የኢትዮጵያውያን ሃገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሃን) በመጭው እሁድ የመስራች ጉባኤውን ያካሂዳል!!!

የኢትዮጵያውያን ሃገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሃን) በመጭው እሁድ ግንቦት 12 ቀን 2010ዓ.ም የመስራች ጉባኤውን
ያካሂዳል!!!


የኢትዮጵያውያን ሃገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሃን) ባለፉት ጊዚያት ከምርጫ ቦርድ አስፈላጊ ሰነዶችን ወስዶ
በፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ መሰረት አስፈላጊ መስፈርቶችን ለማሟላት በአዲስ አበባና በሌሎች የሃገራችን ክፍሎች አስፈላጊውን እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል።

በተጨማሪም ንቅናቄው በመስራች አባላት መካከል በንቅናቄው ረቂቅ ደንብና ፕሮግራም ላይ የጋራ ግንዛቤ እንዲኖር ውይይቶችን አድርጒል። ኢሃን ለምስረታ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች ሰርቶ በማጠቃለሉ መስራች ጉባኤዎን በመጭው እሁድ ግንቦት 12 ቀን 2010 ዓ.ም የመስራች ጉባኤውን ካሳንችስ ቶታል አካባቢ በሚገኘው ሁሉገብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ያካሂደል።

ንቅናቄው በጉባኤው የንቅናቄውን መተዳደሪያ ደንብ፣
ፕሮግራም፣ አርማና ስያሜ በይፋ የሚያፀድቅ ሲሆን የንቅናቄውን ሊቀመንበርና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችን ይመርጣል።

በተጨማሪም የሃገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ አቋሙን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።