የስኳር እና ዘይት እጥረት እንዳማረራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ

የስኳር እና ዘይት እጥረት እንዳማረራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ

BBN – በአዲስ አበባ የተከሰተው የዘይት እና ስኳር እጥረት በእጅጉ እንዳማረራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ ለቢቢኤን አስተያየታቸውን የሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ ‹‹እጥረቱ መከሰት ከጀመረ ትንሽ ቆየት ቢልም፤ አሁን ላይ ግን አማራሪ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡›› ብለዋል፡፡ እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ፣ በአሁን ወቅት ስኳርን በፈለጉት ሰዓት ማግኘት ዘበት ሆኗል፡፡ ዘይትም ቢሆን፣ ከዋጋው መወደድ ጀምሮ እስከ ከገበያ መጥፋት ደረጃ መድረሱንም ነዋሪዎቹ ይናገራሉ፡፡
በተለይ ከአዲሱ ዓመት የበዓል ሸመታ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ እጥረት እንደተከሰተ የሚናገሩት የችግሩ ተጠቂዎች፣ መንግስት በቂ ምርት አለ ማለቱንም ያጣጥሉታል፡፡ ‹‹በቂ ምርት ካለ ለምን አውጥቶ አያሳየንም ታዲያ?›› ሲሉ ጥያቄ አዘል አስተያየት ያቀረቡት ነዋሪዎቹ፣ ሀገሪቱ በየጊዜው ቁልቁል እየሔደች እንደሆነም ይናገራሉ፡፡ አክለውም ‹‹መንግስት መሰረታዊ ነገሮችን በአግባቡ አሟልቶ ሳይጨርስ፣ ስለ ዕድገት ባያወራ ይመረጣል፡፡›› ብለዋል፡፡
በመሰረታዊ ፍጆታዎች ላይ ከፍተኛ እጥረት መከሰት የጀመረው በተለይ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ2002 ወዲህ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በወቅቱ በገበያ ስርዓቱ ላይ ተፈጠረ የተባለውን አለመረጋጋት ለማስተካከል በሚል፣ ነጋዴው ማኅበረሰብ መንግስት ባወጣለት ተመን ዕቃዎችን እንዲቸረችር ተደርጎ ነበር፡፡ ሆኖም ይህ ሁኔታ ከተወሰነ ጊዜ በላይ መዝለቅ አለመቻሉን ታዛቢዎች ያስታውሳሉ፡፡ በወቅቱ መንግስት የእዝ ኢኮኖሚ ስርዓት በመከተል ነጋዴው፣ መንግስት ባስቀመጠለት የዋጋ ተመን እንዲሸጥ ማስገደዱ እስከ ዛሬ ለቀጠለው የገበያ ስርዓት ቀውስ የራሱን አስተዋጽዖ ማድረጉንም ታዛቢዎቹ ይስማሙበታል፡፡
ዛሬ ገበያ ወጣ ብሎ የፈለጉትን ዕቃ ገዝቶ መመለስ ከባድ እየሆነ ነው ያሉት ለቢቢኤን አስተያየታቸውን የሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ ዘይት እና ስኳር አልያም ሌላ ዕቃ ለመግዛት ረዥም ሰዓት ሰልፍ ለመያዝ እንደሚገደዱ ገልጸዋል፡፡ ‹‹መንግስት ነጋዴውን ማኅበረሰብ እንደ ጠላት ስለሚያየው፣ በሁለቱ አካላት መካከል ጤናማ ግንኙነት እንዳይኖር አድርጓል፡፡›› ሲሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ መንግስት በተለያየ ጊዜ በነጋዴው ማኅበረሰብ ላይ የተከተለው አካሔድ፣ ለሀገሪቱ የገበያ ስርዓት መመሰቃቀል ትልቅ ሚና ተጫውቷል ብለዋል-ነዋሪዎቹ፡፡





የአንባቢያን አስተያየቶች

 1. Amanuel ze ፥ says:

  ውድ Wow መልዕክቱ ካልጣመሽ/ህ/ይቅርታ በርግጥ ማንም ይሁን ማን ሁሉንም ሰው በእኩል ማስደሰት አይችልም! ሁሉም ሰው ነገሮችን ለራሱ በገባው መልኩ ይተረጉማልና! ቢሆንም ይቅርታዬ ይሰመርበት!!አንተ/ቺ/ሁሌም ትክክል ነሽ/ህ/።

 2. Amanuel ze Ambo says:

  ውድ Wow መልዕክቱ ካልጣመሽ/ህ/ይቅርታ በርግጥ ማንም ይሁን ማን ሁሉንም ሰው በእኩል ማስደሰት አይችልም! ሁሉም ሰው ነገሮችን ለራሱ በገባው መልኩ ይተረጉማልና! ቢሆንም ይቅርታዬ ይሰመርበት!!አንተ/ቺ/ሁሌም ትክክል ነሽ/ህ/።

  • waw says:

   ወንድሜ ችግራችን የጋራ ነው 😉

   አበሾች ችግር በመሸከም ፡ ዓለም ላይ የሚወዳደረን ሕዝብ የለም።
   ምስክር ፡- የሕወሃትን መንግስት ከተሽክመን 26 ዓመታችን ነው።

   በተመሳሳይ ሰዓት ፡ አበሾች በአስተያየታችን ላይ ፡ የማረሚያ አስተያየት ፡ ማስተናገድ አንወድም፥
   ለዚህ ምሳሌ የሚያስፈልግ አይመስለኝም!
   ለማንኛውም ቆዳህን ካሳሳህ መጻፍ ይከብዳልና አስብበት። የጠቆምኩት ችግሩ ለተቃዋሚዎች ተብሎ ሊተው እንደማይችል ነው ፥ ይሁላችንም ችግር ነውና።
   እንደተግባባን ተስፋ አረጋለሁ።

 3. Amanuel ze Ambo says:

  የሀገራችን ጉዳይ አንዳንዴ ግርም ያሰኛልኮ!! ለምሳሌ የዘይትን እጥረት ለመቅረፍ መንግስት …የሚል ዜና ከሰማችሁ ቶሎ ዘይት መሸማመት ነው ዜናው የሚያወራው ተቃራኒውን ስለሆነ በአንፃሩ ዘይት ሊጠፋ ነው ማለት ነው። የስኳርም እንዲሁ ነው የስኳርን ምርት ለሀገር ውስጥ ፍጆታ አትረፍርፎ ኤክስፖር በማድረግ ኢኮኖሚያችንን በብዙ ዲጂት ለማሳደግ መንግስት…የሚል ዜና ከተለቀቀ ስኳር ሊጠፋ ስለሆነ ቶሎ ሸመትመት ማድረጉ ይበጃል ዜናው የሚያወራው ተቃራኒውን ነውና። የነዳጅ እጥረትን ለመቅረፍ ቀድሞ ከምንጠቀምበት መንገድ በተጨማሪ ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም በቂ የነዳጅ ክምችት እንዲኖር መንግስት …የሚል ነገር ሚዲያው ካወራ ነዳጅ ሊጠፋ ዋዜማው ላይ ነው ማለት ነውና የመኪናችሁን ከርስ ፉል ከማድረግ በተጨማሪ በሌላ ነገር አጠረቃቅሙ ይሄ በተወራ በአጭር ቀን ነዳጅ ይጠፋል ማለት ነውና።የመብራት እጥረት ፈፅሞ ሊከሰት የማይገባውና ለሌላም የምንተርፍ ሆነን ሳለ አንዳንድ ፀረ ሰላም ሃይሎች ከውጭ ሃይሎች በሚሰጣቸው የጥፋት ተልዕኮ ቆጣሪዎችን (መቆጣጠሪያዎችን) በመመለስ ሕብረተሰቡ በመንግስት እንዲማረር በማድረግ የፈጠሩት ተንኮል እንጂ በቂ የመብራት ኃይል ስላለን ህብረተሰቡ በአግባቡ እንዲጠቀም መንግስት …የሚል ዜና ከተለቀቀ ከቀድሞው ሊብስበት ስለሆነ አቅም ያላችሁ ጀነሬተር የሌላችሁ የቻይና ባትሪ ሻማና ኩራዛችሁን አዘጋጁ የሚል መልዕክት ስላለው በዚህ መልኩ ተረዱት የትራንስፖርት ጉዳይም በዚህ መልኩ ይታይ ለምሳሌ የትራንስፖርትን እጥረት ለመቅረፍ ባቡር:በርካታ አውቶቡሶችን:ሜትር ታክሲዎችን:ሌሎች ልዩልዩ መንገዶችን በመጠቀም ህብረተሰቡ ወደፈለገበት ሁሉ በፈለገው ሰዓት እንዲደርስ መንግስት …የሚል ዜና ብትሰሙ እንዳትዘናጉ አቅም ያላችሁ መኪና:ሌሎችም እንደአቅማችሁ ሞተር ሳይክል:የሌላችሁ ደግሞ እግሬን ባርክልኝ ብላችሁ ቀደም ብሎ በመነሳት በእግር መሸክሸክ ነው ሌሎቹንም በዚሁ መልኩ ተረድቶ መጠቀሙ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው። እናንተየ አስተውላችሁ ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ በየዕለቱ ያልተከለከለ ሰልፍ አለኮ የታክሲ:የዳቦ:የዘይት:የስኳር:የስጋ:የነዳጅ ዋ ዋ ዋ ያልታደለ ተቃዋሚ ይህን የመሰለ የየዕለት ሰልፍ እያለለት እነኚህን የተለያዩ ሰልፎች አደራጅቶ ለውጥ ማምጣት ሲችል እንዲያው…

