ዘመን ለሞተባት.. መልካም አዲስ አመት

ዘመን ለሞተባት.. መልካም አዲስ አመት ሲሳይ በዛብህ

ለዚህ ጽሁፍ መነሻ ከዚህ ቀደም ያነበብኩትና አሁን ቃል በቃል የማላስታውሰውን የዶ/ር ሃይሉ አርአያ ግጥም ሃሳብ ነው ፡፡ ኢትዮጵያ- ዘመን የሞተባት ! በእውነቱ እጅግ ከባድ ነው ለማፅናናት – ምክንያቱም ነገም ነው የሞተው፡፡ ዘመናዊው የኢትዮጵያ ታሪክ እንጣጥ ብሎ ወደ ሁዋላ ማለት የጀመረው አስተዋዩና ጠንካራ ሰራተኛው ጸሐፊ ትእዛዝ ወ/ጊዮርጊስ ወ/ዮሃንስ ከቦታቸው ተነስተው የአሩሲ አስተዳዳሪ ከተደረጉ በኋላ እንደሆነ የታሪክ መረጃዎችና አሁንም በሂይወት ያሉ ሰዎች ይናገራሉ፡፡

እኝህ ጠንካራ ሰው ንጉሱ ልክ እንደ እንግሊዝና ስዊዲን አገር ንጉሶች የአገሪቷ አባት ሆነው ፖለቲካውን ግን በዲሞክራሲያዊ የተመረጠ ፓርቲ እንዲያስተዳደርው ያስቀመጡትን ሃሳብ በጊዜው በነበሩት እወደድ-ባይ መሳፍንት ደባ/ ሴራ ምክንያት ከተስተጓጎለ ጀምሮ እስከ አሁን የአገሪቷ አንጡራ ሃብት እንዲሁም ሰዎቿ እንዲሁ እንደባከኑ ይሔው 62 አመት ሞላው፡፡

በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በስደት፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጦርነት፤ በሰላሳ ሺዎች የሚቆጠሩ በቀይ ሽብር፤ በመቶ ሺዎች በወያኔ ድምፅ በሌለው ጥይት፤ ስንቱ ተፅፎ ..ስንቱ ተዘርዝሮ ያልቃል፡፡ ጸሐፊ ትዕዛዝ ወ/ጊዮርጊስ ከ 30 አመት በላይ ኢትዮጵያን ካገለገሉበት ሃላፊነት በ1948 ዓ.ም ከተገለሉ በኋላ የታህሳስ ግርግር (1953)፤ የተማሪዎች አመጽ(1960ቹ)፤ ህዝባዊ አመጽ (1966/67)፤ ደርግ የተማሪውንና የህዝብ ድምፅ መቀማት፤ቀይ ሽብርና ነጭ ሽብር (1967-1972)፤ የ1977 ረሃብ፤ የሻዕቢያና የወያኔ ጦርነት(1969-1983)፤ የኤርትራ መገንጠል (1983)፤ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት (1990-92)፤ ምርጫ 97 ጭፍጨፋ፤ የእሬቻ ጭፍጨፋ (2008) እያለ ይሄው በዘመን ማፌዝ ለጀመረው ወያኔ እየገደሉ “የፍቅር ቀን” የሚከበርበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡

የዘንድሮ ዘመን መለወጫ ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ከዘመናዊ ፓስተሮች የተኮረጀቺውና እንደከሰመ ፈስ የምታስተጋባው “መጪው ጊዜ የኢትዮጰያ የከፍታ ዘመን ነው” የምትል አስቂኝ የልጆች ተረት ይዞ ዘራፊው ወያኔ 2010ን ሊጀምር ነው፡፡ ነገር ግን የሁሉም ሰው ልብ ያውቀዋል -ሃገራችን መኩሪያችን መመኪያችን ዘመኗ እየሞተ እንደሆነ፡፡ ሁላችንም የጨነቀን መጨረሻውን ማየት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሳይተክሉና ሳያጠጡ አምላክ እንዲያፅድው መጠበቅም ቂልነት ነው፡፡ ስለዚህ ለዘመን-ትንሳዔው በጋራ ለመታገል ግን ቆርጠን እንነሳ!!

የአንባቢያን አስተያየቶች

  1. Waralata says:

    What posted here is a genuine view of all Ethiopians who understands the down word spiral our country is in for the past twenty six years and counting.To gain some thing one has to work for it.In our case,some think that time will solve it but the time we think about is sleeping away from us every day and hour.Be it our respective ethnics or political belief Ethiopia must be saved first.If Ethiopia is not there none of us will have a country.Though it is consuming and exploiting us all Wayne itself can’t service in the absence of Ethiopia but it needs a wick Ethiopia so it can exploit as it needs.
    So let this “new”year be the NEW year for our unity and freedom for Ethiopians.

  2. Anonymous says:

    R I P

Leave a Reply

Please answer this math question before submitting your comment: