የሶማሌ ክልል ጦር በኦሮሚያ እየፈጸመ ያለውን ጥቃት ለመመከት ህብረተሰቡ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

የሶማሌ ክልል ጦር በኦሮሚያ እየፈጸመ ያለውን ጥቃት ለመመከት ህብረተሰቡ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

BBN

Image may contain: one or more people and outdoor

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ልዩ ጦር ጥቃት እየተፈጸመባቸው ያሉ የኦሮሞ ተወላጆች በተጠንቀቅ ቆሙ፡፡ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ በኦሮሞ ተወላጆች ላይ እየፈጸመ ያለውን ጥቃት ተከትሎ፣ ህብረተሰቡ በተጠንቀቅ መቆሙን መረጃዎች ጠቆሙ፡፡ ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ በምስራቅ ሐረርጌ ሜኢሶ ከተማ ንጹኃንን ሲገድል የቆየው የሶማሌ ክልል ልዩ ጦር፣ አሁን ደግሞ ወደ ሌሎች የኦሮሚያ አካባቢዎች መዝመቱን በትላንትናው ዘገባችን ጠቁመን ነበር፡፡

ጦሩ በአሁኑ ወቅት በማን አለብኝነት በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች ያደረሰው ጥቃት ብዙዎችን አስቆጭቷል፡፡
ከምስራቅ ሐረርጌ በመቀጠል ወደ ባሌ እና ቦረና እንዲሁም ጉጂ ዞኖች የተንቀሳቀሰው የሶማሌ ክልል ልዩ ጦር፣ በተጠቀሱት ቦታዎችም ግድያ ፈጽሟል፡፡ ይህን ተከትሎም የአካባቢው ህዝብ ራሱን ከጥቃት ለመከላከል በተጠንቀቅ እየቆመ እንደሚገኝ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ‹‹አስታጥቁን ወይም አታስጨርሱን›› ሲሉ ለኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት አቤቱታ ያቀረቡት ተጠቂ የኦሮሞ ተወላጆች፣ ‹‹ካለበለዝያ ባለን አቅም ራሳችንን ለመከላከል እንገደዳለን፡፡›› ማለታቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት በበኩላቸው፣ ግጭቱ የሁለቱ ክልሎች ማለትም የሶማሌ እና የኦሮሚያ ክልል ህዝቦች አለመሆኑን በመግለጽ፣ የተጠቂዎቹን የነደደ ቁጣ ለማብረድ መሞከራቸውንም ምንጮች አክለው ገልጸዋል፡፡ ባለስልጣናቱ ይህን ቢሉም፣ ጥያቄ አቅራቢዎቹ ግን ‹‹ምንም አላችሁ ምን ራሳችንን ለመከላከል እንገደዳለን፡፡›› በማለት በተጠንቀቅ መቆማቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
የሶማሌ ክልል ልዩ ጦር በምስራቅ ሐረርጌ የሚፈጽመውን ጥቃት ተከትሎ፣ የአካባቢው ማኅበረሰብ ራስን የመከላከል እርምጃ ሲወስድ ቆይቷል፡፡ ራስን የመከላከል እርምጃው በተመሳሳይ ሁኔታ በባሌ እና በቦረና ጉጂ ዞኖችም ሊተገበር እንደሚችል ተነግሯል፡፡ በዚህም የተነሳ በተጠቀሱት አካባቢዎች ሰላም እና መረጋጋት እንደሌለ ከመረጃዎች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በህወሓት አዛዥነት የሚመራው የሶማሌ ክልል ልዩ ጦር፣ ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ በኦሮሚያ ባሌ እና ጉጂ ቦረና ዞኖች ከ15 በላይ ሰላማዊ ሰዎችን መግደሉ ተነግሯል፡፡

የአንባቢያን አስተያየቶች

  1. Hailu shawul says:

    Tigrai siting in daily bomb and sleeples due to fear from shabya. therefore they try to share such fear and instablity through out the country. additionaly they want to change direction of people struggle.

  2. ገረመው says:

    ወያኔ ናት ይህን ሁሉ ወንጀል እየሰራች ያለችው ፡ ልዩ ሃይል ብላ የመሰረተችው ወያኔ ነች ፡ ያስታጠቀችውና ደሞዝ የምትከፍለው ወያኔ ነች ፡ የምታዝዘውም ይህችው ደንባራ ወሮ በላ ወያኔ ነች ፡ ይህችው ደንባራ ካልተነቀለች ማነኛውም ኢትዮጵያዊ በሰላም መኖር አይችልም ፡ ተባብረህ አንድ በል ወገኔ ።

Leave a Reply

Please answer this math question before submitting your comment: