የሌባ አይነ ደርቅ መልሶ ልብ ያድርቅ::በኢትዮጵያ ረሃብ አለ:: በኢትዮጵያ ድርቅም አለ::በድርቁም በረሃቡም የከፋ ሞት አለ::(ምንሊክ ሳልሳዊ)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የሌባ አይነ ደርቅ መልሶ ልብ ያድርቅ::በኢትዮጵያ ረሃብ አለ:: በኢትዮጵያ ድርቅም አለ::በድርቁም በረሃቡም የከፋ ሞት አለ::(ምንሊክ ሳልሳዊ) ‪#‎EthiopiaFamine‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi – አባወራ አይውጣልሽ ተብላ የተረገመች ሴት ወይዘሮ ይመስል ሃገራችን በሰከሩ ፖለቲከኞች እየተናወጠች ነው::የወያኔ ባለስልጣናት እና ጭፍሮቻቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ታማኝነት ካለው ትርጉም በወጣ የፈጠራ ትንታኔ በኢትዮጵያ ውስጥ የምግብ እጦትና እጥረት ስላስከተለውም ድርቅ እና (ረሃብ/የለም) ሲያብራሩ ሰንብተዋል፡፡ድርቅ እንጂ ረሃብ የለም እስከሚለው መደምደሚያ ተጉዘዋል::ስኬት አልባ ሆነው ነው እንጂ::የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት በአንድ ሕብረተሰቡ ውስጥ ረሃብ መኖሩን የሚያረጋግጠው መሠረታዊ ዕለታዊ ጉልበት ለማስገኘት አስፈላጊ የሆነውን የምግብ መጠን በመመገብ ቀላል ተግባራትን ለማከናወን የሚያበቃ ኃይል እንዳላቸው እና፤ ክብደታቸውም ላላቸው ቁመት በዝቅተኛ ስሌት ተመጣጣኝነት አለው ወይ? የሚለውን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ነው፡፡የተራቡ ሰዎች በአሜሪካም፤ በአውሮፓም፤ በአውስትራሊያም አሉ በማለት የሕዝባችንን መራብ፤ መታረዝና መጠለያ አጥቶ በየሜዳው መውደቅ ላይ የሚያላግጠው ጨካኝ አገዛዝ ሊወዳደሩ የማይችሉ ሁኔታዎችን በማወዳደር ላይ እንዳለ ሊገነዘበው ይገባል፡፡ይህም ስሜተ-ቢስ የፖለቲካ ብልጣብልጥነት ከመሆን አያልፍም::

ስለሆነም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ የሚያሳየው አርሶ አደሩ ያለችውንም ኩርማን መሬት በረሃብ ምክንያት ማረስ ያቃተውና የምግብ እጥረት ደግሞ በተለይም በህፃናት እና እናቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርስ ይታወቃል፤ የሕፃናት ዕድገት እንደሚቀጭጭ፤ የአእምሮአቸው እድገት እንደሚያዘግም፤ የሰውነት ተፈጥሮአዊ የመከላከያ ሃይል ባለመጎልበቱ በቀላሉ ለበሽታዎች ተጋላጭ የመሆን አደጋ እንደሚደርስባቸው፤ በረሃብ የሚጠቁ እናቶች ደግሞ የሚወልዷቸው ህፃናት ክብደታቸው አናሳ ስለሚሆን ለሞት እንደሚጋለጡ የተረጋገጡ መረጃዎች አሉ፡፡ ይህንን ሳይንሳዊ እውነታ “አንድም በረሃብ የሞተ ሰው የለም” ከሚለውና ሃላፊነት ከጐደለው የአገዛዙ አባባል ጋር ስናስተያየው፣ በኑሮ ምቾት የናወዙ ሙሰኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ማንነት መገንዘብ ይቻላል፤ ከዚህም በላይ በዜጐች ላይ የሚከሰተውን ሞት መንስኤውን መመርመር የጤና አገልግሎቱ አካል ባልሆነበት ሀገር፤ዜጎች “በረሃብ አልሞቱም” ብሎ በማን አለብኝነት ማወጃቸው መንግስታዊ ዝቅጠታቸውን ይመሰክራል፡፡

ሀገራችን ውስጥ በተከሰተው የረሃብ ጉዳይ ላይ መረጃና ማስረጃ ይቅረብ ከተባለ የመረጃው ምንጭ አንደኛውና ብቸኛው የችግሩ ሰለባ እየሆነ ያለው ሕዝባችን ነው፡፡ ይህ ትክክለኛ መረጃና ማስረጃ ሊገኝ የሚችለው በየአካባቢው ልማትን አስፋፍቻለሁ እያለ ለሹመትና ሽልማት ከሚሽቀዳደመው ሞራለቢስ፤ ሆድ አደር የኢህአዴግ ካድሬ ሪፖርት ሳይሆን ገለልተኛ የሆነ የባለሞያ ቡድን በቀጥታ ከሕዝቡ ውስጥ ገብቶ መረጃውን ሲሰበበስብ ነው፡፡ ስነ-ምግባር አልባ ካድሬውማ ከለጋሽ ሀገሮችና ድርጅቶች የተገኘውን ዕርዳታ ሁሉ ሽጦና በልቶ፣ የተረፈውን በረሃብ የተመቱ ዜጎችን በኢህአዴግ ደጋፊነትና ተቃዋሚነት በመፈረጅ ለፖለቲካ ድጋፍ መግዣነት በማዋሉ ለሚገጥመው የአድሎአዊነት ወንጀል እንደሌለበት ጋሃድ የወጣ ጉዳይ ነው::ሌላው በረሃብም ሆነ በሌሎች ማሕበራዊ ጉዳዮች ላይ የመረጃ ምንጭ የመገናኛ ብዙሃን አውታሮች መሆናቸው አጠያያቂ እንዳለመሆኑ፤ ቢቢሲ የሚባለው ዕውቅ የመገናኛ ባልደረቦች በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ያለውን ሁኔታ ተዟዙረው በመቃኘትና ተጨባጭ መረጃ በመሰብሰብ፤ ተደብቆ ያለው የረሃብ ሁኔታ የከፋ መሆኑን ለዓለም ህብረተሰብ ይፋ ማድረጋቸው፤ መንግሥት በጉዳዩ ላይ የሚያደርገውን ፖለቲካዊ መከላከል ሚዛን ማሳጣቱን ሁሉም ይገነዘበዋል፡፡

የምግብ እህል በራስ መቻል አረጋግጫለሁ የሚለው አገዛዙ የምግብ እህል ሲለምን ከለጋሽ አገሮች ሲማጸን እያስትዋልን ነው::እያያችሁ ላሞኛሁ የሚለው የሌባ አይነደረቅ ወያኔ ተረጂዎች በተመለከተ የሚሰጠው አሃዝ እና አለም አቀፍ ተቋማት የሚሰጡት አሀዝ ልዩነት አለው::አገዛዙ ተረጂው ሕዝብ ቁጥር ከ8.2ሚሊዮን በላይ አይበልጥም ሲል፤ የእርዳታ ድርጅቶች ግን ወደ 15 ሚሊዮን በላይ እየሆነ መሆኑን ተናግረዋል::የዕርዳታ ፈላጊው ቁጥር በአርሶ አደሩና በአርብቶ አደር በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚቀንስ አገዛዙ ሲተነብይ፤ የእርዳታ ሰጪዎች ቀመር ግን የአርብቶ አደሩ ተረጂ ቁጥር መቀነስ እንደማይችል ያሳያል፡፡ ይህ የተረጂው ቁጥር በስፋት ያለመቀነሱ እውነታ ከ11በመቶ በላይ የኢኮኖሚ ዕድገት አስመዘግባለሁ ከሚለው የወያኔ አገዛዝ የተጋነነ ፖለቲካዊ መረጃ ጋር ያለመጣጣሙ፣ በረሃብ የተጠቃውን ሕዝብ ለመታደግ በቂ የቅድሚያ ዝግጅት እንዳይደረግ ስላደረገ አንደምታው የከፋ ሆኗል::በኢትዮጵያ ረሃብ አለ:: በኢትዮጵያ ድርቅም አለ::በድርቁም በረሃቡም ሞት አለ:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.