በአደርቃይ የተከሰተው ግጭት መቀጠሉ ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 9/2010) በሰሜን ጎንደር ዞን አደርቃይ የተከሰተው ግጭት መቀጠሉ ተገለጸ። ዛሬም በማይጋባ ወንዝ አካባቢ በሚገኘው የወርቅ ማውጣት ስራ በተሰማሩ ሰዎች የተነሳው ግጭት በመከላከያ ሰራዊት የሚደገፉ የትግራይ ሚሊሺያዎች ጣልቃ መግባታቸውን ተከትሎ አድማሱን በማስፋት መቀጠሉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በግጭቱ ምክንያት በአደርቃይ