የጆሮ ሕመም(Ear Pain) (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የጆሮ ሕመም በአብዛኛው በልጆች ላይ የሚከሰት ሲሆን በአዋቂዎች ላይም ይታያል፡፡ የሕመሙ ዓይነት አልፎ አልፎ የሚመጣ ወይንም ዘላቂ የሆነ ሊሆን የሚችል ሲሆን በአንደኛው ጆሮ ብቻ አልያም በሁለቱም ጆሮዎች ሊከሰት ይችላል፡፡

✔ የጆሮ ሕመም መከሰት ምክንያቶች

የጆሮ ሕመም በራሱ በጆሮ ላይ በሚደርስ ችግር እና በጆሮ አካባቢ በሚከሰቱ ችግሮች ምክንያት ሊመጣ ይችላል፡፡

• በጆሮ ኢንፌክሽን ምክንያት
• በጆሮ ላይ የደረሰ ጉዳት (ለማፅዳት በመሞከር)
• የጉሮሮ ኢንፌክሽን
• የመንገጭላ ሕመም
• በጥርስ ላይ የሚገኝ ኢንፌክሽን
• በጆሮ አካባቢ የሚገኙ ነርቮች ሕመም ናቸው፡፡

✔ የጆሮ ሕመም ሕክምና

የሕመም ማስታገሻ መድኃኒት መጠቀም የሚችሉ ቢሆንም ወደ ሕክምና ማዕከል በመሄድ የጆሮ ሕመሙ የተከሰተበትን ምክንያት በምርመራ ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡

በኢንፌክሽን ምክንያት የመጣ ከሆነ በሐኪም በሚታዘዝ ፀረ ባክቴሪያ የሚድን ይሆናል፡፡

ጤና ይስጥልኝ http://www.honeliat.com/here-is-what-you-need-to-know-abou…/