በሳዑድ አረብያ ጠ/ሚንስትሩ በህክምና ስህተት እስካሁን ድረስ መናገር የማይችለውን ህጻን እናት አነጋገሩ

ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከ12 ዓመታት በፊት በሳውዲ በደረሰበት የህክምና ስህተት እስካሁን ድረስ መናገር የማይችለውን ህጻን እናት አነጋግረዋል፡፡

ሳውዲ አረቢያ ላይ የሚገኝ አንድ ህጻን ከዛሬ 12 ዓመት በፊት አፍንጫው ላይ ቀዶ ህክምና ለማድረግ አንድ ሆስፒታል ከገባ በኋላ በደረሰበት የህክምና ስህተት እስካሁን ድረስ እራሱን እንደማያውቅና መናገር እንደማይችል በማህበራዊ ድረ ገጾች በሰፊው መነጋጋሪያ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ የዚህን ህጻን እናት የሆኑት ወ/ሮ ሀሊማን አግኝንተው አነጋግረዋል፡፡

ከቆይታም በኋላ ህጻኑ የሚገኝበትን ሆስፒታል እንደሚጎበኙ ይጠበቃል፡፡

ከእናቱ ጋር በነበራቸው ቆይታ የህጻኑ እናት ህጻኑን ወደ አገሩ እንዲመለስ መጠየቃቸውን ተከትሎ ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የኢፌዴሪ መንግስት ህጻኑን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመልስ ቃል ገብተዋል፡፡

ህጻኑ ለላለፉት 12 አመታት ምንም መለየት በማይችልበት ሁኔታ “ኮማ” ውስጥ ይገኛል፡፡
የሳውዲ ፍርድ ቤትም ለህጻኑ ካሳ ጭምር እንዲሰጥ ቢወስንም በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን ሳይፈጸም ቆይቷል፡፡

ይህንንም የፍርድ ቤት ውሳኔ ማስፈጸም የሚችልበት ሁኔታ ከሳውዲ ባለስጣናት ጋር መወያየታቸውንም ለእናቱ ገልጸዉላቸዋል፡፡