የሐበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ ማኔጅመንት የተደራጁ ሀይሎች ማስፈራሪያና ዛቻ እያደረሱበት ነው ተባለ ።

የሀበሻ ሲሚንቶ ማኔጅመንት ማስፈራረያ፣ ግድያና ዛቻ በተደራጁ ኃይሎች እየደረሰበት መሆኑ ታውቋል  በዚሁም ምክንያት ፋብሪካው በተደጋጋሚ ምርት ለማቆም ተገዶ ነበር፡፡ ሀበሻ የሚለውን “የነፍጠኛ” ስያሜ ጭምር እንዲቀይር ማስጠንቀቂያ ደርሶታል፡፡ ይህ ኮማንድ ፖስቱን መሸሸጊያ አድርጎ ወንጀል የሚሰራው ቡድን ከሕወሓት ደህንነት ቢሮ ድጋፍ እንዳለው ይነገራል።

የዳንጎቴ ማናጀር ከተገደሉ በኃላ የወጡ መረጃዎች እንደጠቆሙት ከ4 ወር በፊት የዳንጎቴ ስሚንቶ ህንዳዊው ፋይናንስ ማናጀር ቢሮቸው ድረስ በመሄድ ለሞት የሚያበቃ ያክል በተደራጁ ወጣቶች ገንዘብ ካለከፈልከን በሚል ድብደባ ደረሶባቸው ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር ሄደዋል።ምንሊክ ሳልሳዊ ።