በኦሮሚያ ክልል የተማሪዎች ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሏል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በኦሮሚያ ክልል የተማሪዎች ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሏል።
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎OPDO‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በወለጋ ዩንቨርስቲ የፌዴራል ፖሊስ በመግባት ተማሪዎች ላይ ኣስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ላይ ሲገኝ መብራቱን በማጥፋት ጨለማን ተገን በማድረግ ወደ ሴቶች መኝታ ክፍል ገብቶ ሴቶችን ክፉኛ እየደበደበ ይገኛል።

በወለጋ ጉሊሶ፣ጊዳሜ ቀለሜና ሆሮ ጉድሩ ኣሙሩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሰሜን ሸዋ ኣቦቴ ተማሪዎች ተቃውሞ ሲያሰሙ በነቀምት ወለጋ ዩንቨርስቲ ከፍተኛ ተቃውሞ ተነስቶ ተማሪዎች የአግኣዚ ወታደሮችን ጭካኔ በመሽሽ ወደ ኣከባቢው ደናማ ጫካ መደበቃቸው ታውቋል።በተለያዩ ትምሕርት ቤቶች ለመጀመሪያ ሲሚስተር ፈተና የገቡ ተማሪዎች እጃቸውን ወዳ ላይ በማጠላለፍ ተቃውሞ ሲገልጹ ተስተውሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግምገማ የተቀመጠው የኦሕዴድ ማእከላዊ ኮሚቴ ባለስልጣኖቹን ያባርራል ተብሎ ሲጠበቅ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር ኣቶ ሙክታር ከድር ምናልባት በፓርላማ ኣባሉ በኣቶ ባካሪ ሻላ ይተካሉ የሚል ግምት ሲኖር ይህ ግምገባ ኣቶ ኣባይ ጸሃዬ የክልሉን ምክር ቤት አንበትናለን ካሉት ዛቻ ጋር የተያያዘ መሆኑ ሲጠቆም በተላያየ ኣከባቢ ያሉ የኦሕዴድ ኣመራሮ ከስልጣናቸው ይባረራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Minilik Salsawi's photo.