የረሃቡ እና የድርቁ ምክንያት የዝናብ እጥረት ብቻ ሳትሆን ወያኔ የምትባል አረም ናት ሲሉ የአፋር ነዋሪ ገለጹ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


«ወያኔ» ብለው የሚጠሯት የዛፍ አይነት ለግጦሽ የሚጠቀሙት ሳር መሃል እየገባች ትበቅላለች፡፡ እሷ በበቀለችበት ቦታ ሁሉ ምንም ነገር አይበቅልም፤ ወይም ይደርቃል፡፡

የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በአፋር ክልል ስለተከሰተው ድርቅና ረሃብ፣ አቶ ሃሰን መሃመድ የተባሉ የክልሉ ነዋሪን በትላንትናው ምሽት አቅርበው ነበር፡፡ ጋዜጠኛዋ ጽዮን ግርማ ጥያቄዋን ታነሳለች፡፡

«በአከባቢው የተከሰተው ድርቅና ረሃብ ምክንያቱ ምንድን ነው?»
«1ኛ የዝናብ እጥረቱ ነው፡፡ 2ተኛ ወያኔ የሚባል ዛፍ አለ፡፡ ያ ዛፍ የበቀበለበት ቦታዎቹ ሳር የሚባል ነገር አይበቅልም፡፡ 2ተኛ የድርቁ ምክንያት እሷ ናት»

«ከመቼ ጀምሮ ነው ይሄ ወያኔ የሚባለው ዛፍ መብቀል የጀመረው?»
«ወያኔ ከመጣ ጀምሮ ነዋ! ከዚያ ሀገሩን በሙሉ አለበሰች፡፡ የአፈርን ሃገር በዛፉ አለበሰች፡፡ ከሃዋስ ጀምሮ እስከ አሰሙ ድረስ ይህች ዛፍ ሀገሩን ወረሰች፡፡ ጠቅላላ ሳር የሚባል ነገር ጠፋ፡፡ 1ኛ ድርቁ እሷ ነች፡፡ ሁለተኛ የዝናብ ማጣት ነው»

የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢዋ ጽዮን ግርማ እንዲህ ትላለች፡፡ «አቶ ሃሰን እንዳሉት የዝናብ እጥረቱ ከመከሰቱ በፊት የአከባቢው ነዋሪዎች «ወያኔ» ብለው የሚጠሯት የዛፍ አይነት ለግጦሽ የሚጠቀሙት ሳር መሃል እየገባች ትበቅላለች፡፡ እሷ በበቀለችበት ቦታ ሁሉ ምንም ነገር አይበቅልም፤ ወይም ይደርቃል፡፡ ከዚያ በኋላ ምንም አይነት ነገር በአከባቢው አይበቅልም፡፡»

አለም ተፈራ