የፕሮፍ 60 ዓመታትን የተሻገረ ምጥ — አስማማው ሀይለጊዮርጊስ 

የፕሮፍ 60 ዓመታትን የተሻገረ ምጥ

አስማማው ሀይለጊዮርጊስ

‹‹እንዘጭ-እንቦጭ የኢትዮጵያ ጉዞ›› በሚል ርዕስ ለንባብ የበቃውን የመስፍን ወልደማሪያም (ፕ/ር) መፃፍ ምረቃ መነሻ በማድረግ ባሳለፍነው ቅዳሜ በኬምብሪጅ የተዘጋጀው ፕሮግራም ይህን ሐሳብ ለመወርወር መነሻ ሆነኝ፡፡ በዚህ ፕሮግራም ላይ በቦስተን እና አካባቢው የሚገኙ የፕሮፌሰሩ አድናቂዎች፣ ሀሳባቸውን ለመሟገት የመረጡ የአገራችን ሰዎች፣ የተገኙ ሲሆን ሰማኸኝ ጋሹ (ዶ/ር) – የሰብዓዊ መብትና የዓለም አቀፍ ሕግ አስተማሪና ተመራማሪ፣ አቶ ገለታው ዘለቀ – የኢትዮጵያ ሪሰርችና ፖሊሲ ተቋም ጸሀፊ፣ የህግ ተመራማሪው እና ጦማሪው ዘላለም ክብረት (በሃርቫርድ ዩንቨርስቲ ሀትቺንስ ማዕከል ፌሎው) በመፅሐፉ ዙሪያ ያላቸውን አጭር አስተያየት በእለቱ አቅርበዋል፡፡ ከዚህ ውጪም ከቦስተን ውጪም እንደ ደረሰ ጌታቸው (ዶ/ር) – የአርበን ሶስዮሎጂ አስተማሪና ተመራማሪ ያሉትም ከኒው ዮርክ በመምጣት ተሳትፈውበታል፡፡ በአደባባይ ምሁርነታቸው፣ በሰብኣዊ መብት ተሟጋችነታቸው፣ በፖለቲካዊ እና ማሕበራዊ አቋማቸው ፕሮፍ የብዙ ሰዎች ምሬትን፣ የሶስት ሥርዓት ተግሳፅን ሆነ እስርን ተቋቁመው በደረሰባቸው ያልተገባ ቅጣት ሳይመረሩ የልባቸውን ያለፍርሃት እየተናገሩ፤ ላመኑበት ነገር በፅናት በመቆም አስፈላጊ ሲመስላቸውም ብዙዎች አንድ የሆኑበትን ሐሳብ ሳይቀር ብቻቸውን ሚያስቀር ቢመስል እንኳ ሐሳባቸውን ለማንጸባረቅ ወደ ኋላ ባለማለት (ለዚህ ምሳሌ ብዙዎች የሚያውቁት በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጊዜ ኤርትራውያን ከአገር እንዲባረሩ ሲደረግ እርሳቸው ይህን የመንግስት ውሳኔ በመቃወም በአደባባይ ይህን አቋማቸውንም በመግለፁ ብቻ ሳይገቱ ያልተገባ ባሉት የመንግስት ውሳኔ ኤርትራውያን ከቤት ንብረታቸው እንዳይፈናቀሉ የሚችሉትን ሁሉ በተግባር ያደረጉ ናቸው፡፡ የዚህን ጉዳይ ዝርዝር ወደፊት ራሳቸው ያስነብቡን ይሆናል፡፡)

ከ85 ዓመታቸው በኋላ ብዙዎች ምን ያደርጉ ይሆን? የሚለውን መጠየቁ ለፕሮፍ ለማይዝለው ብእራቸው አድናቆትን ለመቸር እንድንነሳሳ ይገፋፋል፤ ከዚህ ውጪ ግን ዛሬም ሐሳባቸውን ለሚሞግት እሳቸው “እንዴት ተነካሁ?” ባይነት አይዳዳቸውም፣ ደርግ ሥልጣኑን እንደተቆናጠጠ ለሚሰጡት የተለየ ሐሳብ ሹማምንቱ ‹‹ሽማግሌው›› እያሉ ሐሳባቸውን ከመቀበል ወደኋላ ይሉ የነበር ሲሆን አሁን ላይ ከ40 ዓመታት በኋላም ይበጃል ያሉትን ሐሳብ ከማጋራት አልተገቱም፡፡ በመጻህፋቸው ምረቃ ወቅት ባቀረቡት ማብራሪያ ‹‹ ከልጅነቴ ጀምሮ የነበረኝ ፍላጎት በኢትዮጵያ የቤተ ክህነት ትምህርት ለመግፋትና ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን በጥልቀት ለማጥናት ነበር፤ ነገር ግን ከእኔ ቁጥጥር ውጭ በሆኑ ምክንያቶች የልጅነት ምኞቴ ሳይሳካልኝ ቀረ፤ የቤተ ክህነቱን ትቼ ተፈሪ መኮንን ተማሪ ቤት ገባሁ፤ ከዚያም ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ሲከፈት ከመጀመሪያዎቹ ተማሪዎች አንዱ ሆንሁ፤ በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለአንድ ዓመት ያህል ቆይቼ በእቴጌ መነን ትምህርት ቤት አስተማሪ ሆንሁ፤ ከዲሬክተርዋ ከወይዘሮ ስንዱ ጋር ተጋጨንና ከእተጌ መነን ወጣሁ፤›› መጋጨት ልማዴ ነው መሰል ብለው ፈገግ አስብለውናል፡፡ በተለይ ከዚህ በኋላ ፕሮፍ አጋጣሚ ሆኖ ወደህንድ ለትምህርት መሄዳቸው ራሳቸውን ለማወቅ የቻልበት ሁኔታን ስለመፍጠሩም ያወሳሉ፡፡

‹‹ በህንድ አገር የመጀመሪያውን ሌላ አገር አየሁ፤ ህንድ ከሁለት መቶ በላይ ቋንቋዎች የሚነገሩበትና ከነዚህም ሃያ ሁለት የሚሆኑት የየራሳቸው ፊደል ያላቸው መሆናቸውን ስረዳ የእኔን አገር ትንሽነት ገለጠልኝ፤ ነገር ግን የህንድ ሕዝብ ከአሥራ ሦስተኛው ምዕተ-ዓመት አስከአሥራ ስምንተኛው ምዕተ-ዓመት በተለያዩ የእስልምና ኃይሎች ስር ወድቀው ከቆዩ በኋላ ከአሥራ ስምንተኛው ምዕተ-ዓመት በኋላ ደግሞ እአአ አስከ1 947 የብሪታንያ ቅኝ ግዛት ሆነው ቆዩ፤ በአንጻሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሌም በነጻነት በመኖሩ ልቤ ኮራ፡፡›› ይሉናል፡፡ ኩራታቸው ግን እንዳለ አልቆየም፡፡ ቀስ እያለ የተፈጠረባቸውን ስሜት እንዲህ ይገልፁታል፡፡ ‹‹እየቆየሁ፣ እያደግሁና ብዙ ነገሮችን እየተገነዘብሁ ስሄድ የኢትዮጵያዊነት ኩራቴ በደሀነት ብል እየተበላ ተናደብኝ፤ በዚህ ጊዜ በአንድ በኩል በታሪካዊ ኩራት፣ በሌላ በኩል ደግሞ በኑሮ ደሀነት ተወጥሬ የተያዝኩበት ሀሳብ የኢትዮጵያን ሕዝብ ምን ይዞት ነው በሥልጣንና በሀብት ድልድል ለማደግና ለመሻሻል ያልቻለው? የሚል ጥያቄ ነበር፤ ይህ ጥያቄ አእምሮዬን ቀስፎ ይዞት ኩራቴ ወደ ቁጪት ተለወጠ፤ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማወቅ በትሬንታ ኳትሮ፣ በባቡር፣ በእግሬና በበቅሎ፣ በላንድሮቨር ተራራውን ስወጣ፣ ቁልቁለቱን ስወርድ ሁሌም የሚነዳኝ ይህ ጥያቄና ቁጪቱ ነበር፡፡›› ይህ ቁጭት በተለይ ወደ ብስጭት እንዲያመሩ ያደረጋቸው ሲሆን ዩኒቨርሲቲም በሚስተምሩበት ጊዜ ኢትዮጵያ ወደኋላ መቅረትዋ ብቻ ሳይሆን ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብም ወደኋላ መቅረት የተመቸው እየመሰለኝ እበሳጭ ነበር፤ አሁንም ያበሳጨኛል፡፡›› ሲሉ ከወጣትነት እስከ አዛውንትነት ዕድሜያቸው ከውስጣቸው ያልተለየውን በወገናቸው ተቆርቋሪነት ያደረባቸውን ስሜታቸውን ይናገራሉ፡፡

