13ኛው የአማራ ክልል ዝክረ ኪነ ጥበባት እና የባህል ፌስቲቫል

በባህር ዳር ከተማ  ሲካሄድ የሰነበተው 13ኛው የአማራ ክልል ዝክረ ኪነ ጥበባት እና የባህል ፌስቲቫል ዛሬ ተጠናቀቀ። ካለፈው እሁድ ጀምሮ በተካሄደው ፌስቲቫል በክልሉ የሚኖሩ የተለያዩ ማህበረሰቦች ባህላቸውን እና ትውፊታቸውን አቅርበዋል።