‹‹ቤዛ እንሁን!›› ወገን ተርቧል፤ እንድረስለት! የበጎ ፈቃደኝነት ኮሚቴ ተቋቋመ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በትላንትናው እለት በገለፅነው መሰረት በሀገራችን በተከሰተው ቀውስ (ድርቅ/ርሃብ) ዙሪያ ‹‹ያገባኛል!›› የምንል ዜጎች በበጎፈቃደኝነት ኮሚቴ አቋቁመናል፡፡ ዛሬ ባደረግነው አስቸኳይ ስብሰባ የተገኙ 13 ሰዎች የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፈዋል፡፡

1. ሁላችንም እንደዜጋ ከራሳችን በመጀመር ሚናችንን መወጣት ይኖርብናል፡፡ በዚህም መሰረት ከእያንዳንዳችን በነፍስ ወከፍ በትንሹ ከ100 ብር በመጀመር እንድናዋጣ፤
2.
3. በዙሪያችን ያሉ ሰዎችን (ወዳጅ፣ ዘመድ፣ ቤተሰብ፣ ጎረቤት፣ ጓደኛ፣ የስራ ባልደረባ…..) በማስተባበር ለእነዚህ ወገኖቻችን አስቸኳይ የገንዘብና የቁሳቁስ እርዳታ ማሰባሰብ፤
4.
3. ቀጣይነት ያለው የገቢ ማሰባሰቢያ ስልቶች ተቀይሰው በአፋጣኝ ወደተግባር እንዲገባ፤
4. መንግስት የቅድሚያ ተነሳሽነት (initiative) ወስዶ ‹‹ብሔራዊ የእርዳታ ማስተባበሪያ ኮሚቴ›› በፍጥነት እንዲያቋቁም ግፊት ማድረግ፤

5. ከዓለም-ዓቀፍ የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች፣ በውጪ ሀገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፣ ከታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም አጋር ሊሆኑ ከሚችሉ ማንኛቸውም ተቋማት ጋር የቀረበ የስራ ግንኙነት በመፍጠር ለተጎዱ ወገኖቻችን በአስቸኳይ መድረስ፤
6.
7. እስካሁን ያሉና ወደፊትም ሊከሰቱ የሚችሉ ሁነቶችን እግር በእግር እየተከታተሉ ለሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወቅታዊ መረጃን ማድረስ፤
8.
7. የዚህን ሀገራዊ ቀውስ ሙሉ ገፅታ የሚያሳይና ለቀጣይም የአስቸኳይ እርዳታና ዘላቂ የምርምር ስራዎች ግብአት በሚሆን ደረጃ፤ መረጃዎችን ሰብስቦ በሰነድ፣ በምስል፣ በድምፅ አጠናቅሮና ሰንዶ በአንድ የመረጃ ቋት ማዕከል ማስቀመጥ፤

በመሆኑም ቅድሚያ የተሰጠው ገንዘብ የማሰባሰብ ሥራ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል፡፡ ለዚሁ ዓላማም በተወከሉ ሰዎች ስም፡-

ሀ. ወ/ት ሜሮን አዲስ ገብረፃዲቅ ለ. ወ/ት መስከረም ያረጋል ማህተመ ሐ. አቶ ሀብታሙ ምናለ ፍሰሐ …… በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራዳ ጊዮርጊስ ቅርንጫፍ የባንክ ሒሳብ ቁጥር (1000143645987) ተከፍቷል፡፡
ከዚህም በተጨማሪነት ኮሚቴውን በአመራርነት እንዲያገለግሉ ሰብሳቢ፣ ዋና ፀሐፊና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችን ምልዓተ-ጉባዔው መድቧል፡፡

Getachew Shiferaw's photo.

በዚህም መሰረት፡-
ሀ. ኤልያስ ገብሩ ጎዳና /ሰብሳቢ/ ለ. ኢዮኤል ፍሰሐ ዳምጤ /ዋና ፀሐፊ/
ሐ. አናንያ ሶሪ ጉታ /የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ/ ሆነው የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ተወስኗል፡፡
የምልዓተ-ጉባዔው አባላት ዝርዝር
1. ስለሺ ሐጎስ በርሔ
2. ሜሮን አዲስ ገብረፃዲቅ
3. ሐብታሙ ምናለ ፍሰሐ
4. ጋሻው መርሻ ይማም
5. በላይ ማናዬ ደመቀ
6. ዘሩባቤል ጌታቸው ዝቅአርጌ

7. ሰባህ ሙባረክ አወል
8. ጌታቸው ሽፈራው አንዳርጌ
9. ሮቤል አያሌው ሀይሌ
10. ኤልያስ ገብሩ ጎዳና
11. አናንያ ሶሪ ጉታ
12. ኢዮኤል ፍሰሐ ዳምጤ
13. መስከረም ያረጋል ማህተመ
በዚህ አጣዳፊ ‹‹ሀገራዊ ቀውስ›› የተነሳ ወገናችን የሆነው ኢትዮጵያዊ በየዕለቱ የሞትና የእርዛት አደጋን እየተጋፈጠ ነው፡፡ ከዚህ ቀውስ በአስቸኳይ ይወጣ ዘንድ ሁላችንም አለን በምንለው የሃሳብ፣ የገንዘብ፣ የቁሳቁስ፣ ወዘተ… ድጋፍ ልንረባረብ ይገባል! በመሆኑም ያላችሁን ማንኛውንም የመፍትሔ ሀሳብ በግልፅነት ታመላክቱን ዘንድ የዜግነት ድርሻችሁ ግድ ይላችኋል፡፡

አንድ ሆነን ለወገናችን እንድረስለት!!!

ሕዳር 04 ቀን 2008 ዓ.ም