የቡሩንዲ ሬፈረንደም

በቡሩንዲ ፕሬዚደንት ፒየር ንኩሩንዚዛ እንደገና ለር/ብሔርነት እንዲወዳደሩ ሲባል በሕገ መንግሥቱ ላይ በቀረበው ማሻሻያ ላይ በዛሬው ዕለት ውሳኔ ሕዝብ እየተካሄደ ነው። ውሳኔ ሕዝቡ ከጎርጎሪዮሳዊው 2005 ጀምሮ ሀገሪቱን በመምራት ላይ ያሉት ንኩሩንዚዛ ለተጨማሪ የስልጣን ዘመን እንደሚወዳደሩ ካስታወቁ ከሶስት ዓመት በኋላ ነው የተካሄደው።