ፓፓያ እና የጤና ጥቅሞቹ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ፓፓያ በሆድ ውስጥ የሚገኙ ትላትሎችን ለማጥፋት እና የጨጓራን አሲድነት ይቀንሳል፡፡
የፓፓያ ጁስ መጠጣትን ልምድ ማድረግ በአንጀት ውስጥ የሚፈጠርን ኢንፌክሽን እና ጎጂ ፈሳሽ ጠርጎ ያወጣል፡፡

ፓፓያ ዝቅተኛ የካሎሪ እና ከፍተኛ የጠቃሚ ምግብ ይዘት ስላለው በውፍረት መቀነስ ሂደት ውስጥ ላሉ ሰዎች አስተዋጽዖው የላቀ ነው፡፡

ፓፓያ የጸረ ካንሰር እና የሰውነት መቆጣትን የሚቀንስ ባህሪ አለው፡፡ ይህ የሰውነት መቆጣትን የሚቀንስ ባህሪ በማንኛውም የሰውነታችን መገጣጠሚያ ላይ ለሚደርስ ህመም /Arthritis/ እና የአጥንት መሳሳት /Osteoporosis/ ለመቀነስ ይረዳል፡፡

ፓፓያ ፎረፎርን በመከላከል ጤናማ ጸጉር እንዲኖረን ስለሚያግዝ በተጨማሪ ከፓፓያ የተሰሩ የጸጉር ማስዋቢያ ምርቶችን መጠቀም ይመረጣል፡፡

ፓፓያ በውስጡ ፕሮቲዮላይቲክ የተባለ ኢንዛይም ምንጭ ሲሆን ካለ እድሜ የሚመጣን የቆዳ መሸብሸብን ይከላከላል፡፡ እንዲሁም ፓፔን የተባለ ኢንዛይም የምግብ መፈጨት ሂደትን በማገዝ ብሎም የአንጀት ካንሰር የመከሰት እድልን ይቀንሳል፡፡

ፓፓያ አርጀኒን የተባለን ንጥረ ነገር ሲኖረው ይህም የወንድ ልጅን መሀንነት ይከላከላል፡፡
ፓፓያ በቫይታሚን ኤ’ ሲ እና ኢ የበለጸገ በመሆኑ የኮሌስትሮል መጠንን ለመቀነስ በተጨማሪም በስ£ር ምክንያት የሚመጣን የልብ ህመምን ይከላከላል፡፡

ፓፓያን መጠቀም ልምድ አድርገን ጤናችንን እንጠብቅ!!!

Salim Jibril's photo.