እውነቱን ማወቅ ለሚፈልግ‬ – Yidnekachew Kebede – ሰማያዊ ፓርቲ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ክፍል አንድ
‪#‎እውነቱን_ማወቅ_ለሚፈልግ‬
ከቀናት በፊት በፓርቲያችን ውስጣዊ ጉዳይ ለመነጋገር ከኢ/ር ይልቃል ጋር ከቢሮ ውጪ ተገናኝተን ለመነጋገር ችለናል፡፡በዚህ አጋጣሚ እየሆነ ያለወ ነገር ዳር ቆሞ ከመመልከት ይልቅ በመነጋገር መፍትሔ ማምጣት ይቻላል የሚል ጽኑ እምነት ያለው፣በኢትዮጵያ የፖለቲካ ተሳትፎ እረጅም እድሜ የስቆጠረው ምርጥ ጓዳችን ግርማ በቀለ ፣የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል፡፡
ከኢ/ር ይልቃል ጋር በፓርቲያችን ውስጣዊ ችግሮቻችን ዙሪያ ሰፊ ውይይቶችን አድርገናል፣እኔም እሱ በጋራ የፓርቲያችን ውስጣዊ ችግሮች ምንድናቸው ? በማለት ለመለየት ጥረት አድርገናል ፣በሰማያዊ ውስጥ ለተፈጠረው ችግር እና እሱን ተከትሎት ለመጣው ውጤት ፣የሚያለያይ እና አንድ የሚያደርገን ሃሳብ እንደለን በውይይይታችን ያገኘነው ግባት ነበር፡፡
የነበረን የውይይት ጊዜ እጅግ በጣም ቆንጆ ተስፋ ሰጪ መሆኑን በወቅቱ ለነበርነው ለሦስታችንም በእኩል ስሜት የተጋራነው ሃቅ ነው፡፡ይህም በመሆኑ በቀጣይ ለፓርቲያችን ቅን አሳቢ የሆኑ ሰዎችን ጨምርን፤ ለይተን ባስቀመጥናቸው ችግሮቻችን ዙሪያ ለመነጋገር ተለዋጭ ቀጠሮ ይዘን ተለያይተናል፡፡በድጋሚ ተገናኝተን በችግሮቻችን ዙሪያ ሳንሰለች፣ትልቁን ዓላማችንን አስቀድመን፣ ለሁላችንም ገዢ የሆነ ሃሳብ ይዘን ወደፊት እንደምንጓዙ እምነቴ ጽኑ ነው፡፡
ለጹኑ እምነቴ መሠረት የሆነኝ አብዛኞቻችን ለ5 ዓመት ያህል በጣም በቅርበት ፖለቲካዊ ውሳኔዎችን በመወሰን እና በመስራት፣ ለ2 ዓመት ያህል በቅርብ ርቀት፣በአጣቃላይ ለ7 ዓመት በፖለቲካ የምንቀራረብ ጓዶች ነን፤ለ7 ዓመት ያሳለፍነው ጓዳዊ ቅርርብ ብዙ ነገር እንድንጋራ አስችሎናል፡፡ይህን ሐቅ ያልተረዱ ወይም ለመረዳት እራሳቸውን ያላዘጋጁ፣ የሐሳብ ትንሽነት እና የአዕምሮ ልምሻ ያጠቃቸው እነ ‹በቀቀን› “ይሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ” እንደሚበለው አይነት ነገር ሆነው፤ ገብያው ላይ ተኳኩለው ሣያቸው ፤በሀፍረታቸው እኔ ለእነሱ አዘንኩላቸው፡፡
የሆነው ይሁን እና ከኢ/ር ይልቃል ጋር ተነጋግረን በስተመጨረሻ ካለ ምንም ልዩነት የተስማማንበት ሃሳብ፤በፓርቲያችን ውስጥ የተከሰተው አነስተኛ ችግር እንደተጠበቀ ሆኖ፤ማንም ማንንም ፣በሐሳብ ልዩነት ብቻ ማንኛው ዓይነት ፍረጃ ውስጥ መገባት የለበትም፡፡ይሄ ፍረጃ ለማንም አይጠቅምም በማላት፤ ሁለታችንም ተስማምተን የተለያየንበት ዋና ጉዳይ ነው፡፡እኔና ይልቃል፣ ይሄ ሐሳብ ያስማማን ያለምክንያት አልነበረም፤የዛሬ 5 ዓመት አከባቢ ፤በአንድነት ፓርቲ ውስጥ የመርህ ጥሰት ተፈፅሞ ነበር፤አብዛኞቻችን “መርህ” ይከበር በማለት የፓርቲ ውስጠ ዴሞክራሲ መሠረት አድረገን እንንቀሳቀስ ነበር፤ይሁን እንጂ የተወሰኑ የአንድነት አባላት፣ “ለመርህ” ግድ የሌላቸው ፤የአብዘኞቻችንን ስም አጥፍተዋል፡፡ ግማሹን ግንቦት 7 የተቀረውን የወያኔ ሰላይ በማለት