የእናት ሐሊማና የጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ ወግ (ነቢዩ ሲራክ)

ብርቱ ናት የምላችላሁ እናት ሐሊማ ለገንዘብ ሰብዕናዋን ሽጣ ለልጇ ፍትህ መከበር ስለ እውነት ቃል እምነቷን ሳታዛንፍ 13 አመት በመከራና ስቃይ ተጓዘች። በ13 ኛው አመት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይን አገኘች። እውነቷን ዘርግፋ አጫወተቻቸው። ጠ/ሚኒስትሩም “እህ” ብለው መስማት ያውቃሉና እናት ሐሊማን አዳመጧት!

በመጨረሻም «አይዞሽ፣ በልጅሽ ጉዳይ ከልዑላኑ ጋር ተነጋግረናል፣ አስፈላጊው ካሳችሁ ተከፍሏችሁ በቅርቡ ወደ ሀገር ትገቡ ዘንድ ስምምነት ላይ ተደርሷል» የሚል የደስታ ብስራት እናት ሐሊማን አበሰሯት። እናማ እናት ሐሊማ ስቃ ፈንድቃ የደስታ እንባ እያጎረፈች ተሳሳምን።

እናንተ ሰብዕናን ያስቀደማችሁ የብላቴናው አጋሮች ሆይ ድሉ የሁላችሁም ነው። ምስጋናውም ለእናንተ ነው። ሀገሬ መሪ አግኝታለች። የዜግነት የላቀ ክብሩ የተሰማኝ ታላቁ አርብ ጁምአ የፍትህ ዘመቻችን 13ኛ ሳምንት ስኬት ምክንያቱ ብርቱው የእናት ሐሊማ ጽናትና የእናንተ አጋርነት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድንና ዶር ወርቅነህን ደጋግሜ አመሰግናለሁ።

ለዚህ ደስ የሚል ቀን ላደረሰን ፈጣሪ አምላክ ምስጋና ይድረሰው።