መንግስት ከህወሓት የንግድ ድርጅቶች የመኪና ግዢ ሊፈጽም ነው

መንግስት ከህወሓት የንግድ ድርጅቶች የመኪና ግዢ ሊፈጽም ነው

BBN – መንግስት ከህወሓት የንግድ ድርጅቶች የመኪና ግዢ ሊፈጽም መሆኑ ታወቀ፡፡ ሰሞኑን በስራ ላይ የዋለው የመንግስት መመርያ አስቀድሞ የነበረውን የመኪና ግዥ ስርዓት አፍርሶ በአዲስ ተክቶታል፡፡ በአዲሱ የመንግስት መኪና መግዣ ህግ እና ደንብ ስርዓት መሰረት፣ ከዚህ በኋላ መኪና መገዛት ያለበት ከውጭ ሀገር ሳይሆን ከሀገር ውስጥ እንዲሆን ተደንግጓል፡፡ አሁን ባለው የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ መኪና የመገጣጠም እና የማምረት ኢንዱስትሪውን ተቆጣጥረው የያዙት የህወሓት የንግድ ድርጅቶች በመሆናቸው፣ መንግስት መኪና ሊገዛ የሚችለው የግድታ ከህወሓት ድርጅቶች መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
ኤፈርት የሚባለው የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የንግድ ድርጅት በውስጡ በርካታ የንግድ ድርጅቶችን የያዘ ሲሆን፣ የመኪና ማምረቻ እና መገጣጠሚያም አንደኛው የድርጅቱ የንግድ አካል ነው፡፡ መስፍን ኢንደስትሪያል የሚባለው የህወሓት ድርጅት መኪና በማምረት እና በመገጣጠም ስራ ላይ የተሰማራ ሲሆን፣ በመንግስት በኩል የሚደረጉት የመኪና ግዥ ውሎች በአብዛኛው ከዚህ ድርጅት ጋር የሚፈጸሙ ናቸው፡፡ ህወሓት የግል መኪና አምራች እና መገጣጠሚያ ድርጅቶችን አስቀድሞ ከገበያ በማስወጣቱ፣ ኢንዱስትሪውን ለብቻው እንዲቆጣጠረው አስችሎታል፡፡
ከመስፍን ኢንዱስትሪያል ቀጥሎ በመኪና መገጣጠም እና ማምረት ዘርፍ በሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የገበያ ድርሻ ያለው፣ የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ነው፡፡ ኮርፖሬሽኑ በመከላከያ ሚኒስቴር ስር ይቋቋም እንጂ በጠቅላላ ኃላፊዎቹ የህወሓት ጄኔራሎች ሲሆኑ፣ ከድርጅቱ የሚገኘውም ገቢ በዘረፋ መልክ ወደ ህወሓት ባለስልጣናት ኪስ እንደሚገባ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከዚህ በኋላ መኪና መግዛት ያለባቸው ከሀገር ውስጥ እንዲሆን በሚያዘው ህግ መሰረት፣ አብዛኞቹ ግዢዎች ከሁለቱ የህወሓት ድርጅቶች እንዲፈጸሙ እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የህወሓት የንግድ ድርጅቶች፣ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ በጅምር ላይ የነበሩ የግል የመኪና መገጣጠሚያ ድርጅቶችን የንግድ ፈጠራ ሀሳብ በመስረቅ ድርጅቶቹን በኃይል ከገበያ አስወጥተዋቸዋል፡፡

የአንባቢያን አስተያየቶች

 1. አዚዛ ነኝ says:

  ያልነው እየደረስ ነው ! ወያኔ ቁንጮ ቤተስቦች እየሾሎኩ ነው ! ትግሬዎች እግራቸውን እየነቀሉ ነው ! ጠላት እግሩን ሲነቅል በማዋከብ እያከታተሉ ማጥቃት የድሉን ጊዜ ስለሚያሳጥር: በአዲሱ አመት በግራና ቀኝ ሲወጠሩ: በስራ በታና በሞያችን በያለንበት የመሀል አገሩ በቅኔውና በጥበቡ: ወጣቶች በማግለል የትግል ዘዴን በመጠቀም በት/ ቤት: በመዝናኛ ቦታዎች: በባስና በታኪስና በአጠቃላይ በህዝብ መገልገያዎች: ፊት የመንሳትና የማግለል ትግላችን የምናጠናክርበት ዘመን ይሁንልን !!

 2. ወደ ውጭ ሸሹ says:

  የውጩን ንግድ በሞኖፖል ይዘውት የነበሩት አስራ ሁለቱ የአባይ ጸሃዬ ልጆች ወደ ውጭ እንዲሸሹ ተደረገ:: ጤፍ፣ በርበሬ፤ እንጀራ፣ ወዘተ ወደ አውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ የሚላኩ የእርሻ እና የባልትና ውጤቶች በሙሉ የተያዙት በአባይ ጸሃይ ልጆች መሆኑንም ካገኘነው መረጃ ለመረዳት ችለናል።

  September 7, 2017 -.
  አባይ ጸሃዬ

  EMF- በሙስና ወንጀል ውስጥ እጃቸው አለበት እየተባለ የሚነገረው አቶ አባይ ጸሃዬ ልጆቻቸውን በሙሉ ወደ ውጭ እንዲሸሹ ማድረጋቸውን ከታማኝ ምንጮች የተገኘ መረጃ ለማረጋገጥ ችለናል።

