የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) በግብር ጭማሪው ላይ ከንግዱ ማህበረሠብ ለተነሳው ቅሬታና ተቃውሞ እንዲሁም በክልሎች መካከል ለሚነሱት ግጭቶች ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠየቀ። (መግለጫውን ይዘናል )

ቆንጂት ስጦታው

በግብር ጭማሪው ላይ ቅሬታና ተቃውሞ ለሚያሰሙ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የሚሰጠው መንግሥታዊ ምላሽና የጉዳዩ አያያዝ ሰብዓዊና የዜግነት መብቶቻቸውን የጠበቀ ሊሆን ይገባል፤

በክልሎች መካከል ለግጭት መንስኤ የሚሆኑ ጉዳዮች በአስቸኳይ እልባት ይሰጣቸው!!

የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) በግብር ጭማሪው ላይ ከንግዱ ማህበረሠብ ለተነሳው ቅሬታና ተቃውሞ እንዲሁም በክልሎች መካከል ለሚነሱት ግጭቶች ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠየቀ። ሰመጉ ጳጉሜ 04 ቀን 2009 ዓም ይፋ ባደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ‹‹አማካይ የቀን ገቢ ግምት›› በማለት በንግድ ማህበረሰቡ ላይ የጣለውን የግብር መጠን ተከትሎ ከንግድ ማህበረሰቡ የገቢ ግምትና የግብር አወሳሰኑ የቀን ገቢያችንን ያገናዘበ አይደለም፣ እጅግ የተጋነነ ነው በማለት ከፍተኛ ቅሬታ በአዲስ አበባ ከተማና በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞችና አካባቢዎች ያቀረበው ተቃውሞና አቤቱታ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን፤ ችግሩን ለመፍታት የመንግስት አካላት በንግዱ ማህበረሰብ ላይ የሚፈፅሙት ዛቻ፣ ማስፈራራት፣ የሱቅ ማሸግ፣ የተሽከርካሪ ሠሌዳ መፍታት እና ሕገ ወጥ እስር ሕገመንግስቱን የሚፃረር መሆኑን ሰመጉ ገልጿል።

በመግለጫው ሁለተኛ ክፍልም በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ከማንነት፣ ከአስተዳደርና ከድንበር ይገባኛል ጥያቄ ጋር በተያያዘ ግጭት እየተቀሰቀሰ እንደሆነ፤ በአንዳንድ አካባቢዎችም ውሎ አድሮ ሊቀሰቀስ እንደሚችል ስጋቱ የገለፀ ሲሆን፤ መንግስት ከሕብረተሰቡ ጋር በመመካከር አስቸኳይና ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጥ ሰመጉ ጥሪውን አቅርቧል።

https://ehrco.org/wp-content/uploads/2017/09/HRCO-Press-Release-September-09-2017-1.pdf

የአንባቢያን አስተያየቶች

 1. ሳምሶን ነኝ says:

  መብት ስለሆነ ድርጅታችሁ ለምን ተመስረት ለማለት አይዳዳንም ! የሚጠቅም ከሆነ መብታችሁ ነው ! ግን ለኛ የፈየደው ነገር የለም ከሞት ከርሸናና ከእስርና ክስድት አላስጣለንም አላዳነንም: ስለዚ መፍቴው ትግላችንን ማጠናካርና ገዳያችንን ታግለን በመጣል: ነፍሳችንን ማትረፍ ነው !!

 2. ሜሮን ነኝ says:

  ስብአዊ መብት ብሎ ነገር የለም ! መብትና ነፃነት ባልተከበረባት ሀገራችን ነፃ ሆኖ የሚስራ የለም ! ሁሉም ከወጪና ከገዢው ብር ለማግኘት ብቻም ሳይሆን: በአለም አንዳንድ አካባቢዎችና በመካከለኛው የአረብ ሀገራት ስብዓዊ መብትና ዶሞክራሲ ምን እንደሆነና ለጉልበተኞ መጠቀሚያ መዋሉን በአለም ሕዝቦች ግንዛቤ በማግኘት ጥያቆ ምልክት ውስጥ የገባ መነጋገሪያ ነው: እኛም በጠመንጃ በጉልበት የምንገዛ በመሆናችን የኛንም ሀገር ከነዚያ ለይቼ አላየውም ምክንያቱም በ26 ዓመታት ውስጥ ወያኔ በዓለም ያልተደረገ ግፍና መከራ ሲፈፀምብን: እናተም ሆናችሁ ፍርጅቱ ወያኔን ከግድያው አላቆሙልንም አላተረፋችሁንም: እናም ጥያቄ ምልክታችን እንዳለ ነው ! የተያያዝነው ትግል የመሽፋፈን ሳይሆን የእውነት ነው !! እየ ጠራ መሄዱ ለህዝቦች ትግል ጠቀሜታ አለው !!

 3. ገረመው says:

  ህወሃቶች እንኩዋን አገር ለማስተዳደር ይቅርና ለከፍት እርኝነት የሚበቃ ስብዕና የላቸውም ፡ ይታያችሁ ለሽ አመታት ፀንታ የኖረች አገር በ20 አመት ውስጥ እነኝህ ተውሳኮች ያፈራርሱዋት ጀመር ፡
  ዘራፍ ወያኔ ዘራፍ ፡ ሰማንያ ጎሳ አናቁዋሪ ፡ አንዱን ጎሳ ከአንዱ አደባዳቢ ፡ ዘራፍ ወያኔ የባንዶቹ ልጅ ኢትዮጵያን አፍራሽ የጣልያን ቡችላ እያለች እየፎከረች ነው ።

Leave a Reply

Please answer this math question before submitting your comment: