የቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቃዮች ቅሬታ

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው ባህር ዳር በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን የተጠለሉ ከ160 የሚበልሱ ሰዎች መንግሥት በክልላቸው ሊያቋቁማቸው ስላልቻለ ቅሬታ እያቀረቡ ነው። ባህር ዳር በገቡበት የመጀመሪያዎቹ ቀናት ከመንግሥት የምግብ ድጋፍ እንደተደረገላቸው ተናግረዋል።