ከልጃቸው መቅደስ (ዶ/ር) ጋር እኔና ዘላለም ልንጠይቃቸው በሄድንበት ወቅት ከዘመን አቻቸው በእጅጉ የተለየ የሚያደርጋቸው ትጋት ሳይለያቸው፤ ላፕቶፓቸው ላይ የአጋሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በማህበራዊ ሚዲያ እየተከታተሉ፣ አለኝ ያሉትንም ሐሳብ (ሶስት አስርተ አመታት ያለፈው የጡረታ ዘመናቸው ሳይገድባቸው) እየወረወሩ ነበር፡፡ በዚህ የእረፍት ዘመናቸው የጤናቸው ሁኔታ ከፍተኛ እንክብካቤን እና እረፍት የሚሻ ሆኖም ሳለ ከማህበራዊ ሚዲያውም ተሳትፎዋቸው ባለፈ ይህንኑ መፅሐፍ ለማዘጋጀት መንስኤ የሆናቸውን ነገር ሲያወሱም ‹‹ጡረታ ከወጣሁ ሠላሳ ሁለት ዓመቶች ያለፉ መሰለኝ፤ ያም ሆኖ፣ በጡረታ ላይ ሆኜም በወጣትነቴ በውስጤ የተፈጠረው ጥያቄ አልለቀቀኝም፤ ይኸ ጽሑፍ የዚህ ውጤት ነው፤ የመጽሐፉ ዋና ይዘት ከብዙ ዘመናት በኋላ ከዚህ ጥያቄ የተወለደ ግኝት ነው፤ በከባድ ምጥና ጭንቀት የተወለደ ሀሳብ ነው፤ አሁን በአለሁበት ሁኔታ ሀሳቡን ለማሰራጨት አይመችም፤ አስተማሪ ብሆን በውድም ሆነ በግድ ተማሪዎቼን እንደአብሽ እግታቸው ነበር፤ አሁን በአለንበት ሁኔታ ግን ሰፊና ነጻ የውይይት መድረክ ባለመኖሩ ሀሳቡ ፋይዳ ያለው እርምጃ ይኖረዋል ብዬ አላምንም፤ ሆኖም ትንሽም ቢሆን በመኮርኮር ለማንቃት ከተቻለ እንሞክር፡፡›› ከሚል ሐሳብ በመነሳት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

‹‹እንዘጭ-እንቦጭ የኢትዮጵያ ጉዞ›› በሚል ርዕስ ያሳተሙት ዳጎስ ያለ መፅሐፍ ያዘጋጁበትን ምክንያት ሲገልፁ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ ለብዙ የማኅበረሰባዊ ጥናቶች፣ በጂኦግራፊና በታሪክ፣ በማኅበረሰብ ጥናት፤ በሥልጣንና በኑሮ ዝርዝር ጠቃሚ ጥናት ሊካሄድበት የሚችል ርእስ መሆኑን በማውሳት ነው፡፡ አንደ እናት ከ9 ወር በኋላ እርግዝና ልጇን ባስቸጋሪ ምጥ እንደምትወልደው ሁላ ፕሮፍም ከወጣትነታቸው ጊዜ አንስቶ ከአእምሮዋቸው ሲብላላ የነበረውን ጥያቄ እና ቁጭት መሰረት በማድረግ ከረጅም ጊዜ ምጥ በኋላ መፅሐፍን ስለመሰናዳቱ በአጭሩ ያወሱት ‹‹ የአንድ ሰው የረጅም ጊዜ ምጥና ጭንቀት ነው፤›› በማለት ነበር፡፡

በዚህ መፀሃፋው ፕሮፍ በምልዓት ከ’አድዋ1888’ ተነስተው፣ በ’ማይጨው 1928’ የተከሰተውን አውስተው፣ በጂጂጋ 1968 የተከወነውን ነገር እያወሳሱ አሁን ያለንበት ጊዜ ላይ ያለውን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ታሪካዊና ሌሎችንም ኩነቶች በስፋት ይዳስሳሉ፡፡ በተለይ አንባገነናዊ ሥርኣቶች ላይ ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ሂስን በስፋት ህረተሰቡን መሰረት አድርገው ጭምር ዝርዝር ትንታኔ አቅርበዋል፡፡ በዚህ ረገድ ከወትሮው በተለየ የሚያስብል በስፋት የዳሰሱት ማድፈጥ ሲሉ የሚገልፁትን ሐሳብ ነው፡፡ ይህንን ርዕሰ ጉዳይ በተመለከተም እርሳቸው የመጽሐፉ እንቡጥ ሀሳብ <<ማድፈጥ>> ስለመሆኑ አውስተዋል፡፡ ‹‹ ማድፈጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ ያለው የኃይሉም፣ የድካሙም መግለጫ ነው፤ የድካሙ መግለጫ እንደመሆኑ ጥቃት ይፈጸምበታል፤ የኃይሉ መግለጫ እንደመሆኑ ዕድሉን ጠብቆ በቀሉን ይወጣበታል፤.. ማድፈጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ በግፍ አገዛዝ ላይ የሚፈጽመው እስከዛሬ ያልታወቀ የበቀል ዘዴ ነው፤ምርጫ ሲያሳጡት ሕዝቡ የሚወስደው የራሱ ምርጫ ነው፤›› በማለት የሚገልጹትን ሐሳብ መነሻ በማድረግ ፕሮፍ በዚህ መጽሀፋቸው ማድፈጥ ምንድን ነው?፤ የማድፈጥ ባሕርያት፣ ማድፈጥ የግለሰብ ሀሳብ ነው ( ገፅ 21) ማድፈጥ ምሥጢር ነው፤ መለገም የማድፈጥ አንዱ የማጥቂያ መሣሪያ፣ የማድፈጥ የመጨረሻ ዓላማ፣ የማድፈጥ ውጤት – በተግባር (ገፅ 24)፤ የማድፈጥ ጉዳት (ገፅ 26) በሚሉ ንዑስ ርእሶች ጉዳዩን በጥልቀት በመተንተን ያቀርቡታል፡፡ ይሄ ጉዳይ አጠቃላይ አገራዊ ማህበራዊ ጉዳዮችን በጥልቀት የሚያጠኑ ሰዎች በርግጥ ይህ ፕሮፍ ያነሱት ሐሳብ ያለውን ድርሻ በስፋት በማጥናት ለለውጥ የሚያግዙ ሐሳቦችን ቢያመነጩ ዲሞክራሲያዊ ማህበረሰብን በመፍጠር አምባገነናዊ ሥርዓትን ለመቅጨት የሚደረገውን ጉዞ ባፋጠነ ነበር ያሰኛል፡፡

