(ሐገራዊ አጀንዳ) የዛሬ የሀገር ጥሪ ነው ! ኢሕአዴግ ከጅብ ጅማት የተሰራ ክራር ነው::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


(ሐገራዊ አጀንዳ) የዛሬ የሀገር ጥሪ ነው ! ኢሕአዴግ ከጅብ ጅማት የተሰራ ክራር ነው::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎Dictatorship‬ ‪#‎EthiopianHyna‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi – Ethiopian DJ – እሾህና አሜከላ ዙሪያችንን ከቦናል፡፡ ይሄ የሀገራችን ሀቅ ነው፡፡ ማማር ያለበት መንገድ፣ ህንፃው፣ ሪል ኢስቴቱ ብቻ አይደለም፡፡ ኢሕአዴግ ከጅብ ጅማት የተሰራ ክራር ነው ቅኝቱ ሁሉ ልብላው ልብላው ነው::ዋናውና ዋነኛው የህዝባችን ኑሮ ነው፡፡ ተመችቶኛል፣ ደልቶኛል ማለት ያበት ነዋሪው ህዝብ ነው! በግፍ ተበልቻለሁ፣ ተመዝብሬአለሁ ማለትም ያለበት ነዋሪው ህዝብ ነው፡፡ሌሎችን አሸንፍበታለሁ ያልነው ዘዴ አንዳንዴ መሸነፊያችን ሊሆን ይችላል፡፡ በርካታ ህዝብ ዘክሮ መክሮ የሚያመጣው ብልሃት አይታወቅም፡፡ ዋናው ነገር የሚዘክር የሚመክረውን ህዝብ መሰባሰብ፣ መምረጥና ማደራጀት መቻል ነው፡፡ ይህ ባልሆነበት ሁኔታ የተበታተነ የህዝብ ሐተታ እንጂ የሰከነ ዕምነት ማፍራት አንችልም፡፡ የአስተሳሰብ አንድነት (ሐገራዊ አጀንዳ) የዛሬ የሀገር ጥሪ ነው!

በሹመት ስም፣ በሀገር ሰላም ስም፣ በትራንስፎርሜሽን ስም፣ በኢንቬስተሮች ማበረታታት ስም፣ ዘራፊዎችን በማሳደድ ስም፣ በፋይናንስ፣ በገቢ አሰባሰብና የመሬት ቁጥጥር ጉዳይ ስም… የሚካሄዱ ምዝበራዎች ተጧጡፈው ቀጥለዋል::በሥልጣን ብልግናም፣ በመሬት ዘረፋም ፣ በታክስ ማጭበርበርም ፣ በኮንስትራክሽን ግዢም ፣ በሚዲያ ኢንዱስትሪ ሀሳዊ – ስብከትም ፣ የቦርድ አባልነትን ተገን በማድረግም፣ በሙልሙል ቢሮክራት መልክም ኢሕኣዴጋዊ ቅኝቱ ከጅብ ጅማት እንደተሰራ ክራር ልብላው ልብላው ብቻ ነው::

Minilik Salsawi's photo.

በሀገራችን የሚታየውን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ስናይ ኃምሌት ይከሰታል፡-
“…ኋላ ምን ሊታየኝ ኖሯል፣ ጊዜ ከፈተነው ሌላ
ምድር ዕፅዋት ብቻ አታበቅል፣ ያለሾህ ያላሜከላ
ወይንም የተፈጥሮ መልክ፣ ሲካበት ሞልቶ ድርጅቶ ብቻውን አደለም ከቶ
ግን እንደዚሁ እንደ ህንፃ፣ ላዩ በሰም አንፀባርቆ
አካባቢው በጌጥ ደምቆ
መሰረቱ ግን በግድፈት፣ በአገም ጠቀም ተደባብቆ
በመሀንዲስ ጥበብ ጉድለት፣ ወይ ባጉል መራቀቅ ዘፍቆ
ከስህተቱም፣ ከጥራቱም፣ ተቻችሎ፣ አለ ተጣብቆ”
ህንፃው ብቻውን ባዶ ነው፡፡ መሰረቱ የተዛባ ነው፡፡ መሀንዲሱ ስራውን በአገም – ጠቀም ሰርቶ አሳቡን ከወሰደ ቆይቷል፡፡ አካባቢያችን ጌጥ ብቻ ነው! እሾህና አሜከላ ዙሪያችንን ከቦናል፡፡ ይሄ የሀገራችን ሀቅ ነው፡፡የሃሳብ ስብስብ – addisadmassnews.com ድረ ገጽ ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬ ‪#‎AddisAdmass‬