በከፍተኛ ሁኔታ ስማችንን ለማጥፋት ሞክረው ነበር፤እውነቱ ግን ይህ ስላልሆነ፣ እኛ አሸንፈናል ! በወቅቱ “የወያኔ ሰላይ” ይባሉ የነበሩቱ “ጓዶቻችን” እነማን እንደነበሩ፣ ይሄን ጉዳይ ለምናቅ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ፣ አሁን የሕዝብ ፓርቲ ሆኗአል፡፡ፓርቲያችን ከአምባገነን አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ የሚደረገውን ትግል ለመምራት እና ለማስተባበር አቅሙም ችሎታውም አለው ብዬ አምናለው፡፡እዚህ እምነት ላያ የሚያደርሰኝ የአመራሩ እና የአባላቱ ጥንካሬ እንዲሁም የሕዝብ ድጋፋ ጭምር እንደሆነ እረዳለው፡፡ በእንዲህ አይነት ደረጃ ላይ የሚገኝ ፓርቲ፣ በውስጡ የተቋማትና የአባላት ተጠያቂነት እና ግልጽነት፣ የፓርቲ መተዳዳሪያ ደንብ ማክበር እና ማስከበር፣ለመርህ መቆም፤ የፓርቲያችን ሚዛን የሚጠብቅ መተኪያ የማይገኝለት ቁልፍ ግዴታ ነው፡፡
ይህን ግዴታ በቅጡ ለመረዳት ያልፈቀዱ፣ቅሬታቸው ወይም ፀባቸው የሚጀመረው፣ ከፓርቲው ተቋማት፣ከደንብ እና ከመርህ ጋር ሄዶ መላተም እንደሆነ፣ ከእስካሁን የፖለቲካ ልምዴ የታዘብኩት ሐቅ ነው፡፡በእኛ ፓርቲ ውስጥ የመርህ እና የደንብ ጥሰት ዋና እና አሳሳቢ ችግር ነው ብዬ አላምንም፡፡ይህ ማለት ግን ምንም ነገር አልተከሰተም ማላት አይደለም፡፡

ከሰሞኑ በሰፊው ስለሚነገረው “የገንዘብ ብክነት ክስ” እና እሱን ተከትሎ ስለሚሰጡ አሰተያየቶች ለአሁን ቅድሚያ በመስጠት፤ለማህበራዊ ድረገጽ ፍጆታና ታይታ ሣይሆን፣ እንዲሁም ፖለቲካዊ ዋሾነት ሳይጣባኝ፣ አምላኬ እውነቱን እድናገር ይርዳኝ እያልኩ ፤የክሱን ይዘት ሳይሆን ሂደት በአጭሩ ግልጽ ለማደረግ ያቅሜን ልሞክር፡፡
በፓርቲያችን ወስጥ ከፋይናንስ አሰራር ጋር ተያይዞ ችግሮች አሉ ፤የሚል ጥቆማ እና ቅሬታ በስፋት ይነሳ ነበረ፤ይሄ ጉዳይ ከጥቆማና ከቅሬታ ባላፈ ወደ-ስም ማጥፋት ደረጃ ተደረሰ፤ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ መደረሱ በፓርቲያችን ውስጥ ለነበረ አባል ለማንም ግልጽ ነበር፤ በወቅቱ ይሄን ጉዳይ የሚያጣራ ኮሚቴ ይቋቋም ተብሎ በምክር ቤት ጥቅምት 7ቀን 2008 ዓ.ም ተወሰነ፡፡ አጣሪ ኮሚቴ በወቅቱ ከነበሩ 21 የምክር ቤት አባላት፣ በ18 ድምጽ ድጋፍ በ3 ድምጽ ተዓቅቦ እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡ ((ልብ በሎ 18 ድጋፍ ከሰጡት ውስጥ ሁለቱ ተከሳሾች ናቸው)) ፡፡ሕዳር 5 ቀን 2008 ዓ.ም በተደረገው የምክር ቤት ስብሳባ፣ ጥቅምት 7ቀን 2008 ዓ.ም የተያዘው ቃለ ጉባኤ ተነቦ በእለቱ በተገኙ አባላት በ22 ድምጽ ድጋፍ ቃለ ጉባሄ ጸድቋል፡፡
በምክር ቤት የተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ፤ ታሕሳስ 4 ቀን 2008 ዓ.ም ሥራው ካጠናቀቀ በኋላ በማጣራት ሂደት የደረሰበትን የመጨረሻ ሪፖርት ለምክር ቤቱ አቀረበ፡፡በቀረበው ሪፓርት የተቋቋመው ኮሚቴ ለአንድ ወር ባደረገው የማጣራት ሥራ 31 ገፅ ቃለ ጉባኤ፣36 ገፅ የቃል እና የጽሑፍ መልሶችን እንዲሁም 76 ገፅ ማስረጃዎች በጠቅላላው 143 ገፅ አባሪ ሰነዶችን እንዳሉት በእለቱ አስረድቷአል፡፡በሪፓርቱ መሠረት የገንዘብ ብክነት እንደነበርእና ለዚህም ተጠያቂ ናቸው፣ ያላቸውን በሪፓርቱ ለምክር ቤቱ ገልፆአል፡፡ምክር ቤቱ የቀረበለት ሪፓርት ካዳመጠ በኋላ ጥልቀት ያለው ሰፊ ውይይይት አድርጓአል፡፡ውይይቱም ፣ አዎ ድርጊቱን በግልም በጋራ ፈጽመናል፣ የቀረበው ሪፓርት ሚዛናዊነት ይጎድለዋል፣ሪፓርቱ ሙሉ በሙሉ ስም የሚያጠፋ ነው፣ አዎ በፓርቲያን ውስጥ የገንዘብ ብክነት አለ፣እና የመሳሰሉ ሃሳቦች ሪፓርቱን መነሻ በማድረግ የምክር ቤት አባላት በሰፊው ካነሳናቸው ሃሳቦች መካከል ይገኝበታል፡፡
በስተመጨረሻም አጣሪ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፓርት መሠረት፣ “የአጣሪ ኮሚቴው በሪፓርቱ ላይ ያቀረባቸውና ተፈጽሟል ያላቸው ድርጊቶች በዲስፕሊን የሚያስጠይቁ መሆናቸውን ምክር ቤቱ ስለተረዳው ፣ስህተቱን ፈጽመዋል የተባሉትን ግለሠቦች በማስቀረብ ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔ እንዲሰጥበት ለዲስፕሊን ኮሚቴ ይመራ” የሚል ሞሽን ቀርቦ በ21 የድጋፍ ድምጽ፣ በ1 ድምጸ ታዓቅቦ እና በ0 ተቃውሞ ምክር ቤቱ ክስ ይመስረት በማለት ወሰነ፡፡(( አሁንም በድጋሚ ልብ ማለት የሚያስፈልገው ከ 5 ተከሳሾች ውስጥ 3ቱ ድምጽ መስጠት የሚችሉ የምክር ቤት አባላት ናቸው፣በዚህም መሠረት ክሱ ይመስረት በማለት 3ቱም ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡)) ተከሳሾች ክስ ይመስረት በማላት ድጋፍ የሰጡበት ምክንያት ምን አልባት በክርክሩ ሂደት ሐቀኝነታውን እንደሚያረጋግጡ አምነው ሊሆን ይችላል ብዬ እገምታለው ወይም ደግሞ እነሱ የሚያውቁት የራሳቸው ምክንያት ይኖራቸው ይሆናል፡፡
በዚህም መሠረት የምክር ቤት አባላት ክስ ይመስረት አሉ፤እኔ ደግሞ የብሔራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ እንደመሆኔ መጠን ፣የምክር ቤቱ ውሳኔ ማስፈጸም ኃላፊነትና ግዴታሄ ነው፡፡ይህም በመሆኑ አጣሪ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፓርት ሳልጨምር ሳልቀንስ ፣ቅደም ተከትል በማስያዝ፣ የመሸኛ ደብዳቤ በማዘጋጀት፣ ምክር ቤቱ ያዘዘውን ወይም የወሰነውን ጉዳይ የፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በማድረግ ወደ ሥነሥርዓት ኮሜቴ እንዲቀርብ አድርጊያለው፡፡ለማስታወስ ያኸል 160000 ሺህ ብር ነው የባከነው ገንዘብ እየተባለ የሚወራው ወሬ ከይት እንደመጣ እኔ አላውቅም ፣ እውነታው ግን ይሄ አይደለም፡፡ከላይ ስለገለጽኳቸው የስብሰባ ሂደቶች በቪዲዮ የተቀረጹ ስለሆነ ትክክለኝነቱን ለማረጋገጥ አድካሚነት የለውም፡፡ስለቪዲዮ መቀረፅ በተመለከተ አንድ ነገር ትውስ አለኝ፤እኔና ጌታነህ በምክር ቤት ስብሰባ ስላነሳነው ሃሳብ አስመልክቶ አንድ የምክር ቤት አባል ፣ በተለይ እኔ ላይ አምጥቶ ያላልኩትን አልክ ብሎ ፣የእኔን ስም በማጥፋት የእሱ ስም ከፍ የሚል መስሎት የዋሸውን ውሽት ምን እንደሆነ፣እሱ እንዳለው የደምፅ ቅጂ ስላለ በቀጣይ እመለስበታለው ፡፡
ይህ ጉዳይ በእንዲህ ሁኔታ ላይ እያለ ፣ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ በእጅ ስልኬ ተደወለልኝ፣ የደወለችልኝም ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ ናት፤ከእኔ ጋር የነበራት የስልክ ቆይታ በጣም አጭር ነበር፤ “በፓርቲያችሁ ውስጥ የገንዘብ ምዝበራ ተፈፅሟል፣ የሚል የውስጥ ምንጮቻችን መረጃ አድረሰውናል፣ጉዳዩን ለማጣራት አቶ ስለሺ ጋር እንዲሁም ወ/ሪ ወይነሸት እና አቶ ጌታነህ ጋር ደውለን በጉዳዩ ዙሪያ አነጋጋረናል፤ እርሶስ ምን አሰተያየት አለዎት ?” በማለት ጠይቃኝ የመለስኩላት መልስ “ከፋይናንስ አሰራር ጋር ተያይዞ የታዩ ችግሮች ነበሩ፣ይሄን የሚያጣራ ኮሚቴ ተቃቋሞ የደረሰበትን የማጣራት ሪፓርቱን ለብሔራዊ ምክር ቤት አቅርቦአል፤ አሁን ጉዳዩ በሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ ተይዞአል፡፡” በማለት መለስኩላት፣ይህን እንደመለስኩላት በድጋሚ የጠየቀችኝ ጥያቄ “ አቶ ጌታነህ በምክር ቤት ስብሰባ ላይ የገንዘብ ብክነት መኖሩን አምነው ይቅርታ ጠይቀዋል ‹ የተባለው እውነት ነው › ?” በማለት በድጋሚ ጠየቀችኝ እኔም “አዎ እውነት ነው ይቅርታ ጠይቀዋል” ብዬ መልሻለው፤ከጋዜጠኛዋ ጋር የነበረኝ ቆይታ ይሄና ይሄ ብቻ ነው፡፡ከዚህ ውጪ የማውቀው ነገር የለም፡፡
ጋዜጣው ለንባብ ከበቃ በኋላ፣ይዞት በወጣው የዜና ዘገባ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጠ ይገኛል፡፡ለፓርቲያችን በጎውን በማሰብ፣ ገንቢ የሆነ ትችት የሰጡ አሉ፡፡ለእነዚህ አድናቆቴ ከፍ ያለ ነው!ይሁን እንጂ በፓርቲ ውስጥ የሚገኙ ተቋማትን እንዲሁም አባላትን፣ እጅግ በጣም ድፍረት በተሞላበት ሁኔታ ስም የሚያጠፉ ፣የእድሜ ብቻ ሣይሆን የሐሳብ ልጅነት የሚያሰቃያቸው፣እነ-ልጅ እና የልጅ “ጅል” ጓደኞች የሚያውቁትን እውነት ወደ-ጎን አድርገው፣ በሐሰት ፣እነ-እትና ወያኔ ናቸው፣ እነዚህ ደግሞ ደግሞ የግንቦት ሰባት አባል ናቸው፡፡ በማላት ስም ሲያወጡ ስመለከት ፤የተለመደው የዘፈን ቅኝት በተለመደው ቦታ፣ በአዲስ ዘፋኛ ሲዘፈን እንደማየትና መስማት፣ ፖለቲካችንም እንደዛው ሲሆንብን፤ ለእኔ አግራሞትን ባይሰጠኝም፣በልጆቹ ልጅነት የእውነት አዘንኩኝ፡፡
አንድ ቀልቡን በአግባቡ መሰብሰብ የማይችል ፣የአዕምሮ ዘገምተኛ ልጅ ግሩም የሚባል፤ በማያውቀው ጉዳይ ገብቶ ሲፈትፍት ፤ከትላንት ዛሬ እብደቱን ያረጋገጠበት ጹሑፍ በተደጋጋሚ በማህበራዊ ድረ-ገጹ ላይ ለጥፎ ሲያሰራጭ ነበረ አሁንም እንደዛው፤ከእሱ ይልቅ ይሄን እንዲያደርግ የቅርብ አማካሪ ሆነው በሚያገለግሉት በእኛ “ድኩማኖች” በጣም ነው ያፈርኩባቸው፡፡የአዕምሮ ዘገምተኛው ልጅ ጉርም እና መሰሎች ትክክለኛውን እውነት ፈረተው እና ሸሽተው፣ በሬ ወለደ ወሬቸውን፣ በማህበራዊ ድረገጽ አብዝተው መልቀቃቸው ፤እውነቱን ለማወቅ ለሚፈልግ የተሳሳተ መረጃ እንዳይሆን፣ ትክክልኛውን ነገር አንድ ብዬ ጀምሪያለው ሌላውም ነገር ይቀጥላል……….

Yidnekachew Kebede's photo.