በጉጂ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እየታደኑ እየታሰሩ መሆናቸው ተገለጸ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በጉጂ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እየታደኑ እየታሰሩ መሆናቸው ተገለጸ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ የዞንና የወረዳ አመራሮችና አባላት ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ከየቤታቸው እየታደኑ እየታሰሩ መሆናቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

በዞኑ የፓርቲው ሰብሳቢ አቶ ግርጃ ገቦውጮ ዛሬ የካቲት 03/2008 ዓ.ም እንደገለጹት ከቅዳሜ ጀምሮ ጉጂ ዞን ቦሬ ወረዳ ላይ ለእስር የተዳረጉት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት መምህር ጥላሁን አለቄ፣ መምህር ዮናስ ገልቱ እና አቶ ኤሊያስ ቶቶላ ናቸው፡፡ በእስር ላይ የሚገኙት አባላት ቤታቸው በፖሊስ መፈተሹም ታውቋል፡፡

አቶ ግርጃ እንደገለጹት ጉዴሳ ዋደሞ፣ ሽብሩ ጎዳና፣ ዮሃንስ ባልዲ፣ ወ/ሪት ፍሬ ገ/ህይወት፣ ሀጂ ኡመር ሸካ ደግሞ በፖሊስ ማዘዣ ወጥቶባቸው እየተፈለጉ የሚገኙት አባላት ናቸው፡፡

በዞኑ በሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ እየተደረገ ያለው እስር ምክንያት በኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰው የህዝብ የመብት ጥያቄ ንቅናቄ ላይ ‹‹የዞኑን ህዝብ ታደራጃላችሁ፣ መንግስትን ትቃወማላችሁ›› የሚል መሆኑን አቶ ግርጃ ገልጸዋል፡፡