የኦሮሞ ህዝብ ላይ የዘመተው ማን ነው? (በጌታቸው ሺፈራው)

የኦሮሞ ህዝብ ላይ የዘመተው ማን ነው?

(በጌታቸው ሺፈራው)

በኦሮሚያና ሶማሊ ክልል አካባቢ “የሶማሊ ክልል ልዩ ሀይል” የሚባል ንፁሃን ኦሮሞዎች ላይ ሲዘምንት እንደሰነበተ ኦህዴድም በግልፅ መናገር ጀምሯል። አብዲ የሚባለው የሶማሊ ክልል ሹም ካለው ስብእና እና የትህነግ ወኪልነቱ አንፃር ኦሮሚያ ውስጥ የቀጠለው ህዝባዊ እምብይተኝነት አቅጣጫ ለማስቀየር በተልዕኮ እየፈፀመው ያለ በህዝብ ላይ የተከፈተ ጦርነት ስለመሆኑ ግልፅ እየሆነ ነው። ነገር ግን ከአብዲ በተጨማሪ የሌላ አካል እጅም እንዳለበት የሶማሊያ ጦር አባል መሳተፉን የሚያሳይ ወረጃ ተገኝቷል። የሶማሊ ክልል ኮሚኒኬሽንና የኦሮሞያ ክልል ኮሚኒኬሽን ስለዚህ የአህሉሱና ዋልጀማ አባል ነው በተባለ ወታደር ጉዳይ ቪኦኤ ላይ ተከራክረዋል። የኦሮሚያ ክልለኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊው የሶማሊያ ወታደር መሳተፉን ገልፀው ተከራክረዋል። ለመሆኑ አህሉሱና ማን ነው? የሚዋጋው ለማን ነው?

አህሉሱና ዋልጀማ የሱፊ እምነትን መሰረት ያደረገ ቡድን ነው። ሶማሊያ ውስጥ የጎላ ታሪክ ባይኖረውም የዚያድባሬ መንግስት ከወደቀ በሁዋላ የተነሱ ” ፅንፈኛ ቡድኖች” ጋር ሲዋጋ እና በዚህ አቋሙ ምክንያት ከጎረቤት ሀገራት ጋር መልካም ግንኙነት የመሰረተ ቡድን ነው። ከሶማሊያ ጎረቤት ሀገራት መንግስታት መካከል ከዚህ ቡድን ጋር መልካም ግንኙነት ያለው የትህነግ/ ኢህአዴግ “መንግስት”ነው። ትህነግ እስካሁን ሶማሊያ ውስጥ አህሉሱናን የሚያክል እምነት የሚጥልበት ቡድን አላገኘም። ትህነግ ይህን ቡድን ለዘብተኛ ነው ብሎ በማመን እገዛ ሲያደርግለት የቆየ ሲሆን አህሉሱና ትህነግ/ ኢህአዴግ ሶማሊያ ድረስ ጦር የላከባቸውን ቡድኖች ሁሉ ሲዋጋ ቆይቷል። ትህነግ/ ኢህአዴግ በይፋ ወደ ሶማሊያ ጦር የላከው አሊትሃድ አል እስላሚያን ለመውጋት ነው። አህሊሱና ዋል ጃማ ሶማሊያ ውስጥ ከአሊትሃድ ጋር ሲዋጉ ከነበሩ ቡድኖች መካከል አንዱ ነው። ትህነግ/ ኢህአዴግን በቅርብ ረዳትነት አስቀምጠው ምዕራባዊያኑ የመሰረቱት የሽግግር መንግስትን ጨምሮ ሶማሊያ ውስጥ የተመሰረቱ ድርጅቶች መሰረታቸው ውሃብያ እስልምና ነው። ይህን እስልምና ትህነግና ምዕራባዊያኑ በፅንፈኝነት ስለፈረጁት በውክልና ጦርነት ተዘፍቀው ቆይተዋል። ምዕራባዊያኑ ትህነግን ወኪል ሲያደርጉ ትህነግ በበኩሉ እዛው ሶማሊያ ውስጥ የበቀሉ እንደ አህሉሱና ያሉትን ቡድኖች ወኪል አድርጎ ሲሰራ ቆይቷል።

በተለያዩ ጊዜያት ሶማሊያ ውስጥ የሽግግር መንግስት ሲመሰረት አህሉሱና ዋልጀማ የሽግግር መንግስቱ አካል እንዲሆን ተደርጓል። ይህ ሲሆን የትህነግን ሚና ቀላል ነው ማለት አይቻልም። የሽግግር መንግስት በሚመሰረትበት ወቅት ከአልሻባብና ከሌሎች ከአህሉሱና በተቃራኒ የቆሙ ቡድኖች “አቋም ቀይረናል” እያሉ ወንበር ተሰጥቷቸዋል። እንደ አልሻባብ ያሉ ቡድኖች ቅርበት ያላቸው የማህበረሰብ መሪዎች ተካተዋል። በዚህም ምክንያት የሽግግር መንግስቱ ከጥጉ ሆኖ ከሚጠብቀው ትህነግ/ ኢህአዴግ ጋር አለመተማመን ውስጥ የገባባቸው ጊዜያት ነበሩ። ይህ ሲሆን ግን አህሊሱና ከትህነግ የሚያቀራርበውን አቋም ሲያራምድ እንዲየውም ትህነግ በጥርጣሬ የሚያያቸውን የሽግግሩ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ” አክራሪዎች” በሚል ፈርጆ ከሽግግሩ ለመውጣት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ትህነግን የሚጠረጥራቸው የሽግግር መንግስቱ ፖለቲከኞች ጋር የለየለት ውዝግብ ውስጥ ገብቷል።

ምንም እንኳ ትህነግ ከሸሪያ ህብረት፣ ከዛም በሁዋላ አልሻባብ እና ሂዝቡል እስላም ወጥተው “የሽግግር መንግስት” ውስጥ የሚገቡት ላይ እምነት ባይኖረውም አልሻባብን የመሰሉ ቡድኖች ለማዳከም፣ በምዕራባዉያኑ ውሳኔና በአረብ ሀገራት ረዥም እጅ ራሱ ትህነግ/ ኢህአዴግ “ጀሃድ አውጀውብኛል” ብሎ ወደ ሶማሊያ ጦር እንዲልክ ምክንያት ያደረጋቸው ግለሰቦች የሽግግር መንግስት አካል ሲሆኑ ምንም ማድረግ አልቻለም። በሁዋላ ከእነዚህ ግለሰቦች ጋር ግጭት ውስጥ የገቡትን አህሉሱና አይነት ቡድን ድጋፍ ከመስጠት ውጭ።

አህሉሱና የእስልምና እምነት አይነት ሳወዲና መሰሎቿ ከሚደግፉት እንዲሁም አብዛኛው የሶማሊያ ህዝብ ከሚያምነው ውጭ በመሆኑ ይህ ቡድን እንደተፈለገው ሊጠናከር አልቻለም። ሆኖም ባለፉት 10 አመታት ለምዕራባዊኑ ጠንካራ የሶማሊያ ወኪል ለነበረው ትህነግ ጥሩ መንገድ መሪና በአቅሙም ወኪል ሆኖ አገልግሏል። ትህነግ/ ኢህአዴግ ከተዋጋቸው አሊትሃድ፣ አልሻባብና ሂዝቡል ኢስላም ጋር ብቻ ሳይሆን ከኦብነግም ጋር የተዋጋ ቡድን ነው። አህሉሱና ዋልጀማ ትህነግ የገጠመውን ሲገጥም፣ የጠላው ጋር ሲጣለ የቆየ በሚቆጣጠረው መሬት፣ የህዝብ ተቀባይነትና አደረጃጀትም ደካማ እና አናሳ ቡድን ነው። አብዛኛው ህዝብ ሱኒ አማኝ በሆነበት ሶማሊያ የተለየ እምነት ይዞ ስልጣን ለመውጣት የውጭ ሀገራትን ይሁንታ የሚፈልግ የትህነግ ወኪል ነው።

አህሉሱና ዋልጀማ ለትህነግ ወኪል ብቻ አይደለም። ትህነግ ይህን አናሳ ቡድን ሞዴልም ጭምር አድርጎ ተጠቅሞበታል። ትህነግ/ ኢህአዴግ በ ካድሬ ስልጣና መልክ የሚሰጠው እና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ ለመጫን እየጣረ ያለው ” አህበሽ” የሚባል እምነት የአህሉሱ እንደ ቡድን የሚከተለውና መንግስት ቢሆን አስፋፋዋለሁ የሚለው የ እምነት ነው። አህሉ ሱናን ምን አልባትም እንደ መንግስት እውቅና የሰጠው የትህነግ/ ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት ነው። ከእሱ በሁዋላ የኖወይ መንግስት እውቅና ሰጥተው ግንኙነት መስርቶ እንደነበር መረጃዎች አሉ። የትህነግን ያክል ግን ከአህሉሱና ጋር ግንኙነት ያለው የለም።

ለትህነግም የአህሉሱናን ያህል ታማኝ፣ ትህነግ የሚወጋቸው አልሻባብ፣ ሂዝቡል እስላምና እና ኦብነግ ጋር የተዋጋ የሶማሊያ ቡድን የለም። በግልፅ ከትህነግ ጋር ግንኙነት ያለው የሽግግሩም ሆነ የአሁኑ መንግስት የአህሉሱናን ያህል ታማኞች አይደሉም። የኦብነግ ከፍተኛ አመራር ተላልፎ ሲሰጥ ደስተኛ ያልሆኑ የሶማሊያ መንግስት አመራሮች እንዳሉ ከመታወቃቸው በተጨማሪ የሽግግሩም ሆነ የአሁኑ መንግስት ውስጥ ያሉ የትህነግ ጥቂት ታማኞች ካልሆኑ በስተቀር እንደ ቡድን ወይም መንግስት ኦብነግ ሞቃዲሾ ውስጥ ሲንቀሰቀስ ቢያንስ እንዳላዩ የሚያልፉ፣ ከዚህ ገፋ ሲል የሚደግፉ ናቸው። አህሉሱና ግን ከኦብነግ ጋር ጦርነት የገጠመባቸው ጊዜያትም አሉ። ለትህነግ ታማኝ በመሆኑ።

የአብዲ ” ልዩ ሀይል” ተሳተፈበት በተባለው ጦርነት የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር መታወቂያ ያለው እና በተለያዩ ጊዜያት መንግስት ሲቋቋም የትህነግ/ ኢህአዴግ ድጋፍ ሳይለየው ወንበር የሚሰጠው የአህሉሱና አባል መሆኑ ተነግሯል። በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ያለው እንቅስቃሴ ለመንበሩ አደጋ መሆኑን የተረዳው ትህነግ/ ኢህአዴግ የህዝብን አቅጣጫ ለማስቀየር በሶማሊ ክልሉ ወኪሉ እንዲሁም ሶማሊያ ውስጥ ትህነግ የጠላውን በአቅሙ ሲዋጋ የኖረው በሶማሊያው ወኪሉ በአህሉ ሱና ዋልጀማ በኩል ኦሮሚያ ውስጥ ጦርነት እንደከፈተ ግልፅ ነው። ይህ የሶማሊያ ብሄራዊ ወታደር መለያ የያዘ ግለሰብ ጉዳይ ከተሰማ በሁዋላ “የታላቋ ሶማሊያ” አጀንዳም ተነስቷል። ሆኖም ወታደሩ አባል ነው ከተባለለት አህሉሱና ዋልጃማ በላይ ከእሱ ጋር የሚጋጩት የሶማሊያ መንግስት ባለስልጣናት ለዚህ አጀንዳ ቅድሚያ የሚሰጡናቸው። በመሆኑም ይህ ጦርነት ከታላቋ ሶማሊያ አጀንዳ በላይ የትህነግ የበላይነት፣ ህዝብን በቅጥረኛ፣ በውስጥና የውጭ ወኪል አስገድሎ፣ አቅጣጫ አስቀይሮ የመግዛት ፕሮጀክት አካል ነው። በመሆኑም የኦሮሞ ህዝብ ላይ የዘመተው ትህነግ እንጅ ሌላ አካል አይደለም። ሶማሊ ክልልና ሶማሊያ ባሉት ወኪሎቹ በኩል!

የአንባቢያን አስተያየቶች

 1. አቡሽ ነኝ says:

  የዘመተበት ማ ! የትናንት ሽሪኩ የዛሬው ጠላቱ ሱማሌ ነዋ ! ያው ከማይተማመን ጉዋደኛ ጋር እንደሚባለው አይንት መሆኑ ነዋ ! አቶ ሌንጮ ለታ ኮትኩቶ ውኃ አጠጥቶ ያሳደገው ቃሪያ ( በሽግግሩ ወቅት ያረቀቀውን አንቀፅና ስነዱን ) ማለቴ ነው: መልሶ እራሳቸውን እያቃጠላቸው መሆኑን ከኛ ይልቅ እርቃቂው በደንብ ስለሚረዳ: ለአቶሌንጮ ለታ ፅናቱንና ብርታቱን ይስጥህ እላለሁ !

 2. Demse says:

  The Ethiopian people freedom struggle has been continuing, weyane on its side trying hard to deverse the direction of our great effort. The Somile region police has been killing innocent people, comitting crime against the Oromos. what has been going on between the Ethiopian Somalies and oromos is the dirty hand work of the tplf. Keep in mind, things are going to be out of coutrol of weyane.we, therefore, must push forword to remove them once and for all. As the adage goes ” nothing is impossible”. History teaches: Even the Nazi which was well organized, rich in material wealth,had well educated manpower, full of proffisationals defeted once and for all, not alone tplf which is a banch of sheepers.
  The fight shall continue to eredicate weyane(evile) once and for all from the surface of the earth.Ethiopia shall be free and be the land of truth, peace and prosperity where each and every one of us can live in equivalence.

 3. bos says:

  olf fascist thugs have been working in collaboration with tigre people liberation front since 1991 when they were crowed by america and england to take over Meneliks palace. the current chaos , massacre and displacements of people is the result of the policy these two fascist groups designed to divide Ethiopians along ethnic , tribal and clan lines.
  we are now paying heavy prices for the ethno fascsit agenda these groups prepared for us. ethnic group against ethnic group is rising all over Ethiopia, racial and ethnic hatred and violence is being stirred up deliberately, and people who lived as neighbours for generations are being brainwashed to see each other as enemies.

  the current killing is in thr region of Eastern Ethiopia is being seen as oromo against ogaden. this is the picture tplf and olf fascists want us to see. this is the impression they want to create. the truth is that these two groups are the cause of the violence and deaths. they want one group to annihilate the other so that there wont be peace between the people. creating chaos is the job of tplf thugs. they only survive by doing so.

  there is no animosity between ordinary oromo and ordinary ogaden people. the current crisis is man made , manufactured by tplf and olf. people should not be fooled by tplf and olf delusions. they should be able to see what is going on behind the scenes and focus on the real enemies of the Ethiopian people.

 4. waw says:

  ሕወሃት ነው!
  አራት ነጥብ።

  ወይስ ወታደር ተርፎት ፡ እያንዳንዱን ወታደር ለአሜሪካ በዶላር አከርይቶ ፥ ሱማሌ የላከው ሕወሃት ፥ የኦሮሞ ህዝብን ሕይወት የሚታደግ የሚመስለው ጅል ዛሬም ይኖር ይሆን?

  በእርግጥ ሕወሃት ክፍያውን በዶላር ማግኘት ከቻለ ፥ በአሽከርነት የቀጠራቸውን ወታደሮች ፡ አትግደሉ ብሎ ትዕዛዝ ሊያስተላልፍ ይችላል!

 5. Kaleb says:

  Yes, that is exactly right! It is a proxy war being waged by Weyane against the peoples of Oromo. I always laugh when other people characterise it as war by ethio somalis.

  Weyane is using a slightly different approach in the Amhara region – divide and conquer by pitting Amharas against other tribes within the region. As we all know, the Amhara and Oromo regions have been resisting tigre weyane since recently and they are in fact credible threats to the survival of the Tigre regime. So, weyane is fighting to to kill this threat. I can tell you that it will not succeed. I am not a fortune teller, but I can tell you that Tigre weyane will not survive thus time around. The resistance will get more momentum and the regime will fall in few years. Oromos were the source of weyane strength, but this is now changing slowly but surely.

  • Tesso says:

   Savage Sebehat Nega 87 years old
   Abay Tshay 76 years old
   Seyoum Mesfin 73 years old
   Fake doctor Debretsion 67 years old
   Fake Doctor Arkebe equbay 65 years old

   and all bunch of Tigre criminals for 43 years are stinky old, blood drinkers and flesh eaters.

   They will be gone soon.

 6. ዕቡይ ስብሃት says:

  አዎ የ’ኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል’ ፕሬዘዳንት ተብየው መሃይም አብዲ እኮ የትህነግ ዋና አጋር ተላላኪ መሆኑን በቃላትም ሆነ በምግባር ሲገልፅና ሲያስመሰክር የቆየ ነው:: የወያኔ የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ የእርሱም እንደሚሆን የተገነዘበ በመሆኑ ከዚህም በላይ ርቆ መሄድ የሚችል ወደል አህያ መሆኑን ከወዲሁ ተገንዝቦ ዕርምጃወችን ማስተካከል ብልህነት ነው::

 7. hunan says:

  “ይህ ጦርነት ከታላቋ ሶማሊያ አጀንዳ በላይ የትህነግ የበላይነት፣ ህዝብን በቅጥረኛ፣ በውስጥና የውጭ ወኪል አስገድሎ፣ አቅጣጫ አስቀይሮ የመግዛት ፕሮጀክት አካል ነው። በመሆኑም የኦሮሞ ህዝብ ላይ የዘመተው ትህነግ እንጅ ሌላ አካል አይደለም። ሶማሊ ክልልና ሶማሊያ ባሉት ወኪሎቹ በኩል!”

  የትህነግ = የትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር ወይም ህወሀት= ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ

Leave a Reply

Please answer this math question before submitting your comment: