የናይጄሪያ አየር መንገድ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የ56 ሚሊዬን ዶላር ክስ መመስረቱ ተነገረ

የናይጄሪያ አየር መንገድ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የ56 ሚሊዬን ዶላር ክስ መመስረቱ ተነገረ

BBN  –  የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሐሰተኛ መግለጫ አሰራጭቶብኛል ያለው የናይጄሪያ አየር መንገድ ክስ መመስረቱ ተገለጸ፡፡ አሪክ በሚል ስያሜ የሚጠራው የናይጄሪያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህ ቀደም ያሰራጨውን መግለጫ በመቃወም ነው ክስ መመስረቱን የገለጸው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰሞኑ በሰጠው መግለጫ፣ አሪክ የተባለውን የናይጄሪያ አየር መንገድ ማኔጅመንት ተረክቦ ለማስተዳደር ድርድር መጀመሩን ገልጾ ነበር፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋ ያደረገው መረጃ ‹‹በስራዬ ላይ ጉዳት አድርሶብኛል፡፡›› ሲል አቤቱታ ያቀረበው የናይጄሪያው አየር መንገድ፣ ለዚህ የሞራል ጉዳትም ካሳ እንዲከፈለው ለናይጄሪያ ፍርድ ቤት ክስ አቅርቧል፡፡ አየር መንገዱ ለሀገሩ ፍርድ ቤት ባቀረበው የሞራል ካሳ ይገባኛል ክስ ላይ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 56 ሚሊዬን ዶላር እንዲከፍለው ጠይቋል፡፡ የናይጄሪያው አየር መንገድ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጨማሪም፣ በናይጄሪያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ላይ አባሪ ክስ መስርቷል፡፡
አሪክ የተሰኘው ይኸው አየር መንገድ በክስ ማመልከቻው ላይ፣ ‹‹የናይጄሪያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ከእውቅናዬ እና ፈቃዴ ውጭ፣ ከጀርባዬ ዞሮ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ድርድር ጀምሯል፡፡›› ብሏል፡፡ ሁለቱ አካላት እያካሔዱ ያሉትን ድርድር የናይይጄሪያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በአስቸኳይ እንዲያስቆም የጠየቀው አሪክ አየር መንገድ፣ የናይጄሪያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ ድርጊት ውስጥ መሳተፉን ገልጿል፡፡
ከዚህ ቀደም አምኮን የተባለ ድርጅት የናይጄሪያ አየር መንገድን ማኔጅመንት ተረክቦ እንዲያስተዳድር ውሳኔ መተላለፉን ያስታወሰው አሪክ አየር መንገድ፣ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ክርክር እየተደረገበት ባለበት በዚህ ወቅት፣ የናይጄሪያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ድርድር ጀምረናል ማለታቸው በስራው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳሳደረበትም ተናግሯል-አሪክ አየር መንገድ፡፡ አፍሪካን ፕሬስ ኤጀንሲ እንደዘገበው ከሆነ፣ የናይጄሪያው አየር መንገድ በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በናይጄሪያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር መካከል ተጀመረ የተባለውን ድርድር ፍርድ ቤቱ እንዲያስቆምለት ጥያቄ አቅርቧል፡፡
‹‹የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስራዬ ጣልቃ ገብቷል፡፡›› ሲል ክሱን ወደ ፍርድ ቤት ይዞ የሔደው የናይጄሪያው አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የናይጄሪያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ፈጸሙብኝ ላለው ሴራ እና ደረሰብኝ ላለው የሞራል ኪሳራ 56 ሚሊዬን ዶላር እንዲከፈለው ጥያቄ አቅርቧል ሲል አፍሪካን ፕሬስ ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡ ክሱ የቀረበለት የናይጄሪያው ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ በጉዳዩ ላይ ምን ዓይነት ብይን እንደሰጠ አልያም ጉዳዩ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም፡፡■ Subscribe to mereja.com's email newsletter. ⇒ CLICK HERE እዚህ ላይ ይጫኑ ⇐

► Post your comment below
የአንባቢያን አስተያየቶች

  1. You made money and destroyed people’s physical and facial appearance. What you saying now. It is a disrespect and stressful life you couse to human structure.

Leave a Reply

Please answer this math question before submitting your comment: