ቃር (Heartburn) (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ቃር የምንለው ወይንም በህክምና አጠራሩ ሃርትበርን (Heartburn) በመባል የሚታወቀው የህመም አይነት ሲሆን አብዛኞችን የሚያጠቃ እና እጅግ የተለመደም ችግር ነው።

በደረት አካባቢ የማቃጠል ስሜት መሰማት በአብዛኛው ከምግብ በኃላ እና እንቅልፍ ስንተኛ የሚብስ ነው። ይህም የሚከሰተው የጨጓራ ውስጥ አሲድ ወደ ላይኛው የምግብ አስተላላፊ ቱቦ (esophagus) ሲገባ ነው።

✔ ለቃር ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች

* ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ
* ሽንኩርት
* ሲትረስ ያላቸው ምግቦች
* ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች
* ቸኮሌት
* የአልኮል መጠጦችን መውሰድ
* ካፊን ያላቸውን መጠጦች መውሰድ
* ከጥጋብ በላይ መመገብ
* ከመጠን ያለፈ ውፍረት
* ነፍሰጡርነት ናቸው።

✔ ሃኪምዎን ማማከር የሚገባው መቼ ነው

ቃር በአብዛኛው አመጋገብን በማስተካከል እና ቀስቃሽ ሁኔታዎችን በማስወገድ የሚድን ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የደረት ማቃጠል፣ ውጋት፣መጨምደድ ስሜት እና ወደ ትከሻ የሚሰራጭ የህመም ስሜት ከትንፋሽ ማጠር ጋር ከተከሰተ በአፋጣኝ ሃኪም ማማከር ተገቢ ነው ምክንያቱም የድንገተኛ ልብ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ነው።

✔ ከዚህ በተጨማሪ

* በሳምንት ውስጥ ከሁለት ጊዜ በላይ የሚያቅርዎ ከሆነ
* ለመዋጥ የሚችገሩ ከሆነ
* ማቅለሽለሽና ማስመለስ ካልዎት
* የምግብ ፍላጎት በማጣት ወይንም ለመመገብ በመቸገር ምክንያት የሰውነት ክብደትዎ ከቀነሰ ሃኪምዎን ማማከር ይኖርብዎታል።

✔ ቃርን ለማስታገስ መደረግ ያለባቸው የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች

* የሰውነት ክብደትዎን ማስተካከል
* ቃርን የሚይያስነሱ ምግቦችን አለመመገብ
* የአልኮል መጠጦችን አለመውሰድ
* ሲጋራን አለማጤስ
* በመኝታ ጊዜ ጭንቅላትዎን ከፍ ባለ ትራስ ላይ ማሳረፍ ናቸው።

ጤና ይስጥልኝ http://www.honeliat.com/what-are-symptoms-and-causes-of-he…/

heartburn-and-acid-reflux