በምስራቅ ጎጃም ብአዴን በድንገት መሣሪያ መግፈፍ ጀምሯል፡፡

በምስራቅ ጎጃም ብአዴን በድንገት መሣሪያ መግፈፍ ጀምሯል፡፡ (ሙሉቀን ተስፋው)

በሁለት እጁነሴ ወረዳ ቁስቋም ቀበሌ በግምት ከሞጣ 25 ኪ.ሜ አርሶአደሮችን በድንገት በመክበብ መሳሪ ለመንጠቅ የወረዳው አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ አበረ በላይ፣ የወረዳው ሚሊሻ ኃላፊ ጌታቸው እንዲሁም ሌሎች በርካታ አበሮቻቸውን ይዘው እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ መረጃ ደርሶናል፡፡

በዚህም ግንቦት 1 ቀን ሁለት መሳሪያ የወሰዱ ሲሆን አቶ አዲሱ የኋላ የተባለን ግለሰብ በአፈሙዝ በመምታትና ፒፒስ መሣሪያ በመወሰድ ግለሰቡ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በሕክምና ላይ እንደለ ተነግሯል፡፡

ሁለት መሣሪያ አንድ አልቢንና አንድ ፒፒስ መሣሪያዎች እንደወሰዱ ሕዝቡ መሣሪያውን በመደበቁና በመከላከሉ ሌላ ሰው መንጠቅ አልቻሉም፤ ሆኖም በሌሎች የምስራቅ ጎጃም አካባቢዎችም መሣሪያ ለመንጠቅ እቅድ ስላለ ገበሬዎች መሣሪያቸውን እንዳይቀሙ በንቃት እንዲጠብቁ መረጃውን ማስተላለፍ አስፈላጊ ሆኗል፡፡

በሌላ በኩል እነዚህ ሆድ አደሮች ማለትም አቶ አበረ በላይ የጎንቻ ሲሶነሴ ባህር ጊዎርጊስ አካባቢ የተወለደ ሲሆን ሌላኛው አቶ ጌታቸው ደግሞ የመካነ ሰላም አካባቢ ልጅ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