የስዊድን ገዢ ፓርቲ “ከህወሃት ጋር በአንድ ስብሰባ ላይ ልገኝ አልችልም” አለ

የስዊድን ገዢ ፓርቲ “ከህወሃት ጋር በአንድ ስብሰባ ላይ ልገኝ አልችልም” አለ
የስዊድን ገዢ ፓርቲ የሆነው ሶሻሊ ዲሞክራሲ ፓርቲ የአውሮፓ የሶሻሊ ዲሞክራቲክ ፓርቲዎች እንዲሁም የአፍሪካ መንግስታት የሚሳተፉትበትን የናምቢያ ስብሰባ እንደማይሳተፍ አስታወቀ።
የፓርቲው አባል ሚ/ር አንደርስ ኦስተርበርግ ለኢሳት እንደገለጹት ስብሰባው በዋናነት ማህበራዊ ዲሞክራሲያዊ ጉዳዮችን በማንሳት ለመወያየት የተጠራ ቢሆንም፣ ፓርቲያቸው ግን የህወሃት መንግስት በስብሰባው በመጋበዙ ተቃውሞአቸውን ለማሳየት በስብሰባው ላይ አይገኙም።
የህወሃት መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጽመው የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተጠናከረ በመምጣቱ በአንድ ክፍል ውስጥ አብረን ለመሳተፍ መርሆዋቸውን አይፈቅድም ያሉት ሚ/ር አንደርስ፣ በስብሰባው አለመሳተፋቸውን ለአዘጋጆች ገልጸዋል። የህወሃት መንግስት መስመሩን እየጣሰ ነው ያሉት የፓርላማ አባሉ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ሊመረምር ይገባል ይላሉ
የእሳቸው ፓርቲ የኢትዮጵያን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የሚገልጹት ሚ/ር አንደርስ፣ በኦሮምያ በእሬቻ በአል ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ፣ በአማራና በኦጋዴን አካባቢዎች የሚፈጽሙት ጭፈጨፋዎች ሁሉ እንዲጠራ ግፊት እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።
የስዊድን መንግስት የህወሃት መንግስት በሚፈጽመው ድርጊት የተነሳ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት እንደማያቋርጥ የገለጹት ሚ/ር አንደርስ፣ ህዝቡ በቀጥታ ተጠቃሚ በሚሆንባቸው ስራዎች ላይ መሳተፋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።■ Subscribe to mereja.com's email newsletter. ⇒ CLICK HERE እዚህ ላይ ይጫኑ ⇐

⇩ Post your comment below
Leave a Reply

Please answer this math question before submitting your comment: