አንድ የእስራኤል ኩባንያ የኢትዮጵያ መንግስትን በዓለም ዓቀፍ ፍርድ ቤት እገትረዋለሁ አለ

አንድ የእስራኤል ኩባንያ የኢትዮጵያ መንግስትን በዓለም ዓቀፍ ፍርድ ቤት እገትረዋለሁ አለ

BBN  –  እስራኤል ኬሚካል የተባለ አንድ የእስራኤል ኩባንያ፣ የኢትዮጵያን መንግስት በዓለም ዓቀፍ ፍርድ ቤት መክሰሱን አስታወቀ፡፡ ኩባንያው ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ አፋር ክልል የፖታሽ ማዕድን ለመፈለግ ከመንግስት ጋር ተስማምቶ ሲሰራ ቆይቶ ነበር፡፡ ሆኖም፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከህግ ውጪ ግብር ጠይቆኛል በማለት ከአስራ አንድ ወራት በፊት ስራውን እርግፍ አድርጎ በመተው ኢትዮጵያን ለቅቆ የወጣው ኩባንያው፣ ‹‹የኢትዮጵያ መንግስት ላደረሰብኝ የኢንቨስትመንት ኪሳራ በዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት ክስ መስርቻለሁ፡፡›› ብሏል፡፡
አቤቱታውን ይዞ ወደ ዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት ዘ-ሔግ (ኔዘርላንድ) ያመራው የእስራኤሉ አይ ሲ ኤል ኩባንያ፣ የኢትዮጵያ መንግስት አደረሰብኝ ላለው የኢንቨስትመንት ኪሳራም፣ 198ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንዲከፈለው ለርፍድ ቤቱ ጥያቄ ማቅረቡ ታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ አፋር ክልል ጀምሮት የነበረው የማዕድን ማውጣት ስራ የተደናቀፈው፣ የኢትዮጵያ መንግስት ባቀረበለት ህግን የጣሰ ግብር ምክንያት እንደሆነ የገለጸው ኩባንያው፣ በተጨማሪም የማዕድን ፍለጋውን በሚሰራበት አፋር ክልል በቂ መሰረተ ልማት አለመኖሩ ለኢንቨስትመንቱ መምከን ሌላ ምክንያት እንደሆነው ኩባንያው ገልጿል፡፡
በአፋር ክልል ዳሎል በተባለው ስፍራ የፖታሽ ማዕድን ለማውጣት ከመንግስት ጋር ውል አስሮ የነበረው የእስራኤሉ ማዕድን አሳሽ ኩባንያ፣ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ቀረበልኝ ያለው ህገ ወጥ ግብር መጠን ሃምሳ ሚሊዬን ዶላር ነው፡፡ ኩባንያው እንዲከፍል ከታዘዘው ሃምሳ ሚሊዬን ዶላር ግብር ውስጥ አርባ ሚሊዬኑ የካፒታል ዕድገት ግብር ሲሆን፣ ቀሪው አስር ሚሊዬን ደግሞ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የዊዝሆልዲንግ ታክስ መሆኑ ተነግሯል፡፡
አይ ሲ ኤል የተባለው የእስራኤል ማዕድን ፈላጊ ኩባንያ፣ የማዕድን ማውጣት ስራ ለማከናወን በተሰማራበት አፋር ክልል አንድ የማዕድን ማውጫ ፋብሪካ ጨምሮ ሶስት የማዳበሪያ ፋብሪካዎችን ለመገንባት እንቅስቃሴ ጀምሮ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፣ ሆኖም ከመንግስት በኩል በቀረበለት አላስፈላጊ የግብር ጥያቄ የተነሳ ውጥኖቹ እንደከሰሙበት ኩባንያው አስታውቋል፡፡ ለዚህ ሁሉ ኪሳራ እና መጉላላት ፍትህ ለማግኘት ጉዳዩን ወደ ዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት ይዞት መሔዱን የገለጸው ኩባንያው፣ ለደረሰበት ኪሳራም የኢትዮጵያ መንግስትን 198 ዶላር ካሳ መጠየቁ ተነግሯል፡፡
ከእስራኤሉ ኩባንያ አስቀድሞ በአፋር ክልል የፖታሽ ማዕድን ለማውጣት ከመንግስት ጋር ተስማምቶ የነበረው አላና ፖታሽ የተባለ አንድ የካናዳ ኩባንያ ሲሆን፣ ኩባንያው የማዕድን ማውጣት ስራውን ለማከናወን የሚያስፈልገውን 700 ዶላር ማቅረብ አለመቻሉን ተከትሎ፣ ስራው ለእስራኤሉ ኩባንያ ተላልፎ እንደተሰጠ ተነግሯል፡፡ የእስራኤሉ ኩባንያ 150 ሚሊዬን ዶላር የአክሲዮን ገንዘብ በማቅረብ፣ በ2015 ከካናዳው ድርጅት ላይ የማዕድን ቁፋሮ ስራውን መረከቡም ተገልጿል፡፡
ኩባንያው በመንግስት ላይ የመሰረተውን ክስ አስመልክቶ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጥያቄ የቀረበላቸው የማዕድን፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ሞቱማ መቃሳ፣ ኩባንያው በመንግስታቸው ላይ ክስ መመስረቱን ቢያምኑም፣ ዝርዝር ጉዳይ ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡ ‹‹ጉዳዩ በህግ የተያዘ ስለሆነ አስተያየት እንደማይሰጡም›› አክለው ገልጸዋል፡፡ መቀመጫውን በኔዘርላንድ ያደረገው ዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት ዘ ሔግ፣ ጉዳዩን መርምሮ በቀጣይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡■ Subscribe to mereja.com's email newsletter. ⇒ CLICK HERE እዚህ ላይ ይጫኑ ⇐

► Post your comment below
የአንባቢያን አስተያየቶች

  1. xo says:

    Esti Haile Selassien. Ke silatan endaweredachu. Enezin nekersawoch. Ke Ethiopian midir atfulin.

Leave a Reply

Please answer this math question before submitting your comment: