የወሲብ እርካታን/ፍላጎት ማጣት (በዶር ቤተል ደረጀ – የማህፀን እና ጽንስ ስፔሺያሊስት)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ወሲብ ፈጣሪ ለሰው ልጆች ካደላቸው ተፈጥሮአዊ እርካታ ማግኛ መንገዶች አንዱ ነው፡፡ በአግባቡ ከተጠቀሙበት።

የወሲብ እርካታን/ፍላጎት የማጣት ችግር በሁለቱም ፆታዎች ሊታይ የሚችል ሲሆን በባህልና በልማድ ምክንያቶች በይፋ አይወራም። በዚህ ምክንያት ስንቱ እደተቸገረ ስንቱ ትዳሩ እንደፈረሰ ቤቱ ይቁጠረው።

ይህ ችግር በተለምዶ ‹‹ስንፈተ ወሲብ›› ተብሎ ቢጠራም ቃሉ ክብረ-ነክ ነው ብዬ ስላሰብኩ የወሲብ እርካታን ማጣት/ፍላጎት የሚለውን ቃል ተጠቅሜአለሁ።

ጤናማ የሆነ ወሲባዊ ግንኙነት አምስት ደረጃዎች አሉት፡፡ እነርሱም፦ ፍላጎት፣ መነቃቃት/ መቆም፣ የዘር መፍሰስ(ለወንዶች)፣ እርካታ እና ወደመጀመሪያው ሁኔታ መመለስ ናቸው።

Dr Bethel ዶ/ር ቤቴል ደረጄ's photo.

የችግሩ ዓይነቶች

1. ፍላጎት ማጣት
2. የመነቃቃት/ የመቆም ችግር
3. የዘር መፍሰስ ችግር(Ejaculation)
4. የእርካታ ችግር

የችግሩ መንስኤዎች

1. ጭንቀት (በሥራ መወጠር፣ መድከም፣ ድብርት)
2. የዕድሜ መግፋት
3. ከመጠን ያለፈ ውፍረት
4. ለረዥም ጊዜ የቆየ ህመም
5. ከዚህ በፊት የደረሰ የወሲብ ጥቃት
6. አልኮል፣ ሲጋራ፣ ጫት የመሳሰሉትን መጠቀም
7. ለሌላ ሕመም የሚወሰዱ መድኃኒቶች
8. መካንነት
9. በከዚህ በተጨማሪም እደየችግሮቹ ዓይነቶች የተለያዩ ሌሎች መንስኤዎች ይኖራሉ።

በሚቀጥለው ጽሑፌ የመፍትሔ ሃሳቦችን ይዤ እመለሳለሁ፡፡

ቸር እንሰንብት