ኦህዴድ ውስጥ የፖለቲካ አለመረጋጋት መፈጠሩ ተጠቆመ

ኦህዴድ ውስጥ የፖለቲካ አለመረጋጋት መፈጠሩ ተጠቆመ

BBN  – የኦሮሞ ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) የፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ እንደሚገኝ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ በኦሮሚያ እየተካሔደ ካለው ያላቋረጠ ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ እንደገባ የተነገረለት ኦህዴድ፣ በህወሓት አማካይነት ሹም ሽር ለማድረግ ተገድዷል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ህዝባዊ ተቃውሞ በተነሳ ቁጥር የኦህዴድን አመራር እንደ አዲስ የሚያዋቅረው ህወሓት፣ በዚህኛው የተቃውሞ ወቅትም ሹም ሽር ለማድረግ ተገድዷል፡፡

ህወሓት ባዘዘው መሰረት የድርጅቱን ስራ አስፈጻሚ አመራር በአዲስ ለመቀየር የተገደደው የኦሮሞ ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ ስድስት የስራ አስፈጻሚ አባላትን ሾሟል፡፡ በተጨማሪም የፓርቲውን የፖለቲካ እና የፕሮፓጋንዳ ስራ የሚያስኬዱ አስር የማዕከላዊ ኮሚቴ አላባትንም ቀይሮ በአዲስ ተክቷል፡፡ ላለፉት በርካታ ዓመታት የኦህዴድን የስራ አስፈጻሚም ሆነ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ባሻው መንገድ ሲሾም እና ሲሽር የቆየው ህወሓት፣ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ህዝባዊ ተቃውሞ በሚነሳበት ወቅት ድርጅቱን እንደ አዲስ ማዋቀር ይቀናዋል፡፡

ለህወሓት ፖለቲካ ፍጹም የተመቸው እና በራሱ በህወሓት የተፈጠረው ኦህዴድ፣ በራሱ ውሳኔ ሰጪነት ያሳለፋቸው ትልልቅ የፖለቲካ ውሳኔዎች አለመኖራቸውን ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡ ህወሓት ነባሩን የኦህዴድ ስራ አስፈጻሚ አባላት በአዲስ ለመተካት ያሰበው፣ በኦሮሚያ ክልል ለሶስት ቀናት የስራ ማቆም አድማ መካሔዱን ተከትሎ ነው፡፡ ከ20 ቀናት በፊት በክልሉ የተካሔደውን ህዝባዊ አድማ ተከትሎ፣ በኦሮሚያ የንግድም ሆነ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ቆመው እንደነበር ይታወሳል፡፡ በወቅቱ የተደረገው ህዝባዊ አድማ በኦህዴድ ውስጥ የፖለቲካ አለመረጋጋት እንዲፈጠር እንዳደረገ የሚገልጹት ምንጮች፣ ህወሓትም የድርጅትን አመራሮች ለመቀየር የወሰነው ከዚያ አድማ በኋላ መሆኑን ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል፡፡ የዛሬ ዓመት በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ መነሳቱን ተከትሎ፣ በኦህዴድ ውስጥ የመአራር ለውጥ መደረጉ ይታወሳል፡፡ ለውጡም የክልሉን ፕሬዚዳንት አቶ ሙክታር ከድርን ያካተተ ነበር፡፡

የአንባቢያን አስተያየቶች

  1. waw says:

    ባርነት ያደሩ ሰዎችን ፖለቲካጋ ማን አድርሷቸው ነው “የፖለቲካ አለመረጋጋት” የሚኖረው?

    ሕወሃትን እያገለገሉ ፡ የሕወሃትን ትራፊ በብላት ፡ ፖለቲካ አይሆንም!

  2. Jabessa says:

    Gulicha bekeyayeru wet ayatafetem. a Fish stinks from a head.

Leave a Reply

Please answer this math question before submitting your comment: