የዶክተር አብይ የሳዑዲ አረብያ ጉብኝት

ሳዑዲ አረብያን በመጎብኘት ላይ ያሉት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከሳዑዲ አረብያ አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሳልማን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል።

ትናንት ማምሻውን ጂዳ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአልጋ ወራሹ ጋር ባደረጉት ዉይይት ካነሷቸዉ ፤ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በተለያዩ ምክንያቶች የታሰሩ ኢትዮጵውያን እንዲፈቱ ያቀረቡት ጥያቄ አንዱ ነዉ።

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ኢትዮጵያውያን እሥረኞችን ለመፍታት መወሰኑም ተገልጿል። ዶክተር አብይ በጅዲ ቆይታቸው ከተደረገለት ቀዶ ህክምና በኋላ ፣በሐኪሞች ስህተት ሳይነቃ፣ ላለፉት 13 ዓመታት ጂዳ ሆስፒታል የሚገኘውን ታዳጊ ወጣት መሐመድ አብዱልአዚዝን ዛሬ እንደጎበኙም በስፍራው የተገኘው የጂዳው ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ነግሮናል።

ስለ ዶክተር አብይ የሳዑዲ ጉብኝት ከነብዩ ሲራክ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ያዳምጡ ↓