በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት መኖሩ ተጠቆመ

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት መኖሩ ተጠቆመ

BBN – በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት እየተከሰተ መሆኑን መረጃዎች ጠቆሙ፡፡ በተለይ ከአዲሱ ዓመት የበዓል ስነ ስርዓት ጋር ተያይዞ በአንዳንድ ቦታዎች መብራት በፈረቃ እየሆነ መምጣቱን የዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ በሀገሪቱ እየተገነቡ ያሉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድቦች ለሀገሬው ህዝብ በቂ የኃይል አቅርቦት መስጠት ባልጀመሩበት በዚህ ሰዓት፣ መንግስት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ኃይል መሸጥ መጀመሩ ለኃይል እጥረቱ እንደ ዋነኛ ምክንያት ተወስዷል፡፡
በተለይ በዚህ በዓል ወቅት ከፍተኛ የመብራት መቆራረጥ እየተፈጠረ እንደሚገኝ የገለጹት መረጃዎች፣ በተለያዩ የምርት ስራ ላይ የተሰማሩ ፋብሪካዎችም በኃይል እጥረት የተነሳ ለኪሳራ እየተዳረጉ መሆኑን መረጃዎቹ አክለው ገልጸዋል፡፡ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች መብራት ሁለት ቀን የማይኖርበት አጋጣሚ እየተፈጠረ መሆኑን የሚናገሩት የችግሩ ተጠቂዎች፣ በችግሩ የተነሳም ስራ መስራት እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡ በተለይ ስራቸው በመብራት ላይ የተመሰረተ የኢንተርኔት ቤት እና መሰል የንግድ ድርጅቶች ምንም ሳይሰሩ የቤት ኪራይ እየከፈሉ መሆናቸውን በምሬት ይናገራሉ፡፡
‹‹በዓል በመጣ ቁጥር የኃይል እጥረት መከሰት የተለመደ ድርጊት ሆኗል፡፡›› የሚሉት የችግሩ ሰለባዎች፣ ሁኔታው መንግስት ስለ እድገት የሚያወራውን ፕሮፓጋንዳ የውሸት እንደሚያደርገውም ገልጸዋል፡፡ መንግስት በሀገሪቱ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የእድገት ተዓምር መከሰቱን በየጊዜው ሲገልጽ ይስተዋላል፡፡ ሆኖም አብዛኛው ህዝብ ከመብራት እና ከሌሎች ችግሮች ጋር ዛሬም እየተጋፈጠ መሆኑ፣ በመንግስት በኩል ከበሮ የሚደለቅለት የእድገት ፕሮፓጋንዳ ፍጹም የውሸት እንደሆነ ብዙዎችን ያስማማል፡፡■ Subscribe to mereja.com's email newsletter. ⇒ CLICK HERE እዚህ ላይ ይጫኑ ⇐

► Post your comment below
የአንባቢያን አስተያየቶች

  1. እናት ነኝ says:

    የወያኔ ትግሬ ሽፍቶች አገዛዙን የያዙት በሚገኝ ሀብት ሁሉ ትግራይን ለመገንባት: እንጂ ለኛና ለሀገራችን ሊስሩ አይድለም ! ድሮስ አገዛዝ ላይ ቁጭ ብሎ ሱካር ኬንያ ልኮ የሚሽጥ ከተራ ሽፍታ ሌባ ምን ይጠበቃል: ሀብታችንና ንብረታችን እንዲጠበቅ: ሁላችንም በምንስራበትና በያለንበት ታግለን ለመጣል ባለው ዘዴ ሁሉ እንታገላቸው ! በአዲሱ ዓመት የማግለል የማራቅ ትግላችንን የምናፋፍምበት ይሁን !!

Leave a Reply

Please answer this math question before submitting your comment: