በአዲስ አበባ በተሰጠው የመምህራን የብቃት ማረጋገጫ ፈተና በርካቶች ከደረጃ በታች ሆኑ

በአዲስ አበባ በተሰጠው የመምህራን የብቃት ማረጋገጫ ፈተና በርካቶች ከደረጃ በታች ሆኑ

BBN  – በአዲስ አበባ በስራ ላይ ለተሰማሩ የአንደኛ ደረጃ መምህራን በተሰጠው የብቃት ማረጋገጫ ፈተና በርካቶች ከደረጃ በታች ማምጣታቸውን መረጃዎች ጠቆሙ፡፡ እንደ መረጃዎች ገለጻ፣ የጽሁፍ ፈተና የተሰጣቸው መምህራን ብዛት 5 ሺህ 165 ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ ፈተናውን ያለፉት 9 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ሆነዋል፡፡ ፈተናው የተሰጠው ለአንደኛ ደረጃ መምህራን ሲሆን፣ አብዛኞቹም እንኳን ሌላ ሰው ሊያስተምሩ ራሳቸውም በድጋሚ ትምህርት ቤት ገብተው መማር የሚገባቸው መሆኑ ታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኘው አገዛዝ እየተከተለ ያለው የትምህርት ስርዓት ትውልድ እያመከነ እንደሚገኝ የሚገልጹ አስተያየት ሰጪዎች፣ ከተለያዩ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ተመርቀው እየወጡ ካሉ ሰዎች፣ አብዛኞቹ ብቃታቸው ከደረጃ በታች እንደሆነም አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል፡፡ የብቃት ችግሩ የሚስተዋለው በሁሉም የትምህርት ተቋማት ቢሆንም፣ በተለይ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በመምህርነት የተቀጠሩ ሰዎች፣ ብቃታቸው እጅግ አጠያያቂ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ብቃት ያላቸው ምሁራንን በፖለቲካ አመለካከታቸው የተነሳ ከዩኒቨርሲቲዎች በማባረር የሚታወቀው ስርዓቱ፣ ትምህርት ቤቶች ብቃት በሌላቸው ሰዎች እንዲሞሉ እያደረገ ስለመሆኑ የሚናገሩ ታዛቢዎች አሉ፡፡ ገና ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ከምሁራን ጋር መጋጨት የጀመረው የህወሓት አገዛዝ፣ ባለፉት 26 ዓመታት ትምህርት ቤቶችን የካድሬዎች መፈልፈያ አድርጎ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ ዩኒቨርሲቲዎች ድረስ፣ መምህራን በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ ጥቃት ሲፈጸምባቸው ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡ ብዙ መምህራንም ባላቸው የፖለቲካ አመለካከት ብቻ ከስራቸው እንዲባረሩ ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡■ Subscribe to mereja.com's email newsletter. ⇒ CLICK HERE እዚህ ላይ ይጫኑ ⇐

► Post your comment below
የአንባቢያን አስተያየቶች

  1. Doo says:

    Rasu Wyane Pm Temehert Yelewm

Leave a Reply

Please answer this math question before submitting your comment: