የአማራ ዴሞክራሴያዊ ኃይል ንቅናቄ በወያኔ ሰራዊት ላይ ድል አደረገ።

የአማራ ዴሞክራሴያዌ ኃይል ንቅናቄ / አዴኃን / ይንቀሳቀስበት በነበረበት በጭልጋ ወረዳ ጫንድባ ቀበሌ አካባቢ በቀን 07-09-2010 – ለ0 8- 09-2010 ዓም ጥብ ሌሊት ከወያኔ ወታደር ጋር በተደረገ ውጊያ ሁለት የጠላት ኃይል የተገደለ ሲሆን በዚህ ቀን በአካባቢው የነበረው የአዴኃን ኃይል ቦታ ቢይዝም ጠላት ወያኔ አካባቢውን በማጠናከር የአዴኃን ኃይል ወዳለበት በመቅረብ ለሁለተኛ ቀን በ09-09-2010 — ለ 10-09-2010 ዓም ንጋት ላይ በዚሁ ወረዳ ማለትም/ በጭልጋ ወረዳ/ በፈላሳይባ ቀበሌ በተደረገ ውጊያ ሁለት የፊደራል ወታደር እና አንድ ነበረ የተባለ ፀረ ሽምቅ ሲገደሉ ይዘዋቸው የነበሩ ክላሽኮቭ መሳሬያዋች ከነመሰል ጥይታቸው ተማርከዋል፡፡ የአማራ ዴሞክራሴያዊ ኃይል ንቅናቄ ሰራዊትም አሁን በሰላም ወደስፍራው ተመልሷል፡፡