የብኣዴን 35 የምስረታ በዓል ምክንያት መቐለ በሙዚቃ ድግስ እየተናወጠች ነው። ርሃብተኞችን ማሸበር ይቁም።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


መቐለ በሙዚቃ ድግስ እየተናወጠች ነው። ዛሬ እሁድ 12:00 ማታ መቐለ ከተማ ሮማናት ኣደባባይ ከፍተኛ ድምፅ ባላቸው ትላልቅ ማይክሮፎኖች የታጀበ የሙዚቃ ድግስ እየተደረገ ይገኛል።

Amdom Gebreslasie's photo.

የሙዚቃ ድግሱ የብኣዴን 35 የምስረታ በዓል ምክንያት ኣድርጎ የተደገ ሲሆን ዋና እስፖንሰሩ መቐለ ዩኒቨርስቲ ነው።

መቐለ ከተማ ከትግራይና ኣማራ ክልል ወረዳዎች በድርቅ ምክንያት የተሰደዱ ሰዎች ከቀን ወደቀን እየተሞላች ብትሆንም የሁለቱ ክልል ኣስተዳደሮች በልመና እየተሰማሩ ያሉትና በረሃብ እየሞቱ ላሉ ዜጎች ችላ ብለው ሚልዮኖች ብር ለክብረ በዓል፣ ለስብሰባ፣ ለተሃድሶና ኣበል ወጪ እያደረጉ ይገኛሉ።

ህዝቡ ረሃቡ፣ ጥሙና እርዛቱ እንዳይችል ጀሮ በሚበሳ ድምፅ ያደነቁሩታል። መቐለ ዩኒቨርስቲም በርሃብ እየሞተ ያለው 15 ሚልዮን ህዝብ ረስቶ የብኣዴን በዓል ስፓንሰር በመሆን ልማታዊነቱ እየጎላ፣ ህዝባዊነቱ እየላላ እየሄደ ነው።

ኢህኣዴግ ሆይ … ህዝቡ በረሃብ እየሞተ ርሃቡን ችሎ ዝም ብሎሃል። ኣንተግን ጥጋብህ መቻል ኣቅቶህ እያውደለደልክ ነው።

እስቲ የሰው ሂወት ማዳን ፍላጎት ቢሳንህ እንኳን እየተከተልክ ኣታሸብረው።

‪#‎ETHIOPIA_Famine‬.

‪#‎ክፉ_ቀን‬

‪#‎ዘበን_ኣካሒዳ‬

Amdom Gebreslasie's photo.
Amdom Gebreslasie's photo.