የእሁድ ስፓርታዊ ዜናዎች

➧ ባየር ሙኒኮች ለባየር ሊቨርኩሰኑ የመስመር ተጨዋች ሊዮን ባይሌ ዝውውር €60m አቅርበዋል።ምንም እንኳን የቡንደስሊጋው ሻምፒዮን ተጨዋቹን የማስፈረም ፍላጎት ቢኖረውም ክለቡ €100m ይፈልጋል።ለሪያል ማድሪድ አሳልፈው ሊሸጡት ይችላሉ።(ESPN)

➧ ምንም እንኳን ኔይማር የሪያል ማድሪድ ቀዳሚ የዝውውር ኢላማ ቢሆንም የጁቬንቱሱ ኮከብ ፓውሎ ዲባላ የማድሪድ ሁለተኛ አማራጭ ነው።ዲባላ ክለቡን እንዲለቅ ከማሲሚሊያኖ አሌግሪ ፈቃድ ሊያገኝ የሚችል ሲሆን በባየር ሙኒክ፣ ባርሴሎና እና አትሌቲኮ ማድሪድ ይፈለጋል።(Don Balon)   

➧ ፔፕ ጋርዲዮላ በቀጣዩ አመት በሻምፒዮንስ ሊጉ ጠንካራ ቡድን ለመገንባት ሙከራ እያደረገ ሲሆን ቶኒ ክሩስን ወደ ማንቸስተር ሲቲ የማምጣት ፍላጎት አለው።ጋርዲዮላ ከተጨዋቹ ጋር በባየር ሙኒክ ቤተሰባዊ ቀረቤታ የነበረው ቢሆንም ተጨዋቹን ለማስፈረም ከጆዜ ሞሪንሆው ማንቸስተር ዩናይትድ ፉክክር ይጠብቀዋል።(Don Balon) 

➧ ሰርጂዮ ራሞስ በሪያል ማድሪድ ያለው ኮንትራት ሲጠናቀቅ ዴቪድ ቤካም በሚያስተዳድረው የአሜሪካውን ሚያሚ ለመቀላቀል እያጤነ ነው።ስፔናዊው ተከላካይ እና የቡድን አጋሩ አሁንም ቢሆን የቅርብ ጓደኞች ሲሆኑ የሚያሚው ክለብ በ2020 የሜጀር ሊግ ሶከርን የሚቀላቀል ይሆናል።(Don Balon)

➧ ሳውዝሃምፕተኖች በጥሩ የዝውውር መስኮት ቨርጂል ቫን ዳይክን ለሊቨርፑል ከለቀቁ በኃላ የተከላካይ ክፍላቸውን ሊያጠናክሩ ነው።በ£20m የሚዲልስብሮውን ተከላካይ ቤን ጊብሰን ቀዳሚ ምርጫቸው ሲሆን በስዋንሲው ጊልፊ ማውሰን ላይም ፍላጎት አላቸው።(The Sun)

➧ አንድሬስ ኢኔስታ በማንቸስተር ሲቲ የሚኬል አርቴታ ተተኪ ሆኖ የተጨዋቾች አሰልጣኝ ሊሆን ይችላል።ዝውውሩ የ34 አመቱን አማካይ ከቀድሞው የባርሴሎና አለቃ ጋር ዳግም የሚያገናኝ ይሆናል።(Yahoo Sports) 

➧ ማንቸስተር ሲቲዎች ቤልጂየማዊው ኮከብ ኤደን ሃዛርድ በክረምቱ ቼልሲን ለመልቀቅ የሚወስን ከሆነ ተጨዋቹን ለማዛወር ዝግጁ ናቸው።ሲቲዎች ለሃዛርድ ዝውውር £100m የሚያቀርቡ ሲሆን በሳምንት £300,000 ሊከፍሉት ዝግጁ ናቸው።(The Sun) 

➧ ፒኤስጂዎች ጂያንሉጂ ቡፎን ጁቬንቱስን በነፃ ዝውውር ሲለቅ የማስፈረም ፍላጎት አላቸው።የፈረንሳዩ ሻምፒዮኖች ለተጨዋቹ ፊት መንሻ በአመት €8m ክፍያ አቅርበውለታል።ይህ ማለት በጁቬንቱስ ከሚከፈለው እጥፍ ነው።(Goal)

➧ ሚኬል አርቴታ በመርህ ደረጃ አዲሱ የአርሰናል አለቃ ለመሆን ከስምምነት ላይ ደርሷል።ምንም እንኳን ምንም አይነት ኮንትራት ባይፈርምም የአርቴታ ወደ ኤምሬትስ ዳግም መመለስ በቀጣዮቹ ቀናት ይፋ ይደረጋል።(Goal)

➧ ስቶክ ሲቲ ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዱን ተከትሎ ፖል ላምበርት ከአራት ወራት ቆይታ በኃላ ክለቡን ለቀዋል።ዴቪድ ሞይስ ክለቡን ለመያዝ ቀዳሚ ምርጫቸው ሲሆኑ ከዌስትሃም ጋር ያላቸው ኮንትራት በመጠናቀቁ ክለቡን መልቀቃቸው የሚታወስ ነው።(Mirror)

➧ ማንቸስተር ዩናይትዶች ከሞናኮው ጂብሪል ሲዲቤ ጋር ንግግር ጀምረዋል።ሞናኮዎች ባለፈው ክረምት ለቤንጃሚን ሜንዲ ከተከፈላቸው £52mበላይ ለሲዲቤ ይጠይቃሉ። 

➧ ምንም እንኳን ፒኤስጂዎች ቶማስ ቱሄልን አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ አድርገው ቢቀጥሩም ፈረንሳዊውን አለቃ አርሰን ቬንገር በጠቅላይ አለቃነት ማና መቅጠር ይፈልጋሉ።(Mirror)

➧ አንቶኒዮ ኮንቴ ምንም እንኳን ማንቸስተር ዩናይትድን አሸንፈው የኤፍኤ ካፑን ዋንጫ ቢያነሱም ቼልሲን ሊለቁ እንደሚችሉ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።(Daily Mirror) 

➧ የሊቨርፑል ደጋፊዎች May 26 ለሚደረገው የሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ይፋዊ ካልሆኑ ምንጮች ትኬቶችን እንዳይገዙ በክለቡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።(Liverpool Echo) 

➧ ከእንግሊዝ የአለም ዋንጫ ውጪ የተደረገው የማንቸስተር ሲቲው ግብ ጠባቂ ጆይ ሃርት ከሳውዝሃምፕተን እና ወልቭስ የዝውውር ጥያቄ ቀርቦለታል።(Daily Mirror)

➧ ማንቸስተር ዩናይትዶች ለላዚዮው አማካይ ሰርጌ ሚሊንኮቪች ሳቪች ዝውውር €91m እና ተጨማሪ ክፍያዎችን አቅርበዋል።(Calciomercato)