  የውጩን ንግድ በሞኖፖል ይዘውት የነበሩት የአባይ ልጆች በአሁን ሰዓት በአሜሪካን ሃገር ውስጥ እንደሚገኙ የተጠቆመ ሲሆን ከሚኖሩበት ስፍራ ሰው በቀላሉ እንዳያጘኛቸው ማህበራዊ ገጾቻቸውን እና ስልኮቻቸውን አጥፍተዋል።

  የአስራ ሁለት ልጆች አባት የሆኑት አቶ አባይ ጸሃዬ ከኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን 77 ቢሊየን ብር በማባከን የሚጠቀሱ ሙሰኛ ቢሆኑም እስካሁን ተይዘው ሊጠየቁ ግን አልተቻለም። አቶ አባይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በፌደራል ጉዳዮች እና በስኳር ኮርፖሬሽን ውስጥ በሃላፊነት ሲሰሩ የዘረፉትን የሀዝብ እና የሃገር ገንዘብ በልጆቻቸው እና በሚስታቸው ስም በህገወጥ ንግድ ላይ ማዋላቸውንም የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

  ከአባይ ጸሃዬ ልጆች ውስጥ ትንሽዋ፣ ቤቢ የተባለችው ልጃቸው በአዲስ አበባ ብቻ 7 ሕንጻዎች ያላት ሲሆን፤ በዱባይ እና በአሜሪካም ትላልቅ ህንጻዎች እና የንግድ ተቋማት እንዳላት ምንጮቹ ገልጸዋል። ጤፍ፣ በርበሬ፤ እንጀራ፣ ወዘተ ወደ አውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ የሚላኩ የእርሻ እና የባልትና ውጤቶች በሙሉ የተያዙት በአባይ ጸሃይ ልጆች መሆኑንም ካገኘነው መረጃ ለመረዳት ችለናል።

  ባለቤታቸው ሳሌም ከበደ ከወር በፊት በሙስና ተጠርጥራ መታሰርዋ የሚታወስ ሲሆን በእስር ላይ የሚገኙ ባለሀብቶችም ከአባይ ጸሃዬ ጋር ስላላችሁ የዝርፍያ ግንኙነት ለፖሊስ እና ፍርድ ቤቶች እየተናገሩ ይገኛሉ።

  የኦሮሞን ሕዝብ እንደመሥአለን እያሉ ሲዝቱ የነበሩት እኚህ ሰው ባለበታቸው በታሰሩ ግዜ የተለያዩ ጀኔራሎች ዘንድ በመደወል “አድኑኝ” እያሉ ሲማጸኑ እንደነበር ውስጥ አዋቂዎች ተናግረዋል።

  በአሁን ሰዓት በህወሃት አመራር መካከል በተፈጠረው የከረረ ክፍፍል እና ያለመግባባት ሳብያ ስጋት ውስጥ የገቡት አቶ አባይ ጸሃዬ የተዘረፈውን የሃገርን ሃብት እና ልጆቻቸውን በሙሉ ከሃገር ማሸሹን እንደአማራጭ መውሰዳቸው የሳቸው ቡድን ህልውና አስጊ ሁኔታ ላይ መድረሱን ያሳያል።

  ከአቶ አባይ ጸሃዬ ውጪ ጄነራል ሳሞራ የኑስ፣ አቦይ ስብሃት ነጋ፣ አርከበ እቁባይ፣ ደብረጽዮን ገብረ ሚካአኤል፣ እና ባለ ማእረግ የህወሃት ወታደሮች በቢሊዮን የሚቆጠር የሕዝብ ገንዘብ እና ዘመድ አዝማዳቸውን በማሸሽ ላይ እንደሚገኙም የተጠቆመ ሲሆን አቶ ብርሃኔ ገብረ ክርስቶስ ከምኒስትር ድኤታ ወርደው የቻይና አምባሳደር እንዲሆኑ የተደረገው ለባለስልጣናቱ የመጨረሻ የማምለጫ አማራጭ ለማበጀት መሆኑን የፖለቲካ ታዛቢዎች ይናገራሉ።

  በትግራይ ህዝብ ስም እየነገዱ ያሉት እነዚህ ጥቂት ሰዎች፣ ሃገሪቱን ለማስተዳደር ያልቻሉበት ደረጃ ላይ እንደደረሱ አለም አቀፍ ሜዲያም እየተናገሩ ይገኛል። የህወሃት ሰዎች በሁለት ጎራ ተከፍለው አሁን የማይወጡበት ችግር ውስጥ ስለገቡ ያላቸው አማራጭ ሃብት እና ዘመዶቻቸውን ማሸሽ በመሆኑ ይህንን ተያይዘውታል። በስሙ ሲነግዱበት የነበረውን የትግራይ ሕዝብ ከሌላው ወገኑ ጋር ሆድና ጀርባ ሆኖ እንዲጫረስ አድርገው እነሱ እግሬ አውጭኝ ማለታቸውን የትግራይ ሕዝብ ከወዲሁ ሊያወግዘው እንደሚገባ በርካታ ሃገር ወዳዶች ሃሳብ እየሰጡበት ነው።

 3. መኪሊት ነኝ says:

  የትገሬ ወያኔዎች ክላሽ ነው የመጡት እናም መኪናውን ከየት አመጡት ? ሽጠው ብሩን ይዘው ወደትግራ ለመኮብለለል ነው ቀስ እያሉ እቃቸውን እየሽከፉ ነው ማለት ነው?

Leave a Reply

Please answer this math question before submitting your comment: