በምዕራብ ሸዋ ዞን የአማራ ተወላጆችን መሬት በመንጠቅ ለኦሮሞ ተወላጅ ወጣቶች እያደለ ነው (ሙሉቀን ተስፋው)

ጉዳዩን ከሥሩ ለማጣራት በምዕራብ ሸዋ ዞን በደል ደርሶብናል ያሉ ገበሬዎችን አነጋግሬ ነበር፡፡ እየሆነ ያለው ይኼው ነው፤

ችግሩ፤ ከግንቦት 1 ቀን 2010 ጀምሮ የአማራ ተወላጆች መሬት በመንጠቅ ማፈናቀል፡፡

ዝርዝር፤ ከግንቦት 1 ቀን ጀምሮ ከክልል በወረደ መመሪያ በምዕራብ ሸዋ ዞን የዳኖ ወረዳ የአማራ ተወላጆችን መሬት በመንጠቅ ለኦሮሞ ተወላጅ ወጣቶች እያደለ ነው፡፡ በወረዳው የአወዲ ጉልፋና አጂላ ዳ ቀበሌ ገበሬዎቹ ከ25 ዓመታት በላይ ግብር እየከፈሉ እያለሙት የኖሩትን መሬት ብቻም ሳይሆን ቤታቸው ጭምር ሳይቀር እየተለካ ለኦሮሞ ተወላጆች ተሰጥቷል፡፡ ቁጥራቸው ከ600 በላይ ቤተሰቦች በሁለቱ ቀበሌዎች ብቻ መሬታቸው እንደተነጠቀ ተገልጧል፡፡ እንደገበሬዎቹ ከሆነ ያላቸውን መሬት በመንጠቅ ራሳቸው ገበሬዎቹ በፈለጉት ጊዜ ይሔዳሉ በሚል ነው የተነጠቁት፡፡

የከፋው ችግር፤ ከዚህ የከፋው ደግሞ ደጋግመው አርሰው ለዘር ያዘጋጁት መሬት ለሌሎች ተላልፎ ሲሰጥ አዲስ የተቀበሉት ሰዎች መጥተው ሊያርሱ ሲሉ መሬታችን አናሳርስም የሚሉትን አማሮች የክልሉ ፖሊስና ሚሊሻ በትራቸውንና ሁሉንም መሣሪያቸውን በመቀማት ወጣቶቹን ሒደው እንዲደበድቧቸው በማድረግ የዘር ግጭት በመቀስቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡

በአሁኑ ሰዐት፤ ከ100 በላይ የሚሆኑ ገበሬዎች ለፌደሬሽን ጉዳዮች ሚንስትርና ለሚመለከታቸው አካላት ቅሬታቸውን ለማሰማት አዲስ አበባ ይገኛሉ፡፡