እሳት ላይ ሕዝብን ጥዶ እያመሱ የሚደረግ የትግል ሽሚያ ይቁም!!! የእርስ በእርስ መነካከሱ አንድም የወያኔን እድሜ ማስረዘም ሲልም የሕዝብን ስቃይ ከማባባስ አያልፍም:: ‪


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


#‎Ethiopia‬ : እሳት ላይ ሕዝብን ጥዶ እያመሱ የሚደረግ የትግል ሽሚያ ይቁም!!!የእርስ በእርስ መነካከሱ አንድም የወያኔን እድሜ ማስረዘም ሲልም የሕዝብን ስቃይ ከማባባስ አያልፍም:: ‪

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በኢትዮጵያ ያለው የወያኔ አገዛዝ በሕዝቦች ላይ የሚያደርሰው በደል እጅግ ብዙና ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም እስከዛሬ በሃገሪቱ ከነበሩት አምባገነን አጼዎች እና ወታደራዊ አምባገነኖች በተሻለ መልኩ ወያነ በኢትዮጵያውያን ላይ ከባድ ወንጀል እየፈጸመ ይገኛል::በአሁኑ ወቅት አስፈላጊው እና ዋነናው ጉዳይ ይህንን አደገኛ የማፍያ አገዛዝ በሕዝብ ላይ የሚፈጽመው ወንጀል ከነአገዛዙ ለማስወገድ የሚደረጉ ትግሎችን ማቀናጀት ነው:: የተቀናጀ የተደራጀ ትግል ፋይዳው ስኬት ብቻ ነው ይህ ስከት ደሞ በተግባር እንዲተረጎም በጋራ ጭቆናን በመታገል ማስወገድ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል::ጭቆናን እናስወግዳለን ብለው ከተነሱ ሃገር ወዳድ ዜጎች ጀምሮ እስከ እናት ጡት ነካሾች ድረስ ስለ ነጻነት እና መብት እየጮኽ ይገኛሉ::እከሌ አገር ወዳድ ነው እከለ በኢትዮጵያ ሃብት ተምሮ ዛረ ላይ ተቀምጦ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር እና ባንድራ ይፈልጋል የሚል መከፋፈል ውስጥ ባንገባም ሁለቱም አካላት ግን በየፊናቸው ላይስማሙ ትስማምተው ፖለቲካዉን እያጦዙት ሲገኙ ሕዝቡ በመሃል እየተጎዳ በአምባገነኦች እየተረገጠ ቀጥሏል::

ከስድብ ፖለቲካ እና ከኩርኩም ሲልም ከሆያሆየ እና ከነፈሰበት መንፈስ ብሎም በሰዎች ማምለክ ላይ መመስረት ያልወጣው ፖለቲካችን በትግል ሽሚያ ላይ የሚያነጣጥረው ፖለቲካችን ለሕዝብ የፈየደው አንዳችም ጥቅም የለም::ሕዝቦች ብሶት ፈንቅሏቸው ለተቃውሞ በወጡ ጊዜ ሁሉ ባልዋሉበት ኩበት ለመልቀም የሚንጠራሩ ፖለቲከኞች የህዝብ ልጆች በተሰዉ ሰአት ሁሉ ካድሬዎችን በስማርፎት እና በዶላር በመደለል ከፎቶ እና ቭድዮ ውጪ ምንም ያልፈየዱ በሚዲያ ስም የተደበኩ ግልሰቦች እየተነሱ የሕዝብን ትግል የኛ ነው ቢሉ መስሚያችን ጥጥ ነው::ከዚሁ ሁሉ ግን በግራ እና ቀኝ ጽንፍ ቆሞ ከመነካከስ በቃላት ጦርነት ከመወራወር በሃገራዊ አጀንዳ ላይ የተሞረኮዘ ስራ ቢሰራ ትልቅ እመርታ ይኖረዋል::የሕዝብን ብሶት ሕዝብን ለመለያየት ከመጠቀም አሊያም ለድርጅት የፖለቲካ አጀንዳ ለማዋል ከመንጠራራት ተጠራርቶ እና ተመካክሮ በሰለጠነ ፖለቲካ በትልቅነት እና ቀና መንፈስ ስል ሕዝብ ለሕዝብ የነጻነት ጎህ መፈንጠቅ ችላ ሊባል አይገባም::ካልሆነ የሕዝብን ሰቆቃና የወያኔ ስልጣን ከማስረዘም አይታይም::

የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያውያን ችግር እንዲሁም ትግል የድርጅት አሊያም የሚዲያ ማድመቂያ እንዲሆን ማናችንም አንፈልግም::የምንታገለው እኮ እንዲህ አይነቱ እኩይ ተግባር እንዲቀር እው;;በአሁኑ ወቅት ማንም ሕዝብ በራሱ አነሳሽነት እና በገነፈለው ቁጣ ስም አጀንዳውን እንዲያስፈጽም ለማንም አንፈቅድለትም::በየቦታው የተነሱ የሕዝብ ተቃውሞዎች በነማን እንዴት እና ለምን እንደተነሱ ጠንቅቀን እናውቃለን::ቅጥረኛ ካድረእዎችን በደላልነት አስቀምጦ የሚለፍፍም ይሁም ባልዋለበት ኩበት የሚለቅም ያልሰለጠነ ፖለቲካ አንፈልግም::ይህ ከወያነ ድድብና አይለይም::ሊታስብበት ይገባል::የእርስ በእርስ መነካከሱ አንድም የወያኔን እድሜ ማስረዘም ሲልም የሕዝብን ስቃይ ከማባባስ አያልፍም::እሳት ላይ ሕዝብን ጥዶ እያመሱ የሚደረግ የትግል ሽሚያ ይቁም!!!‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