የስም ማውጫን ጨምሮ በ260 ገፆች ተቀንብቦ የተሰናዳው ይህ መጽሀፍ እንዘጭ!-እምቦጭ! ከመሠረቱ፣ መነሻ ጥያቄዎች፣ መድረሻችን ከመነሻችን፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ና ሕጋዊ ሥርዓት፣ ግፍና ግፈኛ፣ የጉልበተኛነት አዝማሚያ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ኃላፊነት፣ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት፣ ሕግና ማኅበረሰባዊ ኑሮ፣ ሕገ መንግሥትና ሕግ አስከባሪነት፣ የሀሳቦች መምከን
እንዲሁም ባህላዊና ዘመናዊ ትምህርት (ገፅ 167)፣ ከሕገ አራዊት መላቀቅ (ገፅ 199) ዋናዎቹ የኢትዮጵያ ችግሮች (ገፅ 210) ጨምሮ የማይዳስሱት አገራዊ ጎዳ እና አጀንዳ የለም ማለት ይቻላል፡፡ ለምሳሌም ‹‹እንዘጭ!-እምቦጭ!›› እያሉ የሚገልፁዋቸውን አንዳንድ ተጨባጭ ማስረጃዎችን ጨምሮ (ከገፅ 132 እስከ 142 ያለውን ይመለከተዋል) ዋና ዋና ሕዛባዊ ድርጅቶች በሚለው አብይ ርዕስ ዙሪያ ደግሞ- የሠራተኞች ማኅበራት፣ የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ፣ የሥነ ጥበባት ባለሙያዎች፣ የፖሊቲካ ቡድኖች፣ ጋዜጠኞች፣ የመንፈሳዊ መሪዎች ተሳትፎን የተመለከቱ ዝርዝር ሀሳቦች ያወሳሉ፡፡

በስፋት ለሚያነሱት ችግሮችም መፍትሄ ይሆናሉ የሚሉዋቸውን ሐሳቦች ከዳበረ ልምዳቸው፣ በግል ካደረጉት ጥናት እና ምርምር፣ ከዳበረ የንባብ ባሕላቸው፣ በአካል ከተሳተፉበት ገጠመኖች እና ተሞክሮዎች በመነሳት – እንዴት ሽግግር (ገፅ 72)፣ ሰው መሆን ያቃታቸው ፖሊቲከኞች (ገጽ 78)፤ አንድነት በልዩነት፣ ልዩነት በአንድነት (ገጽ 85)፤ ከፖሊቲካ በፊት ሰው መሆን (ገጽ 87) ከአገዛዝ ወደ ፖሊቲካ (ገጽ 92)፣ የሕዝብ አቅመ-ቢስነትን ለማጥፋት (ገጽ 244) በሚል በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ጭቆናንና በደልን የሚመለከተውና የሚቀበለው በግል፣ ለየብቻው ሆኖ ነው፤ የሚልን ሐሳብ በመፅሐፋቸው ላይ በስፋት የሚያወሱት ፕሮፍ ይህም በጋራ በመተባበር ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዳይገነባ ከማድረጉ ባለፈ ‹‹በሚደርስበት በደልና ጭቆና እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ቂም ይይዛል፤ በደሉ፣ቂሙ፣ በቀሉ የግል ነው፤ ቂም የእያንዳንዱ ሰው ምሥጢር ነው፤ ስለበደሉና ስለጭቆናው በውስጡ የተከማቸውን ቂምና የሚመኘውን በቀል ማንም እንዲያውቅበት አይፈልግም፡፡›› ይሉ እና የማድፈጥ ዓላማው በቀል መሆኑን ያወሳሉ፡፡ ይሁን እንጂ ማድፈጥም ሆነ በቀል ሰላምን አይሰጡትም፤ በዝምታ ማድፈጥ እንዳይታገል ያደርገዋል፤
በምሥጢር የሚይዘው ቂም እውነተኘ ችግሩን በጋራ ለመፍታት አያስችለውም፤ በማለት በዝርዝር እንደ አንድ አገር ሕዝብ አለብን የሚሉትን ችግር ይዘረዝራሉ፡፡

‹‹የሄድንበትን እንሄድበታለን?›› የሚል ጥያቄን በማስቀደም ፕሮፍ የመጽሐፍቸው ዓላማ ያለፈውን ለመውቀስ ሳይሆን ‹‹ያለፈ የሚመስለውንና አሁንም በውስጣችን ያለውን እውነት ማውጣትና ማሳየት፣ መናገር ነው፤ ያለፈው ትውልድ የፈጸመውንና አሁንም በእኛ ውስጥ ያለውን ማውጣት ያለፈውን መውቀስ ሳይሆን ያለውን ለማጽዳት መሞከር ነው፤ የኔ ዓላማ ያለውና ወደፊት የሚመጣው ራሱን ለማስተካከል ራሱን በአለፉት ውሰጥ አይቶ ራሱን እንዲታዘብ ነው፤ራሱን ታዝቦ ራሱን እንዲለውጥ ነው፤›› ሲሉ ይገልፁታል፡፡ ‹‹ታሪክ ራሱን ይደግማል›› እንደሚባለው ብሂል በአገራችን በተደጋጋሚ አሳዛኝ ነገሮች ራሳቸውን ደግመዋል፡፡ በአገዛዞቹ አምባገነንነት የሚከሰቱትን እነዚህን አላስፈላጊ እልቂቶች ለማስቀረት ካለፈው መማሩ ግድ ነው፡፡ ለዚህም የሶስት ሥርዓቶችን ኩነት ተሸግሮ የተሰናዳው የፕሮፍ መጽሀፍ የላቀ ድርሻ ይኖረዋል፡፡

ፕሮፍ – << ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ መሆኑን አውቃለሁ፤
አልቀበር እንጂ እኔኮ ሞቻለሁ፤ >> የሚለውን ግጥማቸውን ባስቀደሙበት እና ‹‹ዋናዎቹ የኢትዮጵያ ችግሮች ያሉትን በዘረዘሩበት ምዕራፍ ውስጥ ‹‹ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዋናዎቹ የኢትዮጵያ ችግሮች በሕገ መንግሥቱ ውስጥ በግልጽ የተደነገጉ ናቸው፤ … የሕይወት (በሕይወት የመኖር መብት)፤ የአካል ደኅንነት መብት፤ በነጻነት የመኖር መብት፤ የእኩልነት መብት፤ የሃይማኖትና የእምነት ነጻነት፤ ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት፤ የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት … ›› የመሳሰሉትን ጨምሮ መሰረታዊ የዜጎች መብት የተሰኙት አንቀፆችን በመዘርዝር ‹‹ እነዚህን ነጻነቶችንና መብቶችን የሚያውጁ አንቀጾች የኢትዮጵያ ዋና ችግሮች ናቸው፤›› ሲሉ ይሞግታሉ፡፡ (ዝርዝሩን ከገጽ 85 አንስቶ ማየት ይቻላል፡፡)

ከላይ ከተወሳው ያልተለመደ ሐሳባቸው ወጣ በማለትም በእኔ በአንድ ሰው ዕድሜ የፋሺስት ኢጣልያንን አገዛዝ፣ የአጼ ኃይለ ሥላሴን አገዛዝ፣ የደርግን አገዛዝ፣ የወያኔን አገዛዝ አይቻለሁ፤ እነዚህ ሁሉ አገዛዝ በመሆናቸው አንድ ናቸው፤ ነገር ግን ባሕርያቸው የተለያየ ነው፤ የሚሉት ፕሮፍ ‹‹ የኢትዮጵያ ሕዝብ በግፈኛ አገዛዝ ስር ለምዕተ-ዓመታት የቆየው እንዴት ነው? በብዙ ምዕተ-ዓመታት የኢትዮጵያ ታሪክ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሥልጣንን ለመግራት ሕግን አውጥቶ በሕዝቡ ፈቃድ ላይ የተመሠረተ ሥርዓተ መንግሥት ማቋቋም እንዴት አቃተው?›› ሲሉ ይሞግታሉ፡፡ አክለውም ‹‹ ሲወርድ ሲዋረድ አሁን ባለንበት ዘመን ድረስ የአንድ ሰው አገዛዝ ወይም አንድ ሰው ከጥቂት ሎሌዎቹ ጋር ሆኖ አድራጊ-ፈጣሪ፣ ቆራጭ-ፈላጭ ሆኖ ሕጋዊ ኃላፊነትም ሆነ ተጠያቂነት በሌለው አገዛዝ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ ተሰቃይቷል፤ ግፈኛውን እያደፈጠ ቢደፍቅም ሥርዓቱን ለመለወጥ አልቻለም፤ ሥርዓቱም በተከታታይ ከሚደርስበት የውርደት ውድቀት ተምሮ ሕግን ተመርኩዞ ራሱን ለመለወጥ አልደፈረም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጭቆና አገዛዝን በማድፈጥ ለመጣል የሚያደርገው ቆራጥ እርምጃ ትክክለኛና ሕጋዊ ሥርዓትን ለመትከል ለምን አልዋለም? የግፍ አገዛዝን እያደፈጡ መጣል ወይም መንቀል አዲስና ሕጋዊ ሥርዓትን ወደመትከል ያልተሸጋገረበት ምክንያት ምንድን ነው? መጣል ወይም መንቀል ከመትከል የቀለለ ሆኖ የታየው ለምንድን ነው? ለመንቀል የሚያስፈልገው ለየብቻ ቂምን ቋጥሮ ግፈኛውን የሚቋቋም አጋር ሲመጣ ማጀብ ብቻ ነው፤ መትከል ግን የብዙ ቁም-ነገሮችን መሟላት ይጠይቃል፤ ይህንን ጉድለት ቆይተን እናየዋለን፡፡ እነዚህን ጉድለቶች በማን ላይ እንጣላቸው? በመሪዎች ላይ ነው? ወይስ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ? ወይስ በሁለቱም ላይ?›› በማለት ለምላሹ ይተጋሉ፡፡

በእርግጥም እርሳቸው ያነሱት ለመሰረታዊ ለውጥ የሚረዳ ሐሳብ እንዳለ ሆኖ መጽሀፍ በርግጥ ብዙ ነገሮችን ለውይይት ከመጋበዝ ባለፈ ብዙ ጥያቄዎችንም የሚያስነሳ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች ጥቂቶቹ በመጽሀፍ አዘጋጅ ሊመለሱ የሚገባቸው ብዙዎቹ ግን በፖለቲካ፣ በታሪክ እና በማህበራዊ ሳይንስ ዙሪያ የተሰማሩ ተመራማሪዎች ተገቢውን ጥናት በማድረግ የመፍትሄን ሐሳብ ሊያመነጩበት የተገባ ነው፡፡ (በሌላ ግዜ እንዚህን ጥያቄዎች ዝርዝር ከተሳካልኝ የፕሮፍን ሀሳብ በማከል ጭምር ልመለስበት እሞክራለሁ፡፡ ለጊዜው ግን መጽሀፋ ገና ሰው ዘንድ በስፋት ባለመድረሱ ከዚህ የበለጠ ማውሳቱን አልመረጥኩም፡፡)

ፕሮፍ በሕይወት ዘመናቸው የገጠማቸውን ነገር በማውሳት እንደ ማስጠንቀቂያ ያወሱትን ሐሳብ በማከል ነገሬን ልቋጨው፡፡ ‹‹ ነገ የወጣቶች ነው፤ ትናንት የሽማግሌዎች ነበር፤ ይባላል፤ በትክክልና በጥሞና ካልታሰበበት ይህ የተለመደ አባባል ስሕተተኛ ብቻ ሳይሆን አደገኛም ነው፤ እኔ አርባ ዓመት አልፎኝ ወጣት በነበርሁበት ጊዜ ኢትዮጵያን የሚያሽከረክሯት ሽማግሌዎች ነበሩ፤ ‹‹ይሄ ልጅ›› ይሉኝ ነበር! አርባ አራት ዓመት ግድም ሲሆነኝ ኢትዮጵያን የሚያሽከረክሯት ወጣቶች ሆኑና ‹‹ይሄ ሽማግሌ›› ይሉኝ ጀመር! ‹‹ይሄ ልጅ›› ሲሉኝ ልሠራ የምችለውን ብዙ ነገር የማልችል አደረጉኝ፤ እንደዚሁም ‹‹ይሄ ሽማግሌ›› ሲሉኝ በጣም ደካማና ኋላ-ቀር አደረጉኝ፤ ራስን ከፍ ለማድረግ ሲባል ሌላውን ዝቅ ማድረግ የሥልጣን ጥመኞቹን የሚረዳ ቢሆንም ማኅበረሰቡን በጣም ይጎዳል፡፡››

መጻፉን ለመግዛት የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ መጠቀም ይችላሉ፡፡

https://www.mesfinwoldemariam.org/

የአንባቢያን አስተያየቶች

 1. ሙዘሚል says:

  ፕሮፌሰር መስፍን ቂመኛ ትግሬም ጭምር ናቸው ከጠሉህ ለእድሜ ልክ ነው እዚህ አምድ ላይ አስተያየት የሰጠው ሁሉ በአንድ ድምጽ ጥላቻውን በመግለጹ ሳተናው ድረ ገጽ ላይ በተለመደው ባማራ ጥላቻቸው ህዝበ አዳሙን። ሙልጭ አድርገው ሰድበውታል ይሄ ነው ምሁር መጻፍ አልገዛም በማለቱ የሚወርድበት ውግዘት። አይ ፕሮፍ አስተያየት ለእርሶ የማይመች ከስጠ አማራ ነው ማለት ነው? ልብ ይስጦት ምን ይባላል ይሄ ትግሬነቶ እስከ ወዲያኛው ይዞት ሊሄድ ነው ማለት ነው?

 2. Anonymous says:

  We can say, the so-called Safari Club (read below) is the best proof of a ferenji – arab conspiracy against Ethiopia.

  We all know that in 1977 G.C. Carter’s USA betrayed Ethiopia, a USA ally at the time, by refusing to deliver arms that Ethiopia paid for. What most of us don’t know is that at the same time USA was PRESSURING SOMALIA TO INVADE ETHIOPIA, likely a Henry Kissinger and Zbigniew Brzezinski plan to wipe Ethiopia off the map.

  ” Under the Safari Club pressures and help promises, Siad Barre committed a disastrous strategic mistake of attacking Ethiopia. ” 

  From article: Somalia: How Colonial Powers drove a Country into Chaos

  In the early 1970s G.C. USA used to call Haile Selassie an ally while at the same time plotting to overthrow him with other western countries.

  Of course the “useful idiots” Derg/Mengistu and EPRP/Meison/the protesting students were instrumentalized by USA and company for their anti-Ethiopia agendas.

  Now, why did USA & the West plot against Haile Selassie (read also the points 4 and 5 below) ?

  George Bush Sr. on China

  1971: Argued for dual UN representation for China & Taiwan

  ” In Oct. 1971, the UN voted to recognize Red China and give the People’s Republic of China the seat occupied by Taiwan, or Nationalist China. George vowed in his Senate campaigns if that were to happen, he would advocate US withdrawal from the UN. Now, as Nixon’s Ambassador, he had to argue for “dual representation” and plead for 2 seats: one in the Security Council for Communist China, and one in the General Assembly for Taiwan. He had lobbied hard among the 129 missions for support and had thought he had enough delegates committed to the US policy. But on the final count, he lost 59 – 55, with 15 countries abstaining. He took the defeat as a personal rebuke and said he was disgusted by the anti-American sentiments. “For some delegates (FYI: it was Africans who were dancing in the aisles) – who literally danced in the aisles when the vote was announced – Taiwan wasn’t really the issue.” George said. “Kicking Uncle Sam was.” ”

  As we already know the USA and the West had a lot of records to “settle” with Haile Selassie.

  Ferenjis had many reasons to overthrow Haile Selassie (HIM), revenge being a key factor, among them:

  1. Dont forget that Britain was angry that it was thrown out of Ethiopia in 1945 G.C. and replaced by USA. It was waiting for an opportunity to revenge against HIM. Actually UK started with its revenge mission already in 1946 G.C. with the Bevin Plan.

  Get the youtube video ” I.M. LEWIS “The Somali Interest in the early days ” (i couldn’t post the link here) and listen to the anti-Ethiopian british citizen I.M. Lewis starting at 3:59. Look at his facial expression and tone.

  2. Support for African liberation movements like the Mau Mau rebellion in Kenya, and in other countries like Angola and South Africa.

  3. Efforts to create a continental organization (OAU, founded in 1963 G.C. in Addis Abeba) with agendas among others to free the continent from ferenji or western colonialism.

  4. Support for Chinese membership in the UNO instead of Taiwan that USA and ferenjis had preferred.

  The United Nations Resolution 2758, passed in October 25, 1971 G.C., recognized the People’s Republic of China (PRC) as “the only legitimate representative of China to the United Nations” and expelled “the representatives of Chiang Kai-shek from the place which they unlawfully occupy at the United Nations.”

  Two key points we should know here, Haile Selassie, using his popularity among Africans, played a key role in mobilizing the crucial African vote in favour of China (mainland), and after suffering a defeat ferenjis THREATENED, i guess HIM, to revenge in an article published on a ferenji paper or magazine.
  Was Henry Kissinger the guy who wrote the threat ?

  5. France was reluctant to give up Djibouti that it had leased from Menelik for 99 years in 1878 G.C..

  Consider here the involvement of France in a dubious organization called Safari Club.

  Safari Club
  https://en.wikipedia.org/wiki/Safari_Club

  Four sources about the Safari Club:

  A. ” Organized with the blessing of Henry Kissinger, U.S. Secretary of State for the Nixon and Ford
  administrations, the “Safari Club” was the brainchild of French spy chief Comte Claude Alexandre de Marenches and consisted of France, Egypt, Iran, Morocco and Saudi Arabia.

  Information about the group came to light after the 1979 Iranian revolution exposed previously secret documents of the former Iranian regime’s Foreign Ministry. ”

  B. ” The Safari Club was an alliance of intelligence services formed in 1976 to fight the Cold War in Africa. Its formal members were Iran, Egypt, Saudi Arabia, Morocco, and France. The group maintained informal connections with the United States.

  The Club executed a successful military intervention in Zaire in response to an invasion from Angola. It also provided arms to Somalia in its 1977 – 1978 conflict with Ethiopia. It organized secret diplomacy relating to anti-Communism in Africa, and has been credited with initiating the process resulting in the 1979 Egypt Israel Peace Treaty. ”

  C. According to a third source Mobutu’s Congo and Pakistan were also part of this dubious club: ” … Kissinger was representing an unofficial organization: the Safari Club that was among others including Shah’s Iran, Mobutu’s Congo, Saudi Arabia, Morocco and French and Pakistani intelligence services. ”

  D. Quote from globalresearch.ca:

  The Safari Club

  Following Nixon’s resignation as President, Gerald Ford became the new US President in 1974. Henry Kissinger remained as Secretary of State and Ford brought into his administration two names that would come to play important roles in the future of the American Empire: Donald Rumsfeld as Ford’s Chief of Staff, and Dick Cheney, as Deputy Assistant to the President. The Vice President was Nelson Rockefeller, David Rockefeller’s brother. When Donald Rumsfeld was promoted to Secretary of Defense, Dick Cheney was promoted to Chief of Staff. Ford had also appointed a man named George H.W. Bush as CIA Director.
             
  In 1976, a coalition of intelligence agencies was formed, which was called the Safari Club. This marked the discreet and highly covert coordination among various intelligence agencies, which would last for decades. It formed at a time when the CIA was embroiled in domestic scrutiny over the Watergate scandal and a Congressional investigation into covert CIA activities, forcing the CIA to become more covert in its activities.

  In 2002, the Saudi intelligence chief, Prince Turki bin Faisal gave a speech in which he stated that in response to the CIA’s need for more discretion, “a group of countries got together in the hope of fighting Communism and established what was called the Safari Club. The Safari Club included France, Egypt, Saudi Arabia, Morocco, and Iran [under the Shah].”[1] However, “The Safari Club needed a network of banks to finance its intelligence operations. With the official blessing of George H.W. Bush as the head of the CIA,” Saudi intelligence chief, Kamal Adham, “transformed a small Pakistani merchant bank, the Bank of Credit and Commerce International (BCCI), into a world-wide money-laundering machine, buying banks around the world to create the biggest clandestine money network in history.”[2]

  As CIA director, George H.W. Bush “cemented strong relations with the intelligence services of both Saudi Arabia and the shah of Iran. He worked closely with Kamal Adham, the head of Saudi intelligence, brother-in-law of King Faisal and an early BCCI insider.” Adham had previously acted as a “channel between [Henry] Kissinger and [Egyptian President] Anwar Sadat” in 1972. In 1976, Iran, Egypt, and Saudi Arabia formed the Safari Club “to conduct through their own intelligence agencies operations that were now difficult for the CIA,” which was largely organized by the head of French intelligence, Alexandre de Marenches.[3]

  (Note: i have difficulty to post a number of links here, including links to these quotes. So i only posted the quotes)

  6. Also let us not forget ferenjis’ desire to revenge on HIM who predicted in 1936 G.C. before the League of Nations: ”… the match has been lit in Ethiopia, but the fire will burn Europe.” 

  According to observers, in the years before the overthrow of HIM predictions about the fall of HIM were repeatedly published on French newspapers.

  The predecessor of DGSE was likely behind those publications and it was no doubt a reference to HIM’s speech in 1936 G.C.. If you ask me, all that sounds fishy.

  There are also rumours about France’s roles in creating the Derg.

  7. The OAU resolution in 1973 G.C. to break diplomatic relations with Israel.

 3. Anonymous says:

  instead of give attintion for tplf under cover mesfen woldmariam the adwa man we shoud bring our own professors like fikrea tolssa,haile larabo etc .

  • Anonymous says:

   Nobody will buy prof. Mesfin’s book anymore.

   But let us not forget that, if he is indeed a CIA/TPLF agent, this is a huge huge scandal.

 4. amor ambulance says:

  this demon man parents are the demon adwa .he support the tgreas rule and the genocide of amra .this demon said to mellesse and tplf there is no amra in ethiopia .every time he worried about the tgreas safty only he never hide it .he support only the tgreas not ethiopian he is a demon all ethiopian shoud not accepted him as ethiopian

 5. Dereje says:

  Mesfin agent of CIA.
  How a professor can serve three regimes with big ideological differences.
  He served feudalism, socialism and revolutionary democracy.

