የአስራ አራት አመቱ ታዳጊ የአበጥር ወርቁ ጉዳይ በአማራ ላይ የሚሰሩ ሴራ ፣ ተንኮልና ደባ አንዱ ማሳያ ነው።

የአስራ አራት አመቱ ታዳጊ የአበጥር ወርቁ ጉዳይ በአማራ ላይ የሚሰሩ ሴራ ፣ ተንኮልና ደባ አንዱ ማሳያ ነው።Minilik Salsawi
 
ወያኔና ሻእቢያ አማራ ታሪካዊ ጠላታቸው እንደሆነ ከመናገር አልፈው በተግባር አማራን እያሳደዱ እየገደሉ አያፈናቀሉና ኢሰብዓዊ ድርጊት እየፈጸሙበት ይገናል። እንዲሁም በነሱ ድጋፍ የሚተዳደሩና ቀለብ የሚሰፈርላቸው ሚዲያዎች ስለ ኣማራው ጉዳይ አንድም ትንፍሽ ላለማለት ተማምለዋል።
 
ሆን ተብሎ በአማራ ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በገሃድና በድብቅ እየተደረገበት ነው። ይህ ጉዳይ በጣም አሳሳቢ ነው። በአማራ ስም ከመነገድና አማራውን ከማስገደል ከማሳሰር ጀምሮ በአማራው ላይ መንግስታዊ ወንጀል ተፈጽሟል። ይህ መንግስታዊ ሽብር በአማራ ላይ ሲፈጸም ከመንግስት ባለስልጣናት ጀምሮ እስከ ተቃዋሚ ነን ባዮች ድረስ የዚሁ ግፍ ተባባሪ ሆነዋል።
 
በቤንሻንጉል ጉምዝ በ አማራ ላይ የሚፈጸመው ግፍ ምስክር ነው። አማራው ከመፈናቀል ጀምሮ እስከ መታረድ ሲደርስበት ለመሸፋፈንና አድበስብሶ ለማስቀረት የሚደረገው ሙከራ ነገ ሃገሪቷ ላይ ከባድ አደጋ ያመጣል። የአስራ አራት አመቱ የአበጥር ወርቁ ጉዳይ የዚሁ ሴራ ተንኮልና ደባ አንዱ ማሳያ ነው። #MinilikSalsawi