ኢሕአዴግን ወደ መቃብር ለማውረድ ለትግሉ መቀጣጠል የእያንዳንዳችን ሚና በጽናት ይጠበቅብናል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ኢሕአዴግን ወደ መቃብር ለማውረድ ለትግሉ መቀጣጠል የእያንዳንዳችን ሚና በጽናት ይጠበቅብናል።
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎EthiopianOppositionparties‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) :- ከሕወሓት/ኢሕአዴግ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የጠበቃችሁ፤ ከሕወሓት/ኢሕአዴግ ሥልጣን መጋራት የፈለጋችሁ፤ ከሕወሓት/ኢሕአዴግ የእምነት፣ የፕሬስና የሃሳብ ነጻነት የጓጓችሁ፤ ‘ከሕወሓት/ኢሕአዴግ ጋር ተስማምቶ መሥራት ይቻላል’ የምትሉ፤ ተስፋ ቁረጡ። እንኳን አብሮ ለመሥራት ለመወዳደር እድል የማይሰጥ ፈሪ ድርጅት መሆኑን በይፋ አረጋግጧል።

ከሕወሓት/ኢሕአዴግ ጋር አንድ ነገር ብቻ ነው የሚቻለው፤ ከሕወሓት/ኢሕአዴግ በታች ሆኖ መሥራት። ጫማ እየላሱ ‘ጌታዬ!’ ማለት። ያንን የሚመርጥ የፖለቲካ ድርጅት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደፈለገ መንቀሳቀስና መሥራት ይችላል። ጥሩ ቢሮ ይሰጠዋል። ግዙፍ ባጀት ይመደብለታል። ዓመታዊ ጉባዔውን ሼራተን መደገስ ይችላል። በየምክንያቱ ቤተመንግሥት መግባት መብቱ ይሆናል። የመገናኛ ብዙሃን ችግር አይገጥመውም። እስር፣ ዛቻና ወከባ ሕልም ሆነው ይቀሩለታል። ‘ባሪያ የተቃዋሚ ድርጅት’ እየተባለም ይወደሳል።በምንም ተአምር አትታለሉ፤ ኢሕአዴግ በምንም ሁኔታ ሥልጣኑን አሳልፎ ለማንም አይሰጥም። ከተለያዩ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የፈለገ ዓይነት ስምምንነት ቢያደርግ፣ ሥልጣኑን ያጋራል ማለት አይደለም። ቁራሽ ሥልጣን ጠብቃችሁ ከሆነ ዳግም ተሞኝታችኋል። በዚህ አጋጣሚ ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር በሽብር የታወቀው ሕወሓት ከወደቀ የብአዴን እና ኦሕዴድ በህይወት መኖር ያበቃለታል።

ሕወሓት/ኢሕአዴግ ሃብትና ሥልጣን አያጋራም። ሁሌም የበላይ ሆኖ ሌሎችን መምራትና መቆጣጠር ብቻ ነው የሚፈልገው። ሌሎቹ እሱን እንዲያጅቡት ነው እቅዱ። ለሚቀጥሉት ብዙ ዓመታትም ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ለመታየት የሚያስችለውን እርምጃ ሁሉ ከመውሰድ አይመለስም። ሕወሓት/ኢሕአዴግ ገንዘብ ያላቸውን ዓለም አቀፍ ዘራፊዎች የሚሰበስበው፣ ከትላልቅ ሃገራት የጸጥታ ድርጅቶች ጋር የሚሰራው፣ ከአለም አቀፍ አሸብር እና ወንጀለኛ ድርጅቶች ጋር በጋራ የሚንቀሳቀሰው ፣ ሰላማዊ ዜጎችን እያፈሰ በአሸባርነት የሚወነጅለው ፣ ገንዘብ እየረጨ በየመንደሩ የራሱን ሚሊዮነር የሚቀፈቅፈውና ሰራዊቱን የሚያንጸው ለሃገር ብሎ አይደለም። ለአንድ ግልጽ ዓላማ ነው፤ ሥልጣኑን ላለማጋራት፤ ሥልጣን አጠገብ ማንንም ላለማድረስ! …..ያ መታመን ያለበት እውነት ነው። ስለዚህ ሕወሓት/ኢሕአደግን ወደ ከርሰ መቃብር ለመክተት በሙሉ ሃይል ተባብሮ በመታገል የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻነት ማረጋገጥ የእያንዳንዳችን ሃላፊነት እና ድርሻ መሆኑን መገንዘብ ግደታችን ነው። ሕወሓት/ኢሕአደግን ወደ መቃብር ለማውረድ ለትግሉ መቀጣጠል የእያንዳንዳችን ሚና በጽናት ይጠበቅብናል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!! ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.