 6. ቶሌራ says:

  ጅብ የማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል፡፡
  መስፍን በማያውቁት ላይ ይቀልድ፡፡
  እነ እሸቱ ጮሌ ላይ ግን አይቀልድም፡፡
  ስለ መስፍን ጓደኞቹ ይናገሩ፡፡

 7. ነብይ 1997 says:

  ፕሮፌሰር መስፍን የተመረቀው በጂኦግራፊ ነው፡፡
  በሙያው የሰራው አንዳችም ነገር የለም፡፡
  በፖለቲካ ውስጥም ገብቶ በተለያየ ጊዜ ከግለሰቦች እና ፓርቲዎች ጋር እሰጥ አገባ እየገባ ትግሉ ላይ ውሃ የቸለሰ ነው፡፡
  ሰላማዊ ትግል እያለ እያዘናጋ የማይቀረውን የትጥቅ ትግል ለወያኔ አዘግይቶለታል፡፡ይሳካለተም አይሳካለትም በመሳሪያ ወያኔን እፋለማለሁ ብሎ ዶክተር ብርሃኑ ሲደራጅ ለወያኔ ወግኖ የነቀፈ ሰው ነው፡፡
  መስፍን የወያኔው ደህንነት የነበረው ክንፈ ጋር ሁነኛ ወዳጅ የነበረ ሁለት ገጽታ ያለው ሰው ነው፡፡
  መስፍን ያልተጣላቸው የፖለቲካ ግለሰቦች እና ቡድኖች የሉም ከሁሉም ጋር በጸብ ነው የሚለያየው፡፡ይህ ባሪው ወያኔን በደንብ ጠቅሞታል፡፡ፓርቲ እና ግለሰቦችን መስፍን ቀድሞ ያፈርሳቸዋል፡፡መስፍን ካልሆነለት ወያኔ ይተካል፡፡
  የመስፍን የመጨረሻው ውርደት ወያኔዎች የገደሉትን ገድለው፣ የዘረፉትን ዘርፈው ስልጣን ይልቀቁ ማለቱ ነው፡፡
  ወያኔዎችን ለማባረር አንዳችም ትግል ያለደረገው መስፍን አሁን የወያኔ መቃብር በህዝቦች ደም እውን ሊሆን ሲል ነጻ ልቀቋቸው ይለናል፡፡ይህ ጤነኛ አእምሮ አደለም፡፡ በ1997 ደብተሩን በእጁ እንደያዘ አስፋልት ላይ የተገደለው የ14 አመቱ ነብይ ደም መስፍንን ይፋረደው፡፡
  በሺዎች የሚቆጠሩ ለኢትዮጵያ ነጻነት ሲሉ በወያኔ የተጨፈጨፉ ዜጎች ድምጽ ከመቃብር ይጮሃል፡፡መስፍን ግን በ85 አመቱ ይህንን ድምጽ ዘንግቶ ወያኔ ነጻ ይውጣ እያለ ነው፡፡ምነው የደርግ ሹሞች ነጻ ይውጡ ብሎ አልተናገረ፡፡
  መጸሃፍ ቢማሩት ልቦና ከሌለ ዋጋ የለውም፡፡የቄስ ጥምጥም መሃይም አያቀስም፡፡
  መስፍን የያዘው የእንጨት ሽበት ነው፡፡
  የመስፍን መጸሀፎች ሆኑ አስተሳሰቦች ምንም ውጤት ስለሌላቸው ከመንገዳችን ዘወር በልልን፡፡
  በመሰረቱ መስፍን የትግሬ ደም ስላለበት በመጨረሻው ሰአት ደም ከውሃ ይወፍራል እና ለትግሬዎች መሟገቱ አይደንቅም፡፡

 8. Yohannes Maekel says:

  I have a big respect for professor Misfen Wold Mariam, I have read his books and gained a good knowledge of the Ethiopian history.
  I am 46 years of age from southern part of Ethiopia.
  I can’t wait to get his latest book to read and to understand how we ( Ethiopian )failed to achieve the social goals of human rights and brings prospective lifestyles to the people.

 9. Anonymous says:

  It suffices to read the few sentences below to conclude that the jewish American scum Donald Levine is a CIA agent (CIA = NAZI, white supremacist, jewish & catholic)

  Quote:

  Greetings again Professor Levine. This chapter deals with the political issues you have raised in your response. Let us circumscribe our subject. I will not be talking as you did in general terms about U.S, or U.S official government politics towards Ethiopia, the State Department etc. Instead, I will talk about the CIA – the invisible unofficial, U.S government that has been misgoverning, mismanaging through its proxies in a   large part of the Third World, above all in Latin America, but also, in Asia, and in Africa since the end of the Second World War. We all know the CIA is well present in the Universities in the U.S and Europe, among scholars and students. In general while lecturing on the Third World, Western scholars shy to talk about the CIA. They talk about our under-development, about our poverty. They talk about our famine; they talk about our civil war; about our “tribal wars” particularly in  “primitive“ Africa, – as if they were all homemade homegrown problems for which we are entirely responsible, as “free” people.

  You characterize the Ethiopians, particularly those in the Diaspora =====> as addicted to blaming others for their misfortune. You accuse me of =====> “Indulging in postures, of blaming others…”    

  These CIA assholes are liars, they deny everything. Lying and deception is part of their job.

  THE WATCHMEN: Secrets of the CIA (720p)

 10. ደጃዝማች ሊዎንቴፍ says:

  የኛ ምሁራን ሰው በምሁርነት ስም እንደ በግ የሚመራላችሁ ዘመን አልፏል ከላይ የተሰጠው አስተያየት እንደሚያመለክተው አስተሳሰባችሁ ምን ያህል ከሰው እንደራቅና በሰራችሁት አለም ብቻ እንደምትኖሩ ነው የሚያሳየው። በተሰጠው አስተያየት ህዝቡ ምን ያህል መስፍንን እንደሚያውቃቸው የተረዳችሁ ይመስላል። ሰውን አትናቁ እናንተም ተደብድባችሁ መስፍንንም አስደበደባችሁ። መስፍን አዋቂነትን ሲያበዙ ህዝቡ ጋር ቀጥትኛ ግንኙነት እንዲኖራቸው አውራጃ ገዥ ተደርገው ነበር እግዚኦ ብለው ባማላጅ አዲስ አበባ ከምቾት እንዳይርቁ ተለማምጠው ቀሩ። ያጼ ሐይለ ስላሴ የመንግስቱ ሐ/ማርያም የቅርብ ሰው የመለስ ዘራዊ የቅርብ ስው ነበሩ ከስልጣን ሲወገዱ ከመለስ ዘራዊ በስተቀር ቀድመው ጩቤ የሰኩባቸው መስፍን ነበር። ሰሞኑን የአጼ ሐይለ ስላሴን ስራ ለማጠልሽት በሰነዘሩት አስተያየት አቻም የለህ ታምሩ በማስረጃ አስድግፎ እንዳበራያቸው ተመልክተናል። ሰውዬው የሰሜን ሰው ናቸው በዛ በኩል የመጣባቸው አይወዱም በጣም አዋቂ ነኝ ይላሉ ወምበሩ ሲሰጣቸው ጭንቅ ነው እሳቸውም እንዳሉት በተፈጥሯቸው ከመገንባት መናድን ይመርጣሉ። ስለሳቸው ከሚገባው በላይ መጻፍ ይቻል ነበር ኢላማው እሳቸው ሳይሆኑ በተሽከማችሁት የዲፕሎማ ድርድር ህዝቡ የወረወርነውን ሁሉ ይቀልባል ብላችሁ ላሰባችሁ የስም ምሁራን ማስጠንቀቂያ ለመስጠት የተነጣጠረ አስተያየት ነው። ህዝባዊ ሁኑ እናከብራችኊለን በተረፈ ህዝብ እየተጨፈጨፈ ለቀልድ የምትወረውሩት ሀሳብ ተቀባይነት የለውም። ለሀገራችን ተጨባጭ ስራ አሳዩን።

 11. Abayre says:

  ayeee kkkkkkkkkk

  sew Tira belut Mesfin ?? KK

  Mesfin le 3 mengist yesera selay new

  tsre Ethiopia !! ye enchet shbet !!

 12. Al mehdi says:

  Mesfin did nothing to ethiopia in his life time.
  Leave the youth alone we will democratize Ethiopia by our blood.

 13. Deriba says:

  He is half Tigre like meles.
  I don’t believe him.

 14. Abebe says:

  He made a debate with meles zerawi recognizing tplf.
  He was appointed by the majesty as regional governor but he was not willing to serve the people.
  He was derg advisor during the 60 haile silassie officials massacre.
  He has done nothing practical for Ethiopia people except writing like debtera.

 15. Okolg says:

  He is good for nothing.
  What he contributed for Ethiopia people struggle for freedom.

  NOTHING.
  For me OLF is better than him.

 16. Sasaw says:

  The so called professor said nothing about Amhara genocide.
  He also said nothing about tplf when goshu wolde(colonel) fight in his historical speech about Eritrea independence.
  He opposes birtukan, birhanu, lidetu, hailu shewal, and all political parties.
  He worked for tplf.

 17. አማራ ወዳጅና ጠላትሕን ለይ says:

  በማስቀደም በሥነሥርዓቱ ላይ ተገኙ የተባሉትና የተደረደረው የትምሕርት ማእረግ ጋጋታ ሊነግረን የሚፈልገው በፕሮፌሰሩ ዙሪያ ከሙገሳና ከአድናቆት ባሻገር ሌላ አትበሉ የሚል ቅድመ ሁኔታ ለማስቀመጥ የታሰበ እንድምታ ያለው ይመስላል።ከዚሕም አኳያ ጻኅፊው ጊዜ ያለፈበትን የተማረ ሰው ይግደለኝ ሲባል ሂድና ዩኒቨርስቲ በር ተኛ የሚለው የድሮ አስተሳሰብ ተሸክሞ የሚዞር ይመስላል።ምሁር የሚለው ቃል የአካዳሚክ ማዕረግ ስብሰባ የላቀና ምሁር ነኝ የሚለው ላስተማረው ዎገኑ በሚያበረክተው ተጨባጭ ተግባር የሚለካ መሆኑን ያከተተ መሆኑን የዛሬው ትውልድ ጠንቅቆ ያዎቀና በማእረግ ጋጋታ የማይወናበድ መሆኑን ዛሬ አለማቀቅ ትልቅ ስሕተት ነው።

  ፕሮፌሰሩም የሚታዩት ከዚሕ አንጻር እንደሆነ ግልጽ ሊሆን ይገባል።እኔ አማራ ነኝ።እንደአማራነቴም ሰውየውን የማስታውሳቸው አማራ የለም በሚለው አነጋገራቸው ሲሆን ይሕ ደግም ያሬ አማራ ለሚገኝበት ሁኔታ በአሉታዊ ገጽታው ከፍ ያለ አስተዋጽዖ ያደረገ መሰረታው ጉዳይ ነው።ይሕ ፍጹም ከዕውነቱ የራቀ አነጋገር በአንድ በኩል አማራው በዎያኔና ግብረአበሮቹ ሲጨፈጨፍ፤ሲፈናቀልና ኢሰብአዊ ድርጊት ሲፈጸምበት ጠላቶቹ አማራ የትአለና ነው ተጨፈጨፈ፤ተፈናቀለ የምትሉት እያሉ እንዲሳለቁብንና ያለማቋረጥ በዚሁ ፋሽስታዊ ተግባራቸው እንዲቀጥሉ መሰረት የጣለ አነጋገር ነው።
  ዛሬ ደግሞ ሰውየው [እኔ ሰውን የማከብረው በሥራው ነው] እነዚሕ ፋሽስቶች ለፈጸሙት የዘር ማጥፋት እንዳይጠየቁ ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረፉትን ይዘው እንዲቆዩ እንፍቀድላቸው በማለት ጥብቅና ቁመዋል።ለመሆኑ ሰውየው የሕግ የበላይነትና ተጠያቂነት የሚለውን ሰምተዋል?የቀለም ትምሕርት ማዕረግ ጋጋታ ብቻውን ዋጋቢስነትን ምሳሌ ይሉኅል ይሕ ነው።
  ማንም እንደፈለገ መደናቆር የግሉ ነው።ለኔ ግን እኝሕ ሰው የአማራ ጠላትና ጊዜ ከሰጣቸው ተጠያቂ ናቸው።

  • Anonymous says:

   =====> ዛሬ ደግሞ ሰውየው [እኔ ሰውን የማከብረው በሥራው ነው] እነዚሕ ፋሽስቶች ለፈጸሙት የዘር ማጥፋት እንዳይጠየቁ ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረፉትን ይዘው እንዲቆዩ እንፍቀድላቸው በማለት ጥብቅና ቁመዋል።

   Prof. Mesfin is a very suspicious figure. It looks like he was or still is agent of the CIA and TPLF.

   Ethiopians have now the duty to analyze his activities and role from the days of the Ethiopian Students movement, or even from the days of Germame Neway, to today.

   The lie he told about Haile Selassie that we learned recently, namely that Haile Selassie was not willing to reform, when the truth is that Haile Selassie ordered a reform of the constitution, granting many freedoms, but it was the Derg (perhaps following ferenji orders) who stopped the passing of the new constitution by dissolving the parliament, increases the possibility that he was or still is a CIA agent.

   In that case that would be a huge scandal.

   * Someone on this forum once said Prof. Mesfin is the guy who brought so many problems to Ethiopia by telling false information about Ethiopia to the CIA.

   * There are also those who said he misled the students of the AAU in the days of the “Ethiopian Students Movement”.

   * He was invited in the USA embassy in Addis Abeba during the Haile Selassie era with other elites like Afewerk Tekle and Tsegaye Gebremedhin.

   * He always appears to be in the right place in critical times, like he was in contact with Haile Selassie during the so-called Ethiopian revolution, in reality a covert CIA operation, he was in contact with Mengistu during Derg’s last hours, and with his Qeste Demena he joined the CUDP in the last hours during the 1997 E.C. (2005 G.C.) elections and brought with him Berhanu Nega. And we know what role Berhanu Nega played.
   etc

   So, all that makes him a suspicious figure.

  • Anonymous says:

   We need to start exposing the spies and traitors and telling the truth about the West’s crimes against Ethiopia. It is important that people know the truth, also to prevent repeating mistakes in the future.

   For example most Ethiopians do not know that Haile Selassie was overthrown by the West. It is possible that Prof. Mesfin played a big role in this ignorance of the people, say by telling lies. We learned few days ago that he lied about Haile Selassie.

   That most Ethiopians don’t know that the CIA was the biggest political player in Ethiopia since the 1960s G.C., could be partly because of Prof. Mesfin.

   One of the reasons Ethiopians don’t know about these important facts is that many Ethiopian elites both at home and abroad are bought by the CIA. Some people estimate that thousands of Ethiopians are agents of the CIA at this moment.

