካባቢዎችን ለአደጋው ባላቸው የተጋላጭነት መጠን በሶስት መክፈሉን ያስረዳሉ፡፡
ጥናቱ 18 የከተማዋ አካባቢዎች በጣም ከፍተኛ በሆነ ደረጃ ተጋላጭ በመሆናቸው ነዋሪዎችን ከአካባቢዎቹ የማሸሽና ወደተለዋጭ ቦታ መውሰድ የሚያስፈልጋቸው መሆኑ ተረጋግጧል ያሉት ባለሙያው፤ 54 አካባቢዎች ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸው፣ 34 አካባቢዎች ደግሞ በመካከለኛ ደረጃ ተጋላጭ መሆናቸው በጥናቱ ተጠቁሟል ብለዋል፡፡
በጥናቱን በመመርኮዝ የአደጋ መከላከሉን ተግባር እንዲያከናውን በከተማ ደረጃ ለተቋቋመውና በየወረዳው ንዑስ ኮሚቴዎች ላደራጀው የጎርፍ አስወጋጅ ቢሮ መቅረቡን የጠቀሱት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው፤ ቢሮው በዚሁ መሰረት በተለይ አስቸኳይ መፍትሄ ያስፈልጋቸዋል በተባሉት 18 አካባቢዎች ላይ መፍትሄ ያበጃል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
የአካባቢዎቹን ስም መጥቀሡ በነዋሪዎች ላይ የስነ ልቦና ጫና ሊያሣርፍ ስለሚችል ከመግለፅ የተቆጠቡት አቶ ንጋቱ፤ የጎርፍ አስወጋጅ ቢሮ ዝርዝሩ ተሠጥቶታል፤ አስፈላጊውን ተግባርም ያከናውናል ብለዋል፡፡
የከተማዋን ጎርፍ ጉዳይ መላ ያበጃል ተብሎ የሚጠበቀው የጎርፍ አስወጋጅ ቢሮ ሃላፊን በስልክ አግኝተን ስለጉዳዩ ለማነጋገር ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት ስልኩ ባለመነሳቱ ሊሣካልን አልቻለም፡፡
የክረምቱ ዝናብ አዲስ አበባን ጨምሮ በአብዛኛው የሃገሪቱ አካባቢዎች መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ሊሆን እንደሚችል መገመቱን ብሄራዊ ሜትሮሎጂ በድረ ገፁ ያመለከተ ሲሆን አብዛኛውን የሃገሪቱ አካባቢዎችም ከነሐሴ አጋማሽ በኋላ ቀድሞ ሊወጣ ይችላል ተብሏል፡፡

#አዲስ አድማስ ጋዜጣ

የአንባቢያን አስተያየቶች

 1. Addus says:

  How in earth can this happen in a so called city. Why there is no any drainage system? Shame this to be called a city. Shame.

 2. Anonymous says:

  as far as the golden people okay who cares about immigrant gallo

 3. ጋሜ says:

  አይ ወግ ሲዳሩ ማልቀስ ይልሃል ይሄ ነው ማነው አጥኝው? ወያኔ ጤፍ ምን እንደሆነ የማያውቁ እንሰሶች ስለ ጎርፍ ሊያጠኑ እባችሁ አትቀልዱ

 4. Stoned Peter says:

  I wonder if the water flood drain took the three missing bodies to underground inside the mice and maybe other creatures too infested sewer system of Addis Ababa?

 5. Abel says:

  Hummm, they are now studying the case?

  The flood prone areas in Addis have been identified long ago and the city has been subjected to repetitive and massive flooding. The question is did the city develope flood zone map? And did they delineate the hazardous areas and incorporate risk management in the master plan?

  New buildings and road ways in flood-prone areas are not only exposed to devastating flood hazards but can also make the situation worse by blocking the natural flow and artificially channeling the flow to certain areas. The poor usually ends up being the first victim.

Leave a Reply

Please answer this math question before submitting your comment: