ድምፃችን ይሰማ : በዚህ ሳምንት ሕዝባዊ ስራዎች ይኖሩናል!‪ የትግላችን መለያ ይፋ ይሆናል! የማህበራዊ ቦይኮት የትብብር መንፈግ ዘመቻችንን እንጀምራለን!


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በዚህ ሳምንት ሕዝባዊ ስራዎች ይኖሩናል!

=== ሰኞ ጳጉሜ 2/2007 ===

የስራ ካላንደራችንን ላልደረሳቸው ሁሉ በማዳረስ እንረባረብ! -======

ድምፃችን ይሰማ :- 1/ ነገ ማክሰኞ ጳጉሜ 2/2007 የትግላችን መለያ ይፋ ይሆናል!
ለአራት አመታት ያክል በሰላማዊነት እና ሕጋዊነት የቆየው ትግላችን ሊገለጽበት እና ታጋዮችንም ለአንድ ዓላማ የተሰለፉ መሆናቸውን በማስታወቅ በጋራ የሚግባቡበት የትግል መለያ ምልክት መዘጋጀቱ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በነገው እለት ይኸው የትግላችን መለያ ይፋ የሚደረግ ይሆናል – ኢንሻአላህ!

2/ ረቡእ ጳጉሜ 4/2007 የማህበራዊ ቦይኮት ዘመቻችንን እንጀምራለን!
ማህበራዊ ቦይኮት በታጋዩ ህዝብ ላይ እንቅፋት የሆኑ የበደል አጋሮች ላይ ከጸረ ሕዝብ እና ጸረ ሕገ መንግስት እኩይ ተግባራቸው ይታቀቡ ዘንድ የምንተገብረው የሰላማዊ ትግል አንዱ ስልት የሆነ ስራ ነው፡፡ ስራው ይፋ ሆኖ የሚጀመረው እለተ ረቡእ ሲሆን ዝርዝር አፈጻጸም እና መረጃው በወቅቱ የሚገለጽ ይሆናል – ኢንሻአላህ!

3/ አርብ ጳጉሜ 6/2007 የትብብር መንፈግ ዘመቻ ይኖረናል!
የትብብር መንፈግ ስልት የቀጣይ ትግላችን ዋና መገለጫ እንደሚሆን መገለጹ ይታወሳል፡፡ በዚሁ መሰረት እስካሁን በተወሰነ መልኩ ስራ የተሰራ ሲሆን ይህንንም አጠናክረን የምንቀጥልበት አተገባበር እለተ አርብ ይፋ የሚደረግ ይሆናል – ኢንሻአላህ!

የተጠቀሱት ስራዎች በዚህ ሳምንት ቢጀመሩም ተከታታይ ስራ እና ርብርብ የሚጠይቁ በመሆናቸው ሁላችንም ላልደረሳቸው በማዳረስ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ እንጠባበቅ ዘንድ አደራ እንላለን፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

Minilik Salsawi's photo.