   Knowledge about the past to prevent future disasters and to know who is friend and who is enemy is a good thing.

   The professions of most CIA agents are,

   1. journalist

   2. lecturer

   3. government official

   4. activist

   5. member of civic organizations

   6. politician

   etc

  • Anonymous says:

   We need to start talking about the overthrow of Haile Selassie by the West.

   For example EPRP was created by the CIA in 1972 G.C. in USA/UK/France and Germany controlled West Berlin AS PART OF A COVERT CIA OPERATION AGAINST HAILE SELASSIE AND ETHIOPIA because the CIA, USA and West were mad at Haile Selassie and his Pro-Africa and Anti-European colonization policies since the late 1950s G.C..

   That means all those organizations, including TPLF, were serving a ferenji or western agenda. And that makes them TRAITORS against Haile Selassie, against Ethiopia, against Africa and against the black race.

   And as the revelation by LaRouche shows Derg was also a USA/Western/Ferenji agent group.

   USA political activist Lyndon LaRouche writes: On September 12, 1974 Haile Selassie was overthrown in a Pro-American military coup with approval of Henry Kissinger.
   http://www.larouchepub.com/eiw/public/1995/eirv22n24-19950609/eirv22n24-19950609_012-horn_of_africa_the_british_setup.pdf

   If the above is true, then Haile Selassie (HIM) was overthrown by the USA or the West. And Derg and Mengistu were agents of the USA or ferenjis.
   That Henry Kissinger approved the coup against HIM means also, he or the people behind him like the Rockefellers, Rothschilds and the Queen of England likely ordered Mengistu to kill HIM.

   So, regarding the CIA or western plot against HIM and Ethiopia, there are two camps within Ethiopia,

   a. the camp of the patriots and

   b. the camp of the traitors.

   .

   In the camp of the patriots we find,

   1. Haile Selassie

   2. Ethiopian nationalists

   3. the general Ethiopian public
   .

   In the camp of the traitors we find,

   1. Eritreans

   2. Leaders of the “Ethiopian Students Movement”

   3. EPRP

   4. Meison

   5. EPLF

   6. TPLF

   7. Tribalists

   8. Derg

   9. Likely traitors, among others, Germame Neway, Kassa Kebede, Mengistu Haile Mariam, Walelign Mekonnen, Meles Zenawi, Sebhat Nega and Isayas Afewerki.

   Remember, while many of us are in search of the truth about the CIA and western plot against Haile Selassie and Ethiopia, those peoples and groups you find on the list of the camp of the traitors are against us finding the truth, because that would expose them as the ones on the wrong side of history and as traitors. Of course the western foreign powers dont want also the truth to be revealed.

   That is the situation.

  • Anonymous says:

   So, in general now it is not that difficult to paint a rough picture how things were back in the 1960s G.C. and later.

   When the CIA (CIA = NAZI, white supremacist, jewish & catholic) in the late 1950s G.C. started a covert operation against Ethiopia following the order of Eisenhower, who regarded Ethiopia as a threat to USA national security due to the talks to found the OAU and activities to liberate Africa from western colonisation, it identified Eritreans as a key element in support of that covert operation. For that reason the CIA, through its ferenji American agent who was at the time an adviser of Haile Selassie and who died about a dozen years ago, tricked the Emperor to end the federation. The calculation of the CIA was likely that that would agitate the Eritreans, who held key positions in the Ethiopian government and were present in all provinces, and will make them a great help to CIA’s covert operation against Ethiopia.

   As we know most leading figures of the “Ethiopian Students Movement” were Eritreans.

   ====> December 1960 G.C.,

   Coup d’ etat

   * Remember here what Germame is supposed to have said at the end of the court hearings. Those words were likely those of the CIA. And with those words the CIA was announcing the begining of the “Ethiopian Students Movement” few years later.

   ====> November 1962 G.C.,

   As the first coup d’ etat failed CIA tr icked Haile Selassie to end the federation in order to use Eritreans as a catalyst for the 2nd attempt to overthrow Haile Selassie. Learning from it’s first failure the CIA will try to overthrow Haile Selassie this time through a “broad based movement”, with a civilian branch (the students) and a military branch (Derg)

   ====> 1965 G.C.,

   the begin of the “Ethiopian Students Movement”

   ====> November 1969 G.C.,

   CIA recruited Isayas

   http://www.hafash.org/index.php?option=com_content&id=2336:2013-01-09&Itemid=519

   • Anonymous says:

    Quote:

    ” The Americans told him indirectly that as they are worried that following the fall of the weakened government of Haile Selassie’s, there might come a military government, unfriendly to the United States, they were ready to ally themselves even with anti-unity secessionist forces. Indeed they stressed the point that they desired to ally themselves with an anti-socialist force committed to defend the Qagnew base as well as similar other American bases in the Red Sea. ”

    One would ask, how did the CIA know in 1969 G.C. that the Haile Selassie government will be replaced by a military government (in 1974 G.C.) ?

    Well, the answer is the CIA was planning and organizing the overthrow of Haile Selassie. At least since 1960 G.C..

    https://ethiopiansemay.blogspot.nl/2011/06/cia-in-africa-by-professor-aleme-eshete.html

 18. ደጃዝማች ሊዎንቴፍ says:

  መጻፉ ሸያጭ ላይ ምናምን ነገር ያለህ መሰለኝ እንጅ ለፕሮፌሰሩ የሚገባ ዝባዝንኬ የሚመጥን ጽሁፍ አልመሰለኝም። ፕሮፌሰሩን ካንተ ባላነሰ ሁኔታ የምናውቃቸው መሰለኝ። መግቢያህ ላይ ጠቀስ እንዳደረከው በእርግጥ ለኤርትራውያን ስስ ልብ አላቸውም ትግሬ በፍጹም አልተጠቀም ጭራሮ መሸጥ ነው የተረፈው እያሉ በተሰጣቸው ሚዲያ ሁሉ እንደ አረጋዊ በርሄ አስግድ ገ/ስላሴ አብረሀ ደስታ ዜጋን ሲያምሱ አያለሁ። በሀገራችን ሽማግሌን ማክበር የተሰራንበት ሁኖ ገፍተን አንሄድም እንጅ ፕሮፌሰር መስፍን በወንጀል የሚፈለጉ ሰው ነበሩ። ኢትዮጵያን ጥቢ ጥቢ ከተጫወቱባት ዜጋ አንዱ ናቸው። እንዳልከው ፕሮፌሰሩ ከወደ ሰሜን ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከመሞታቸው በፊት ይናዘዙ ይሆናል። አንተ ጸሀፊውና አከታለህ አጅበውኛል ያልከው ምሁር ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊ ነኝ ያለ ዜጋ ቁም ስቅሉን ሲያይ አፍህ ተሸብቦ ከምሁር እይታ አንጻር መጻፍ ልታሻሽጥ መጣህ ፕሮፌሰር መስፍን አማራ የለም ብሎ አበክሮ ተሟግቷል ሰልፉም ክጸረ አማራ ድርጅቶችና ግለሰቦች ሁኗል ስለዚህ የለም የተባለ ህዝብ ቢገደል ቢጋዝ ቢሰደድ ችግር የለውም ማንም ተጠያቂም አይሆንም የፍልስፍና ምንጩም ፕሮፌሰር መስፍን። አይ ማፈሪያ ያማራ ምሁራን በአረጋዊ በርሄ ሰየ አብረሀ አቅም ትሰግዱላቸዋላችሁ ተኮፍሳችሁ ቁጭ በሉ ነበልባል ወጣት አልፏችሁ ሂዷል።

Leave a Reply

Please answer this math question before submitting your comment: