የቂሊንጦ ኃላፊዎች ክሳቸው ተነስቶላቸዋል የተባሉ ተከሳሾችን “እናያለን! አብይ መጥቶ ያስፈታችኋል” እንዳሏቸው ለማወቅ ተችሏል

የትህነግ/ህወሓት ታጋዮች እብሪት!

“እናያለን! አብይ መጥቶ ያስፈታችሁ!” የቂሊንጦ አዛዦች

የቂሊንጦ ኃላፊዎች የሆኑት ትህነግ/ህወሓት ታጋዮች በቂሊንጦ ቃጠሎ ሰበብ ተከስሰው ክሳቸው ተነስቶላቸዋል የተባሉ ተከሳሾችን “እናያለን! አብይ መጥቶ ያስፈታችኋል” እንዳሏቸው ለማወቅ ተችሏል።

ዶክተር አብይ በቂሊንጦ በር ዘጊና ከፋች ታጋዮችንም እንደ እነ አባይ ፀሀዬ ካላራገፉ እንዲህ እየተሰደቡ መቀጠላቸው ነው። “እናያለን! አብይ መጥቶ ያስፈታችሁ!” እያሉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያላቸውን ንቀት በግልፅ የሚናገሩት ሰዎች መካከል ኮማንደርነት ማዕረግ ተሸክመው ስማቸውንንም መፃፍ የማይችሉ አሉ። ዘሩንና ወሃኪምን መጥቀስ ይቻላል።