የዳንጎቴ ስራ አስኪያጅ የተገደለው በደህንነቱ ሚኒስትር ጌታቸው አሰፋ ትእዛዝ መሆኑ መረጃዎች ጠቆሙ።

የዳንጎቴ ስራ አስኪያጅ የተገደለው በደህንነቱ ሚኒስትር ጌታቸው አሰፋ ትእዛዝ መሆኑ መረጃዎች ጠቆሙ። (ምንሊክ ሳልሳዊ)

የደህንነቱ ሚኒስትር ጌታቸው አሰፋ በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የኢንቨስትመት ትልልቅ ፋብሪካዎችና የቢዝነስ ተቋማት ውስጥ ባለ አክሲዮንና የጥቅም ተካፋይ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ ከደህንነት ሚኒስትሩ በተጨማሪ በዙሪያቸው የሚገኙ የሕወሃት ባለስልጣናትም በተለይ በውጪ ኢንቨስተሮች በሚንቀሳቀሱ የንግድ ተቋማትና ፋብሪካዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሃገርን ገንዘብ በድብቅ ኢንቨስት በማድረግ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ ነው፤ ከነዚህም አንዱ የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ነው።

የፋብሪካው ባለቤትም ከደህንነት ሚኒስትሩ ጋር ተባባሪ መሆናቸውን ምንጮቹ ይናገራሉ። የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ባለቤት ራሳቸው በግድያው እጃቸው ይኖርበታል የሚሉት ምንጮቹ ካሁን ቀደምም ከሁለት አመት በፊት ኢንቨስተሩ የድርጅቴን ምስጢር አባክነዋል ያሏቸውን የዳንጎቴ ኢንዱስትሪያል ሊሚትድ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑትን ግለሰብ ከድርጅታቸውና ከናይጄሪያ የደህንነት ባለስልጣናት ጋር በመተባበር ማስገደላቸውን ጠቁመዋል።

የፋብሪካው ባለቤትም ደም የለመዱ ማኔጅመቶቻቸውን ቀንጥሰው መጣል የለመዱ ናቸው ይላሉ የደህንነት ምንጮቻችን። በዚህ ፋብሪካ ውስጥ በአቶ ሙልጌታ ተስፋኪሮስ ስም የተመዘገበው ሙለር ሪያልስቴት የሚባለው የደህንነት ሚኒስትሩ የንግድ ድርጅት ባለ አክሲዮን ሲሆን ለድርጅቱም የሰራተኛ ቅጥር የሚያስፈጽሙት የግል ካምፓኒዎች የደህንነት ሚኒስትሩና የወዳጆቻቸው መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል።

በዳንጎቴ የሲሚንቶ ፋብሪካ ውስጥ ድርሻ ያላቸው የሕወሃት ባለስልጣናት ከስራ አስኪያጁ ጋር በተለያየ ጊዜ የጥቅም ግጭት ከማድረጋቸውም በተጨማሪ ፋብሪካውን በተመለከተ የኦሮሚያ ክልል መስተዳደር የጠየቀው ሰነድ እንዳይሰጥ ባለስልጣናት ተፅእኖ ቢፈጥሩም ስራ አስኪያጁ አሳልፈው በመስጠታቸው እንዲሁም ጸሃፊያቸው የዚሁ ተባባሪ በመሆኗ ሊገደሉ ችለዋል። ሹፌሩም የደህንነት ቢሮ በስራ አስኪያጁ ላይ ስለላ እንዲያደርግ የታዘዘና ሲሰልል የነበረ ሲሆን ይህንኑ ምስጢር እንዳያወጣ አብሮ መገደሉን የድህንነት ምንጮቹ ጠቁመዋል።ግድያውን ከአስተዳደር ችግሮች ጋር ማያያዝ የሐሰት ክስ በሰራተኞች ላይ መስርቶ ጉዳዩን ለማድበስበስ እየተሞከረ ሲሆን በዳንጎቴ ውስጥ ያለው የአስተዳደር ችግር ለዚህ ግድያ የማያበቃ መሆኑን ምንጮቹ ተናግረዋል። #ምንሊክሳልሳዊ