  • waw says:

   ተቃዋሚው ከእርስዎ የተለየ ነገር እንዲሰራ መጠበቅ ፥ አግባብ ይመስልዎታል?

   ሃላፊነቱ የሁላችንም ነው!

 4. xo says:

  Ye Addis Abeba Hizeb hoy. Tensteh Woyane Atifa . Aleya berhab Talkaleh!?

  • waw says:

   ወደሽ ከተደፋሽ ፥ ቢረግጡሽ አይክፋሽ!

   በፈቃዳችን የተሸከምነውን ሕውሃትን ፡ ማማረር 😉

   • Dinkem Wechegud says:

    man new wedo yetedefaw, tegedo enji! Lemanegnawem lemefered atechekul. our problem is so complex and complicated which your premature suggestion cant make a stone throw away change. Rather find a way and share it with us on its application.

    • waw says:

     ሕወሃት መቶ ሚሊዮን ሕዝብ አስገድዶ የሚገዛበት አቅም ሊኖረው አይችልም! ማንኛውም ዲክታተር ለተወሰነ ግዜ ሕዝብ ላይ በመሳሪያ ጉልበት ሊቆይ ይችላል። ሕዝብ የነጻነት ምንነትና ከተረዳና ፥ ነጻ የመውጣትን ፍላጎት ካየለ ግን ፡ ይህንን ሱናሚ ሕወሃት ሊቋቋም አይችልም።

     አማራ ኦሮሞ ……… ብለን ተከፋፍለን ፥ እራሳችንን ለሕወሃት ቅርጫ ያቀረብነው ፡ እኛው እራሳችን ነን!
     ሌላ ሁለተኛ አገር እንዳለው ሰው ፡ ፖለቲካ አታሰሙን እያልን ከርሳችንን ስንሞላ ኖረን የምናልፈው እኛው ነን!
     መጸለይ የመጀመሪያ ስራ ሆኖ ፥ በተግባር ግን መታገዝ እንዳለበት መረዳት ያቃተን ፡ እኛው እራሳችን ነን!
     እኛ ባለንበት ሁኔታ ፥ ይህ እኔና አንተን ያገናኘን ከላይ ያለው አርዕስት ላይ ፡ መነጋገር እራሱ አሳፋሪ ነው! በአፓርታይድ ስር ያለ ሕዝብ ችግሩ ሌላ ነው!

     መፍትሄው ጎሳ ቆጠራን አቁሞ ፡ ሁሉም ክልሉን ከወያኔ ማጽዳት ነው፡፡ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም በአቅሙ መጠን መሳተፍ የዜግነት ግዴታው መሆኑን መረዳት የመጀመሪያው እርምጃ ይሆናል!

Leave a Reply

Please answer this math question before submitting your comment: