በዳንጎቴ ላይ የተፈፀመው የግድያ ሴራ ሕወሓት በንግድ ድርጅቶቿ በኩል የተቆጣጠረችው የኢኮኖሚ የበላይነት ለኪሳራ እንዳይዳረግ የፈፀመችው ደባ ነው።

በዳንጎቴ ላይ የተፈፀመው የግድያ ሴራ ሕወሓት በንግድ ድርጅቶቿ በኩል የተቆጣጠረችው የኢኮኖሚ የበላይነት ለኪሳራ እንዳይዳረግ የፈፀመችው ደባ ነው።

ሕወሓት ወንጀሏን በሹፌሮቹና በቅጥር ድርጅቶቻቸው ላይ ለማሳበብና ግድያው የተፈፀመው ከአስተዳደር ችግር ጋር ነው ለማሰኘት እየተራወጠች ነው ። ኃላፊውና የስራ ባልደረቦቹ የተገደሉት ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ አይደለችም በማለት ዳንጎቴን ጨምሮ የውጪ ማኑፋክቸሮች ሀገሪቷን ጥለው እንዲወጡ ጫና እንዲፈጥር በሕወሓት የተሸረበ የመጀመሪያ ዙር ሴራ ነው።

ካሁን ቀደምም የሕዝብን ንቅናቄ ተከትለው በተለያዩ የውጪ ካምፓኒዎች ላይ አደጋ ደርሶ በሕዝብ እንዲሳበብ የተፈፀመ ሴራ ሊኖር ይችላል ፤ ባለፈው ሰሞን የኒዘርላድ ኤምባሲ አቶ ለማ መገርሳን በኦፊሺያል ያናገረው በኢንቨስተር ዜጎቹና ንብረታቸው ላይ ሊደርስ ከሚችል ጥቃት አስመልክቶ መሆኑ አይዘነጋም ። ሕወሓት በቀጣይነት ራሷን ከፖለቲካና ከኢኮኖሚ ኪሳራ ለማዳን የማትፈነቅለው ሴራ ስለሌለ ቀድሞ መጠንቀቁ ይበጃል ። ምንሊክ ሳልሳዊ